ዮሐንስ 12:1 - Compare All Versions

ዮሐንስ 12:1 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ፋሲካ ከሚ​ው​ል​በት ከስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ቀን አስ​ቀ​ድሞ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከሙ​ታን ያስ​ነ​ሣው አል​ዓ​ዛር ወደ ነበ​ረ​በት ወደ ቢታ​ንያ መጣ።

ዮሐንስ 12:1 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

የፋሲካ በዓል ስድስት ቀን ሲቀረው፣ ኢየሱስ ከሞት ያስነሣው አልዓዛር ወደሚኖርበት፣ ወደ ቢታንያ መጣ።

ዮሐንስ 12:1 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ከፋሲካም በፊት በስድስተኛው ቀን ኢየሱስ ከሙታን ያስነሣው አልዓዛር ወደ ነበረበት ወደ ቢታንያ መጣ።

ዮሐንስ 12:1 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

የአይሁድ የፋሲካ በዓል ሊከበር ስድስት ቀን ሲቀረው፥ ኢየሱስ ወደ ቢታንያ ሄደ፤ ቢታንያ ኢየሱስ ከሞት ያስነሣው አልዓዛር የሚኖርባት መንደር ነች።

ዮሐንስ 12:1 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ከፋሲካም በፊት በስድስተኛው ቀን ኢየሱስ ከሙታን ያስነሣው አልዓዛር ወደ ነበረበት ወደ ቢታንያ መጣ።