መሳፍንት 10:6-16

መሳፍንት 10:6-16 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፤ በዓ​ሊ​ም​ንና አስ​ታ​ሮ​ትን፥ የሶ​ር​ያ​ንም አማ​ል​ክት፥ የሲ​ዶ​ና​ንም አማ​ል​ክት፥ የሞ​ዓ​ብ​ንም አማ​ል​ክት፥ የአ​ሞ​ን​ንም ልጆች አማ​ል​ክት፥ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ን​ንም አማ​ል​ክት አመ​ለኩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ተዉ፤ አላ​መ​ለ​ኩ​ት​ምም። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ፈጽሞ ተቈጣ፤ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅና በአ​ሞን ልጆች እጅም አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው። በዚ​ያም ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሥቃይ አበ​ዙ​ባ​ቸው፤ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ሀገር በገ​ለ​ዓድ ውስጥ ያሉ​ትን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሁሉ ዐሥራ ስም​ንት ዓመት አስ​ጨ​ነ​ቁ​አ​ቸው። የአ​ሞ​ንም ልጆች ከይ​ሁዳ፥ ከብ​ን​ያ​ምና ከኤ​ፍ​ሬም ቤት ጋር ደግሞ ሊዋጉ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገሩ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም እጅግ ተጨ​ነቁ። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች፥ “አን​ተን አም​ላ​ካ​ች​ንን ትተን በዓ​ሊ​ምን አም​ል​ከ​ና​ልና ኀጢ​አት ሠር​ተ​ናል” ብለው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች አላ​ቸው፥ “ግብ​ፃ​ው​ያን፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ የአ​ሞ​ንና የሞ​አ​ብም ልጆች፥ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም፥ ሲዶ​ና​ው​ያ​ንም፥ ምድ​ያ​ማ​ው​ያ​ንም፥ አማ​ሌ​ቃ​ው​ያ​ንም አላ​ስ​ጨ​ነ​ቋ​ች​ሁ​ምን? ወደ እኔም ጮኻ​ችሁ፤ እኔም ከእ​ጃ​ቸው አዳ​ን​ኋ​ችሁ። እና​ንተ ግን ተዋ​ች​ሁኝ፤ ሌሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት አመ​ለ​ካ​ችሁ፤ ስለ​ዚ​ህም ደግሞ አላ​ድ​ና​ች​ሁም። ሄዳ​ችሁ ወደ መረ​ጣ​ች​ኋ​ቸው አማ​ል​ክት ጩኹ፤ እነ​ር​ሱም በመ​ከ​ራ​ችሁ ጊዜ ያድ​ኑ​አ​ችሁ።” የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “እኛ ኀጢ​አ​ትን ሠር​ተ​ናል፤ አንተ በፊ​ትህ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝ​ህን አድ​ር​ግ​ብን፤ ዛሬ ግን እባ​ክህ አድ​ነን” አሉት። ሌሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አስ​ወ​ገዱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ብቻ አመ​ለኩ፤ ደስም አሰ​ኙት፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከሥ​ቃይ የተ​ነሣ አእ​ም​ሮ​አ​ቸ​ውን አጥ​ተው ነበር።

መሳፍንት 10:6-16 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እስራኤላውያን እንደ ገና በእግዚአብሔር ላይ ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ በኣልንና አስታሮትን እንዲሁም የአራምን፣ የሲዶናን፣ የሞዓብን፣ የአሞንንና የፍልስጥኤማውያንን አማልክት አመለኩ፤ እስራኤላውያን እግዚአብሔርን ስለ ተዉና ስላላገለገሉት፣ እግዚአብሔርም ተቈጣቸው፤ በፍልስጥኤማውያንና በአሞናውያን እጅ ሸጣቸው፤ እነርሱም በዚያ ዓመት ሰበሯቸው፤ አደቀቋቸውም፤ ለዐሥራ ስምንት ዓመታት ከዮርዳኖስ ማዶ ባለው የአሞራውያን ምድር፣ በገለዓድ የነበሩትን እስራኤላውያንን ሁሉ አሠቃዩአቸው። እንዲሁም አሞናውያን ይሁዳን፣ ብንያምንና የኤፍሬምን ቤት ለመውጋት ዮርዳኖስን ስለ ተሻገሩ እስራኤላውያን እጅግ ተጨነቁ። ከዚያም እስራኤላውያን፣ “አንተን አምላካችንን በመተው የበኣልን አማልክት በማምለካችን አንተን በድለናል” ብለው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ። እግዚአብሔርም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “ግብጻውያን፣ አሞራውያን፣ አሞናውያን፣ ፍልስጥኤማውያን፣ ሲዶናውያን፣ አማሌቃውያንና ማዖናውያን አሠቃዩአችሁ፤ እናንተም እንድረዳችሁ ወደ እኔ ጮኻችሁ፤ ታዲያ እኔ ከእጃቸው አላዳንኋችሁምን? እናንተ ግን እኔን ትታችሁ ሌሎች አማልክትን አመለካችሁ፤ ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲያ አላድናችሁም፤ ሂዱና ወደ መረጣችኋቸው አማልክት ጩኹ፤ መከራ በሚያገኛችሁ ጊዜ እስኪ ያድኗችሁ።” እስራኤላውያንም እግዚአብሔርን፣ “ኀጢአት ሠርተናል፤ መልካም መስሎ የታየህን አድርግብን፤ እባክህን የዛሬን ብቻ አድነን” አሉት። ከዚያም በመካከላቸው ያሉትን ባዕዳን አማልክት አስወገዱ፤ እግዚአብሔርንም አመለኩ፤ እግዚአብሔርም እስራኤል ስትጐሳቈል ዝም ብሎ ማየት አልቻለም።

