የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መሳፍንት 6:28-32

መሳፍንት 6:28-32 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

የከ​ተ​ማ​ውም ሰዎች ማል​ደው ተነሡ፤ እነ​ሆም፥ የበ​ዓል መሠ​ዊያ ፈርሶ፥ በዙ​ሪ​ያ​ውም ያለው የማ​ም​ለ​ኪያ ዐጸድ ተቈ​ርጦ፥ በተ​ሠ​ራ​ውም መሠ​ዊያ ላይ ሁለ​ተ​ኛው በሬ ተሠ​ውቶ አገ​ኙት። እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “ይህን ነገር ያደ​ረገ ማን ነው?” ተባ​ባሉ። በጠ​የ​ቁና በመ​ረ​መ​ሩም ጊዜ፥ “ይህን ነገር ያደ​ረገ የኢ​ዮ​አስ ልጅ ጌዴ​ዎን ነው” አሉ። የከ​ተ​ማ​ዉም ሰዎች ኢዮ​አ​ስን፥ “የበ​ዓ​ልን መሠ​ዊያ አፍ​ር​ሶ​አ​ልና፥ በዙ​ሪ​ያ​ውም ያለ​ውን የማ​ም​ለ​ኪያ ዐጸድ ቈር​ጦ​አ​ልና ይገ​ደል ዘንድ ልጅ​ህን አምጣ” አሉት። ኢዮ​አ​ስም በእ​ርሱ ላይ የተ​ነ​ሡ​በ​ትን ሁሉ፥ “ለበ​ዓል እና​ንተ ዛሬ ትበ​ቀ​ሉ​ለ​ታ​ላ​ች​ሁን? ወይስ የበ​ደ​ለ​ውን ትገ​ድ​ሉ​ለት ዘንድ የም​ታ​ድ​ኑት እና​ንተ ናች​ሁን? እርሱ አም​ላክ ከሆ​ነስ የበ​ደ​ለው እስከ ነገ ድረስ ይሙት። መሠ​ዊ​ያ​ዉ​ንም ያፈ​ረ​ሰ​ውን እርሱ ይበ​ቀ​ለው” አላ​ቸው። በዚ​ያች ቀንም መሠ​ዊ​ያ​ዉን አፍ​ር​ሶ​አ​ልና በዓል ከእ​ርሱ ጋር ይሟ​ገት ሲል ጌዴ​ዎ​ንን ይሩ​በ​ኣል ብሎ ጠራው።

መሳፍንት 6:28-32 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ሌሊቱ ነግቶ የከተማው ሕዝብ ከመኝታው ሲነሣ፣ የበኣል መሠዊያ ፈርሶ በአጠገቡ የቆመው የአሼራ ምስል ተሰባብሮ፣ አዲስ በተሠራው መሠዊያ ላይ ሁለተኛው ወይፈን ተሠውቶ ነበር። እነርሱም፣ “ይህን ያደረገ ማን ነው?” በማለት እርስ በርሳቸው ተጠያየቁ። ነገሩን በጥብቅ ሲከታተሉም፣ “የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን መሆኑን ደረሱበት።” የከተማዪቱም ሰዎች ኢዮአስን፣ “የበኣልን መሠዊያ ያፈረሰና በአጠገቡ የቆመውን የአሼራን ምስል ዐምድ የሰበረው ልጅህ በመሆኑ መሞት ስላለበት አውጣልን አሉት።” በዚህ ጊዜ ኢዮአስ በቍጣ ለገነፈለውና በዙሪያው ለነበረው ሕዝብ እንዲህ አለ፤ “ለበኣል ትሟገቱለታላችሁን? ልታድኑትስ ትሞክራላችሁን? ለእርሱ የሚሟገትለት ቢኖር እስከ ጧት ይሙት! እንግዲህ በኣል በርግጥ አምላክ ከሆነ መሠዊያውን ሲያፈርሱበት ራሱን ሊከላከል ይችላል።” ስለዚህም፣ “መሠዊያውን አፍርሶበታልና ራሱ በኣል ይሟገተው” ሲሉ በዚያ ዕለት ጌዴዎንን፣ “ይሩበኣል” ብለው ጠሩት።

