የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መሳፍንት 6:33-40

መሳፍንት 6:33-40 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ምድ​ያ​ምና አማ​ሌ​ቅም ሁሉ፥ የም​ሥ​ራ​ቅም ልጆች አንድ ሆነው ተሰ​በ​ሰቡ፤ ተሻ​ግ​ረ​ውም በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል ሸለቆ ሰፈሩ። ጌዴ​ዎ​ን​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ አጸ​ናው፤ እር​ሱም ቀንደ መለ​ከ​ቱን ነፋ፤ አብ​ዔ​ዜ​ርም በኋ​ላው ጮኸ። ወደ ምና​ሴም ነገድ ሁሉ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ እር​ሱም ከኋ​ላው ሆኖ ጮኸ፤ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ች​ንም ወደ አሴ​ርና ወደ ዛብ​ሎን ወደ ንፍ​ታ​ሌ​ምም ላከ፤ እነ​ር​ሱም ሊቀ​በ​ሉ​አ​ቸው ወጡ። ጌዴ​ዎ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “እንደ ተና​ገ​ርህ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በእኔ እጅ ታድን እንደ ሆነ፥ እነሆ! በዐ​ው​ድ​ማዉ ላይ የተ​ባ​ዘተ የበግ ጠጕር አኖ​ራ​ለሁ፤ በጠ​ጕሩ ብቻ ላይ ጠል ቢሆን በም​ድ​ሩም ሁሉ ደረቅ ቢሆን፥ እንደ ተና​ገ​ርህ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በእኔ እጅ እን​ደ​ም​ታ​ድ​ና​ቸው አው​ቃ​ለሁ” አለ። እን​ዲ​ሁም ሆነ፤ በነ​ጋው ማልዶ ተነሣ፤ ጠጕ​ሩ​ንም ጨመ​ቀው፤ ከጠ​ጕ​ሩም የተ​ጨ​መ​ቀው ጠል አንድ መን​ቀል ሙሉ ውኃ ሆነ። ጌዴ​ዎ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አለው፥ “በቍ​ጣህ አት​ቈ​ጣኝ፤ ደግሞ አን​ዲት ነገር ልና​ገር፤ ጠጕሩ ብቻ​ውን ደረቅ ይሁን፤ በም​ድ​ሩም ላይ ጠል ይው​ረድ።” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚ​ያች ሌሊት እን​ዲሁ አደ​ረገ፤ ጠጕሩ ብቻ ደረቅ ሆነ፥ በም​ድ​ሩም ሁሉ ላይ ጠል ወረደ።

መሳፍንት 6:33-40 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በዚህ ጊዜ ምድያማውያን ሁሉ፣ አማሌቃውያንና ሌሎች የምሥራቅ ሕዝቦች ኀይላቸውን አስተባብረው የዮርዳኖስን ወንዝ በመሻገር በኢይዝራኤል ሸለቆ ሰፈሩ። ከዚያም የእግዚአብሔር መንፈስ በጌዴዎን ላይ ወረደ፤ እርሱም መለከት ነፋ፤ አቢዔዝራውያን እንዲከተሉት ጠራቸው። እንዲሁም በመላው የምናሴ ምድር መልእክተኞቹን ልኮ እንዲከተሉት ጥሪ አደረገ፤ ደግሞም የአሴር፣ የዛብሎንና የንፍታሌም ሰዎች ወጥተው እንዲገጥሟቸው መልእክተኛ ላከባቸው። ጌዴዎን እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “በተናገርኸው መሠረት እስራኤላውያንን በእጄ የምታድናቸው ከሆነ፣ እነሆ፤ የበግ ጠጕር ባዘቶ በዐውድማው ላይ አኖራለሁ። ምድሩ በሙሉ ደረቅ ሆኖ ባዘቶው ላይ ብቻ ጤዛ ቢኖር፣ እንዳልኸው እስራኤላውያንን በእኔ እጅ እንደምታድናቸው ዐውቃለሁ።” እንደዚሁ ሆነ፤ ጌዴዎን በማግስቱም ጧት ማልዶ ተነሣ፤ ባዘቶውንም ሲጨምቅ የወጣው ውሃ አንድ ቈሬ ሞላ። ከዚያም ጌዴዎን እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “እባክህ አትቈጣኝ፤ አንዲት ጥያቄ እንደ ገና ልጠይቅ። በጠጕሩ ባዘቶ ላይ ሌላ ሙከራ እንዳደርግ ፍቀድልኝ፤ በዚህ ጊዜ ምድሩ ሁሉ በጤዛ ተሸፍኖ ባዘቶው ደረቅ ይሁን።” በዚያች ሌሊት እግዚአብሔር እንደ ተጠየቀው አደረገ፤ ምድሩ በሙሉ በጤዛ ሲሸፈን፣ ባዘቶው ብቻ ደረቅ ሆነ።