መሳፍንት 10:6-16 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ በኣሊምንና አስታሮትን የሶርያንም አማልክት፥ የሲዶናንም አማልክት፥ የሞዓብንም አማልክት፥ የአሞንንም ልጆች አማልክት፥ የፍልስጥኤማውያንንም አማልክት አመለኩ፥ እግዚአብሔርንም ተዉ፥ አላመለኩትምም። የእግዚአብሔርም ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፥ በፍልስጥኤማውያንና በአሞን ልጆች እጅ አሳልፎ ሰጣቸው። በዚያም ዓመት የእስራኤልን ልጆች ሥቃይ አበዙባቸው፥ በዮርዳኖስ ማዶ በአሞራውያን አገር በገለዓድ ውስጥ ያሉትን የእስራኤልን ልጆች ሁሉ አሥራ ስምንት ዓመት ተጋፉአቸው። የአሞንም ልጆች ከይሁዳ ከብንያምና ከኤፍሬም ቤት ጋር ደግሞ ሊዋጋ ዮርዳኖስን ተሻገሩ፥ እስራኤልም እጅግ ተጨነቁ። የእስራኤልም ልጆች፦ አምላካችንን ትተን በኣሊምን አምልከናልና አንተን በድለናል ብለው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ። እግዚአብሔርም የእስራኤልን ልጆች አላቸው፦ ግብፃውያን፥ አሞራውያንም፥ የአሞንም ልጆች፥ ፍልስጥኤማውያንም፥ ሲዶናውያንም፥ አማሌቃውያንም፥ ማዖናውያንም አላስጨነቋችሁምን? ወደ እኔም ጮኻችሁ፥ እኔም ከእጃቸው አዳንኋችሁ። እናንተ ግን ተዋችሁኝ ሌሎችንም አማልክት አመለካችሁ፥ ስለዚህም ደግሞ አላድናችሁም። ሄዳችሁ የመረጣችኋቸውን አማልክት ጥሩ፥ እነርሱም በመከራችሁ ጊዜ ያድኑአችሁ። የእስራኤልም ልጆች እግዚአብሔርን፦ እኛ ኃጢአትን ሠርተናል፥ አንተ ደስ የሚያሰኝህን አድርግብን፥ ዛሬ ግን፥ እባክህ፥ አድነን አሉት። ሌሎችንም አማልክት ከመካከላቸው አስወገዱ፥ እግዚአብሔርንም አመለኩ፥ ነፍሱም ስለ እስራኤል ጉስቁልና አዘነች።

