የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዮሐንስ 11:1-11

ዮሐንስ 11:1-11 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

የማ​ር​ያ​ምና የእ​ኅቷ የማ​ርታ መን​ደር በሚ​ሆን በቢ​ታ​ንያ ስሙ አል​ዓ​ዛር የሚ​ባል የታ​መመ አንድ ሰው ነበር። ማር​ያም ግን ጌታ​ች​ንን ሽቱ የቀ​ባ​ችው፥ እግ​ሩ​ንም በጠ​ጕ​ርዋ ያሸ​ችው ናት፤ ወን​ድ​ምዋ አል​ዓ​ዛ​ርም ታሞ ነበር። እኅ​ቶ​ቹም፥ “ጌታ​ችን ሆይ፥ እነሆ፥ የም​ት​ወ​ደው ታሞ​አል” ብለው ወደ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ላኩ። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ሰምቶ እን​ዲህ አለ፥ “ይህ ደዌ በእ​ርሱ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ይከ​ብር ዘንድ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ነው እንጂ ለሞት አይ​ደ​ለም።” ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ማር​ታ​ንና እኅ​ቷን ማር​ያ​ምን፥ አል​ዓ​ዛ​ር​ንም ይወ​ዳ​ቸው ነበር። እንደ ታመመ በሰማ ጊዜM በነ​በ​ረ​በት ቦታ ሁለት ቀን ቈየ። ከዚ​ህም በኋላ፥ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱን፥ “ኑ፥ ወደ ይሁዳ ሀገር ደግሞ እን​ሂድ” አላ​ቸው። ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም፥ “መም​ህር ሆይ፥ አይ​ሁድ ሊወ​ግ​ሩህ ይሹ አል​ነ​በ​ረ​ምን? ዛሬ ደግሞ አንተ ወደ​ዚያ ልት​ሄድ ትሻ​ለ​ህን?” አሉት። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ቀኑ ዐሥራ ሁለት ሰዓት አይ​ደ​ለ​ምን? በቀን የሚ​ሄድ አይ​ሰ​ና​ከ​ልም፤ የዚ​ህን ዓለም ብር​ሃን ያያ​ልና። በሌ​ሊት የሚ​ሄድ ግን ይሰ​ነ​ካ​ከ​ላል፤ በው​ስጡ የሚ​ያ​የው ብር​ሃን የለ​ምና።” ይህ​ንም ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ነገ​ራ​ቸው፤ ከዚ​ህም በኋላ፥ “ወዳ​ጃ​ችን አል​ዓ​ዛር ተኝ​ቶ​አል፤ ነገር ግን ላነ​ቃው እሄ​ዳ​ለሁ” አላ​ቸው።

ዮሐንስ 11:1-11 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በማርያምና በእኅቷ በማርታ መንደር በቢታንያ ይኖር የነበረው አልዓዛር ታሞ ነበር። ይህች ወንድሟ አልዓዛር የታመመባት ማርያም፣ በጌታ ላይ ሽቱ አፍስሳ እግሩን በጠጕሯ ያበሰችው ነበረች። እኅትማማቾቹም፣ “ጌታ ሆይ፤ የምትወድደው ሰው ታምሟል” ብለው መልእክት ላኩበት። ኢየሱስ ይህን በሰማ ጊዜ፣ “ይህ ሕመም የእግዚአብሔር ልጅ በእርሱ ይከብር ዘንድ ለእግዚአብሔር ክብር ነው እንጂ ለሞት የሚያደርስ አይደለም” አለ። ኢየሱስም ማርታን፣ እኅቷንና አልዓዛርን ይወድዳቸው ነበር። ሆኖም አልዓዛር መታመሙን በሰማ ጊዜ፣ በነበረበት ስፍራ ሁለት ቀን ቈየ። ከዚህም በኋላ ደቀ መዛሙርቱን፣ “ወደ ይሁዳ እንመለስ” አላቸው። እነርሱም፣ “መምህር ሆይ፤ ከጥቂት ጊዜ በፊት አይሁድ በድንጋይ ሊወግሩህ እየፈለጉህ ነበር፤ እንደ ገና ወደዚያ ትሄዳለህን?” አሉት። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ቀኑ ዐሥራ ሁለት ሰዓት ብርሃን አይደለምን? ከዚህ ዓለም ብርሃን የተነሣ ስለሚያይ በቀን የሚመላለስ አይሰናከልም፤ የሚሰናከለው ግን በሌሊት የሚመላለስ ነው፤ ብርሃን የለውምና።” ይህን ከነገራቸው በኋላ፣ “ወዳጃችን አልዓዛር ተኝቷል፤ እኔም ከእንቅልፉ ላስነሣው እሄዳለሁ” አላቸው።