መሳፍንት 6:33-40 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ምድያማውያንም አማሌቃውውያንም ሁሉ የምሥራቅም ሰዎች አንድ ሆነው ተሰበሰቡ፥ ዮርዳኖስንም ተሻገሩ፥ በኢይዝራኤልም ሸለቆ ሰፈሩ። የእግዚአብሔርም መንፈስ በጌዴዎን ገባበት፥ እርሱም ቀንደ መለከቱን ነፋ፥ የአቢዔዝርም ሰዎች ተጠርተው በኋላው ተከተሉት። ወደ ምናሴም ነገድ ሁሉ መልክተኞችን ሰደደ እነርሱም ደግሞ ተጠርተው በኋላው ተከተሉት፥ መልክተኞችንም ወደ አሴርና ወደ ዛብሎን ወደ ንፍታሌምም ሰደደ፥ እነርሱም ሊገናኙአቸው ወጡ። ጌዴዎንም እግዚአብሔርን፦ እንደ ተናገርህ የእስራኤልን ልጆች በእኔ እጅ ታድን እንደ ሆነ፥ እነሆ፥ በአውድማው ላይ የተባዘተ የበግ ጠጉር አኖራለሁ፥ በጠጉሩ ብቻ ላይ ጠል ቢሆን በምድሩም ሁሉ ደረቅ ቢሆን፥ እንደ ተናገርህ የእስራኤልን ልጆች በእኔ እጅ እንድታድናቸው አውቃለሁ አለ። እንዲሁም ሆነ፥ በነጋውም ማልዶ ተነሣ፥ ጠጉሩንም ጨመቀው፥ ከጠጉሩም የተጨመቀው ጠል ቆሬ ሙሉ ውኃ ሆነ። ጌዴዎንም እግዚአብሔርን፦ እኔ ይህን አንድ ጊዜ ስናገር አትቈጣኝ፥ እኔ ይህን አንድ ጊዜ በጠጉሩ፥ እባክህ፥ ልፈትን፥ አሁንም በጠጉሩ ብቻ ላይ ደረቅ ይሁን፥ በምድሪቱም ሁሉ ላይ ጠል ይሁን አለው። እግዚአብሔርም በዚያ ሌሊት እንዲሁ አደረገ፥ በጠጉሩ ብቻ ላይ ደረቅ ነበረ፥ በምድሩም ሁሉ ላይ ጠል ነበረ።