መሳፍንት 10:6-16 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እስራኤላውያን ባዓልና ዐስታሮት የተባሉትን ባዕዳን አማልክት እንዲሁም የሶርያን፥ የሲዶናን፥ የሞአብን፥ የዐሞንንና የፍልስጥኤምን አማልክት በማምለክ እንደገና እግዚአብሔርን በደሉ፤ እርሱንም ማምለክ ተዉ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር በእስራኤላውያን ላይ ተቈጣ፤ ለፍልስጥኤማውያንና ለዐሞናውያን አሳልፎ ሰጣቸው። አሞናውያንና ፍልስጥኤማውያንም ከዮርዳኖስ ማዶ በአሞራውያን ምድር በገለዓድ ውስጥ የሚኖሩትን እስራኤላውያንን ለዐሥራ ስምንት ዓመት አስጨንቀው ገዙአቸው። ዐሞናውያን የይሁዳን፥ የብንያምንና የኤፍሬምን ነገዶች ለመውጋት ዮርዳኖስን ተሻገሩ፤ እስራኤላውያንም እጅግ ተጨነቁ። ከዚህ በኋላ እስራኤላውያን “አንተን አምላካችንን ትተን በዓል ተብለው የሚጠሩትን ባዕዳን አማልክት በመከተላችን በአንተ ላይ በደል ሠርተናል” በማለት ወደ እግዚአብሔር ጮኹ። እግዚአብሔር እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ግብጻውያን፥ አሞራውያን፥ ዐሞናውያን፥ ፍልስጥኤማውያን፥ ሲዶናውያን፥ ዐማሌቃውያንና ማዖናውያን ከዚህ በፊት ጨቊነው በገዙአችሁ ጊዜ ወደ እኔ ጮኻችሁ ነበር፤ ታዲያ እኔስ ከእነርሱ ጭቈና በመታደግ አድኛችሁ አልነበረምን? እናንተ ግን እስከ አሁን ድረስ እኔን ትታችሁ ለባዕዳን አማልክት ሰገዳችሁ፤ ስለዚህ እኔ እናንተን ዳግመኛ አልታደጋችሁም፤ ሂዱ፤ ወደ መረጣችኋቸው ባዕዳን አማልክትም ጩኹ፤ መከራ በሚደርስባችሁ ጊዜም እስቲ እነርሱ ራሳቸው ያድኑአችሁ።” የእስራኤል ሕዝብ ግን እግዚአብሔርን “በእርግጥ በድለናል፤ አንተ በእኛ ላይ የፈለግኸውን አድርግብን፤ ብቻ እባክህ የዛሬን አድነን” አሉት። ባዕዳን አማልክታቸውንም አስወግደው፥ እግዚአብሔርን አመለኩ፤ እግዚአብሔርም ስለ እስራኤል መከራ እጅግ አዘነ።

መሳፍንት 10:6-16 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

እስራኤላውያን እንደገና በጌታ ላይ ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ በኣልንና አስታሮትን እንዲሁም የሶሪያን፥ የሲዶናን፥ የሞዓብን፥ የአሞንንና የፍልስጥኤማውያንን አማልክት አመለኩ፤ እስራኤላውያን ጌታን ስለተዉና ስላላገለገሉት፥ የጌታ ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፤ በፍልስጤማውያንና በአሞናውያን እጅም አሳልፎ ሰጣቸው፤ በዚያም ዓመት የእስራኤልን ልጆች ሥቃይ አበዙባቸው፥ በዮርዳኖስ ማዶ በአሞራውያን አገር በገለዓድ ውስጥ ያሉትን የእስራኤልን ልጆች ሁሉ ዐሥራ ስምንት ዓመት ተጋፉአቸው። የአሞንም ልጆች ከይሁዳ ከብንያምና ከኤፍሬም ቤት ጋር ደግሞ ሊዋጋ ዮርዳኖስን ተሻገሩ፥ እስራኤልም እጅግ ተጨነቁ። “ከዚያም እስራኤላውያን አንተን አምላካችንን በመተው የበኣልን አማልክት በማምለካችን አንተን በድለናል” ብለው ወደ ጌታ ጮኹ። ጌታም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “ግብፃውያን፥ አሞራውያን፥ አሞናውያን፥ ፍልስጥኤማውያን፥ ሲዶናውያን፥ አማሌቃውያንና ማዖናውያን አሠቃዩአችሁ፤ እናንተም እንድረዳችሁ ወደ እኔ ጮኻችሁ፤ ታዲያ እኔ ከእጃቸው አላዳንኋችሁምን? እናንተ ግን እኔን ትታችሁ ሌሎች አማልክትን አመለካችሁ፤ ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲያ አላድናችሁም፤ ሂዱና ወደ መረጣችኋቸው አማልክት ጩኹ፤ መከራ በሚያገኛችሁ ጊዜ እስቲ ያድኗችሁ” እስራኤላውያንም ጌታን፥ “ኃጢአት ሠርተናል፤ መልካም መስሎ የታየህን አድርግብን፤ እባክህን የዛሬን ብቻ አድነን” አሉት። ከዚያም በመካከላቸው ያሉትን ባዕዳን አማልክት አስወገዱ፤ ጌታንም አመለኩ፤ እርሱም የእስራኤልን መከራ ሊታገሠው የማይቻለው ሆነ።