ዮሐንስ 11:1-11 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ከማርያምና ከእኅትዋ ከማርታ መንደር ከቢያትንያ የሆነ አልዓዛር የሚባል አንድ ሰው ታሞ ነበር። ማርያምም ጌታን ሽቱ የቀባችው እግሩንም በጠጕርዋ ያበሰሰችው ነበረች፤ ወንድምዋም አልዓዛር ታሞ ነበር። ስለዚህ እኅቶቹ “ጌታ ሆይ፥ እነሆ የምትወደው ታሞአል” ብለው ወደ እርሱ ላኩ። ኢየሱስም ሰምቶ፦ “ይህ ህመም የእግዚአብሔር ልጅ በእርሱ ይከብር ዘንድ ስለ እግዚአብሔር ክብር ነው እንጂ ለሞት አይደለም” አለ። ኢየሱስም ማርታንና እኅትዋን አልዓዛርንም ይወድ ነበር። እንደ ታመመም በሰማ ጊዜ ያን ጊዜ በነበረበት ስፍራ ሁለት ቀን ዋለ፤ ከዚህም በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ፦ “ወደ ይሁዳ ደግሞ እንሂድ” አላቸው። ደቀ መዛሙርቱ፦ “መምህር ሆይ፥ አይሁድ ከጥቂት ጊዜ በፊት ሊወግሩህ ይፈልጉ ነበር፥ ደግሞም ወደዚያ ትሄዳለህን?” አሉት። ኢየሱስም መልሶ፦ “ቀኑ አሥራ ሁለት ሰዓት አይደለምን? በቀን የሚመላለስ ቢኖር የዚህን ዓለም ብርሃን ያያልና አይሰናከልም፤ በሌሊት የሚመላለስ ቢኖር ግን ብርሃን በእርሱ ስለ ሌለ ይሰናከላል” አላቸው። ከዚህም በኋላ፦ “ወዳጃችን አልዓዛር ተኝቶአል፤ ነገር ግን ከእንቅልፉ ላስነሣው እሄዳለሁ” አላቸው።

ዮሐንስ 11:1-11 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

በቢታንያ የሚኖር አልዓዛር የሚባል አንድ ሰው ታሞ ነበር፤ ቢታንያ ማርያምና እኅትዋ ማርታ የሚኖሩባት መንደር ነበረች። ይህች ማርያም የጌታን እግር ሽቶ የቀባችውና በጠጒርዋ ያበሰችው ናት፤ የታመመውም አልዓዛር የእርስዋ ወንድም ነበር። እኅትማማቾቹም “ጌታ ሆይ፥ ያ የምትወደው ታሞአል” ብለው ወደ ኢየሱስ ላኩበት። ኢየሱስም ይህን በሰማ ጊዜ፥ “ይህ ሕመም ለሞት የሚያደርስ አይደለም፤ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ክብር እንዲሆንና የእግዚአብሔር ልጅም በዚህ ምክንያት እንዲከበር ነው” አለ። ኢየሱስ ማርታንና እኅትዋን ማርያምን ወንድማቸውን አልዓዛርንም ይወድ ነበር። ሆኖም የአልዓዛርን መታመም በሰማ ጊዜ በነበረበት ቦታ ሁለት ቀን ቈየ። ከዚህ በኋላ ደቀ መዛሙርቱን፥ “ወደ ይሁዳ ምድር እንደገና እንሂድ” አላቸው። ደቀ መዛሙርቱም “መምህር ሆይ! አይሁድ ከጥቂት ጊዜ በፊት ሊወግሩህ ይፈልጉ ነበር፤ ታዲያ እንደገና ወደዚያ ተመልሰህ ትሄዳለህን?” አሉት። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “በቀን ውስጥ ያለው ጊዜ ዐሥራ ሁለት ሰዓት አይደለምን? በቀን የሚመላለስ የዚህን ዓለም ብርሃን ስለሚያይ አይሰናከልም። ነገር ግን በሌሊት የሚመላለስ ብርሃን ስለሌለው ይሰናከላል።” ኢየሱስ ይህን ካላቸው በኋላ፥ “ወዳጃችን አልዓዛር አንቀላፍቶአል፤ እኔ ግን ከእንቅልፉ ላስነሣው እሄዳለሁ” አለ።

ዮሐንስ 11:1-11 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

አንድ ሰው ታሞ ነበር፤ እርሱም እንደ ማርያምና እንደ እኅትዋ ማርታ ከቢታንያ የነበረው አልዓዛር ነው። ማርያም ጌታን ሽቱ የቀባችው፥ እግሩንም በጠጉርዋ ያበሰችው ስትሆን፤ የታመመውም አልዓዛር ወንድምዋ ነበር። ስለዚህም እኅቶቹ “ጌታ ሆይ! እነሆ የምትወደው ታሞአል፤” ብለው ወደ እርሱ ላኩበት። ኢየሱስም ሰምቶ “ይህ ሕመም ለሞት አይሰጥም፤ ይልቁንም ለእግዚአብሔር ክብር መገለጫ ነው፤ የእግዚአብሔር ልጅ በእርሱ ይከብር ዘንድ ነው” አለ። ኢየሱስም ማርታንና እኅትዋን እንዲሁም አልዓዛርን ይወድ ነበር። እንደ ታመመም በሰማ ጊዜ ያንጊዜ በነበረበት ስፍራ ሁለት ቀን ዋለ፤ ከዚህም በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ “ወደ ይሁዳ እንደገና እንሂድ፤” አላቸው። ደቀመዛሙርቱ “መምህር ሆይ! አይሁድ ከጥቂት ጊዜ በፊት ሊወግሩህ ይፈልጉ ነበር፤ በድጋሚ ወደዚያ ትሄዳለህን?” አሉት። ኢየሱስም መልሶ “በቀን ውስጥ ዐሥራ ሁለት ሰዓት ይገኙ የለምን? በቀን የሚመላለስ የዚህን ዓለም ብርሃን ያያልና አይሰናከልም፤ በሌሊት የሚመላለስ ቢኖር ግን ብርሃን በእርሱ ስለ ሌለ ይሰናከላል፤” አላቸው። ይህንንም ከተናገረ በኋላ “ወዳጃችን አልዓዛር ተኝቶአል፤ ነገር ግን ከእንቅልፉ ላስነሣው እሄዳለሁ፤” አላቸው።