መሳፍንት 6:33-40 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ከዚያም በኋላ ምድያማውያን፥ ዐማሌቃውያንና የምሥራቅ ሰዎች በአንድነት ተሰብስበው የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻገሩ፤ በኢይዝራኤል ሸለቆም ሰፈሩ። የእግዚአብሔር መንፈስ በጌዴዎን ላይ ወረደ፤ የአቢዔዜር ጐሣ ሰዎች ሁሉ እንዲከተሉት እነርሱን ለመጥራት እምቢልታ ነፋ፤ የምናሴን ነገድ ሁሉ መልእክት ልኮ ይከተሉት ዘንድ አስጠራቸው፤ እንዲሁም ወደ አሴር፥ ወደ ዛብሎንና ወደ ንፍታሌም ነገዶች መልእክተኞች ላከ፤ እነርሱም ከሌሎቹ ጋር ለመሰለፍ ወጡ። ከዚህ በኋላ ጌዴዎን እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፦ “እንደ ተናገርከው እስራኤልን በእኔ እጅ ታድን ዘንድ መርጠኸኛል። እነሆ! ስንዴ በምንወቃበት አውድማ ላይ የተባዘተ የበግ ጠጒር አስቀምጣለሁ፤ ነገ ጧት ሌላው ምድር ሁሉ ደረቅ ሆኖ በዚህ ጠጒር ባዘቶ ላይ ብቻ ጤዛ ከሆነ፥ እንደ ተናገርከው እስራኤልን ለማዳን የመረጥከኝ መሆኑን አረጋግጣለሁ።” ልክ እርሱ እንዳለውም ሆነለት፤ ጌዴዎን ጧት በማለዳ በተነሣ ጊዜ የበግ ጠጒሩን ባዘቶ ሲጨምቀው በአንድ መቅጃ የሚሞላ ውሃ ከውስጡ ወጣ። ቀጥሎም ጌዴዎን እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “እባክህ አትቈጣኝ፤ እንደገና አንድ ጊዜ እንድናገር ፍቀድልኝ፤ ይኸውም በበግ ጠጒሩ ባዘቶ ላይ ሌላ ምልክት እንዲታይ ልጠይቅ፤ በዚህን ጊዜ የጠጒሩ ባዘቶ ደረቅ ሆኖ በዙሪያው ያለው ምድር እርጥብ እንዲሆን አድርግልኝ።” በዚያን ሌሊት እግዚአብሔር ያንኑ ምልክት አደረገ፤ በማግስቱ ጧት የጠጒሩ ባዘቶ ደረቅ ሆኖ በዙሪያው ያለው መሬት ግን በጤዛ ርሶ ተገኘ።

መሳፍንት 6:33-40 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

በዚህ ጊዜ ምድያማውያን ሁሉ፥ አማሌቃውያንና ሌሎች የምሥራቅ ሕዝቦች ያላቸውን አስተባብረው የዮርዳኖስን ወንዝ በመሻገር በኢይዝራኤል ሸለቆ ሰፈሩ። ከዚያም የጌታ መንፈስ በጌዴዎን ላይ ወረደ፤ እርሱም መለከት ነፋ፤ አቢዔዝራውያን እንዲከተሉት ጠራቸው። እንዲሁም በመላው የምናሴ ምድር መልእክተኞቹን ልኮ እንዲከተሉት ጥሪ አደረገ፤ ደግሞም የአሴር፥ የዛብሎንና የንፍታሌም ሰዎች ወጥተው እንዲገጥሟቸው መልእክተኛ ላከባቸው። ጌዴዎን እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “በተናገርኸው መሠረት እስራኤላውያንን በእጄ የምታድናቸው ከሆነ፥ እነሆ፤ የበግ ጠጉር ባዘቶ በአውድማው ላይ አኖራለሁ። ምድሩ በሙሉ ደረቅ ሆኖ ባዝቶው ላይ ብቻ ጤዛ ቢኖር፥ እንዳልከው እስራኤላውያንን በእኔ እጅ እንደምታድናቸው አውቃለሁ።” እንደዚሁም ሆነ፤ ጌዴዎን በማግስቱ ጠዋት ማልዶ ተነሣ፤ ባዘቶውንም ሲጨምቅ የወጣው ውሃ አንድ ቆሬ ሞላ። ከዚያም ጌዴዎን እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “እባክህ አትቈጣኝ፤ አንዲት ጥያቄ እንደገና ልጠይቅ። በጠጉሩ ባዘቶ ላይ ሌላ ሙከራ እንዳደርግ ፍቀድልኝ፤ በዚህ ጊዜ ምድሩ ሁሉ በጤዛ ተሸፍኖ ባዘቶው ደረቅ ይሁን።” በዚያች ሌሊት እግዚአብሔር እንደጠየቀው አደረገ፤ ባዘቶው ብቻ ደረቅ ሲሆን፥ ምድሩ በሙሉ በጤዛ ተሸፍኖ ነበር።