መሳፍንት 6:28-32 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

በማግስቱ የከተማይቱ ኗሪዎች ማልደው በተነሡ ጊዜ ለባዓል የተሠራው መሠዊያ መፍረሱንና የአሼራም ምስል ተሰባብሮ መውደቁን አዩ፤ ከዚያም በተሠራው መሠዊያ ላይ ሁለተኛው ኰርማ ታርዶ የሚቃጠል መሥዋዕት ሆኖ መቅረቡን ተመለከቱ። እርስ በርሳቸውም “ይህን ያደረገ ማን ነው?” በማለት ተጠያየቁ፤ ብዙ ከተመራመሩም በኋላ ይህን ያደረገው የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን መሆኑን ደረሱበት፤ ከዚህም በኋላ ኢዮአስን “የባዓልን መሠዊያ ስላፈረሰና በአጠገቡ ያለውንም የአሼራን ምስል ሰባብሮ ስለ ጣለ፥ እንዲሞት ልጅህን ወዲህ አውጣልን!” አሉት። ኢዮአስ ግን በቊጣ ተነሣሥተው በእርሱ ላይ የመጡትን ሁሉ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ለበዓል ትሟገታላችሁን? እርሱንስ ታድኑታላችሁን? ለእርሱ የሚሟገትለት ሁሉ እስከ ነገ ጧት ይገደላል፤ እርሱ አምላክ ከሆነ መሠዊያውን ካፈረሰው ሰው ጋር ለራሱ እስቲ ይሟገት!” ከዚህ በኋላ ኢዮአስ “ፈራርሶ የወደቀው የእርሱ መሠዊያ ስለ ሆነ እስቲ ይችል እንደ ሆነ ባዓል ራሱን ይከላከል፤” ለማለት ፈልጎ፥ ለጌዴዎን ይሩባዓል የሚል ስም አወጣለት።

መሳፍንት 6:28-32 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ሌሊቱ ነግቶ የከተማው ሕዝብ ከመኝታው ሲነሣ፥ የበኣል መሠዊያ ፈርሶ በአጠገቡ የቆመው የአሼራ ምስል ተሰባብሮ፥ አዲስ በተሠራው መሠዊያ ላይ ሁለተኛው ወይፈን ተሠውቶ ነበር። እነርሱም፥ “ይህን ያደረገ ማን ነው?” በማለት እርስ በርሳቸው ተጠያየቁ። ነገሩን በጥብቅ ሲከታተሉም፥ “የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን መሆኑን ደረሱበት።” የከተማይቱም ሰዎች ኢዮአስን፥ “የበኣልን መሠዊያ ያፈረሰና በአጠገቡ የቆመውን የአሼራን ምስል ዐምድ የሰበረው ልጅህ በመሆኑ መሞት ስላለበት አውጣልን አሉት።” በዚህ ጊዜ ኢዮአስ በቊጣ ለገነፈለውና በዙሪያው ለነበረው ሕዝብ እንዲህ አለ፤ “ለበኣል ትሟገቱለታላችሁን? ልታድኑትስ ትሞክራላችሁን? ለእርሱ የሚሟገትለት ቢኖር እስከ ጠዋት ይሙት! እንግዲህ በኣል በእርግጥ አምላክ ከሆነ መሠዊያውን ሲያፈርሱበት ራሱን ሊከላከል ይችላል።” ስለዚህም፥ “መሠዊያውን አፍርሶበታልና ራሱ በኣል ይሟገተው” ሲሉ በዚያ ዕለት ጌዴዎንን፥ “ይሩበኣል” ብለው ጠሩት።