የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኢሳይያስ 42:1-7

ኢሳይያስ 42:1-7 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እነሆ፥ ደግፌ የያ​ዝ​ሁት ባሪ​ያዬ ያዕ​ቆብ፤ ነፍሴ የተ​ቀ​በ​ለ​ችው ምርጤ እስ​ራ​ኤ​ልም፤ በእ​ርሱ ላይ መን​ፈ​ሴን አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ እር​ሱም ለአ​ሕ​ዛብ ፍር​ድን ያመ​ጣል። አይ​ጮ​ኽም፤ ቃሉ​ንም አያ​ነ​ሣም፤ ድም​ፁ​ንም በሜዳ አያ​ሰ​ማም። የተ​ቀ​ጠ​ቀጠ ሸን​በ​ቆን አይ​ሰ​ብ​ርም፤ የሚ​ጤ​ስ​ንም ክር አያ​ጠ​ፋም፤ ነገር ግን በእ​ው​ነት ፍር​ድን ያመ​ጣል። በም​ድ​ርም ፍር​ድን እስ​ኪ​ያ​ደ​ርግ ድረስ ያበ​ራል እንጂ አይ​ጠ​ፋም፤ አሕ​ዛ​ብም በስሙ ይታ​መ​ናሉ። ሰማ​ይን የፈ​ጠረ፥ የዘ​ረ​ጋ​ውም፥ ምድ​ር​ንና በው​ስ​ጥዋ ያለ​ውን ሁሉ ያጸና፥ በእ​ር​ስዋ ላይ ለሚ​ኖሩ ሕዝብ እስ​ት​ን​ፋ​ስን፥ ለሚ​ሄ​ዱ​ባ​ትም መን​ፈ​ስን የሚ​ሰጥ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ “እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ በጽ​ድቅ ጠር​ቼ​ሃ​ለሁ፤ በእ​ጄም እይ​ዝ​ሃ​ለሁ፤ አበ​ረ​ታ​ሃ​ለ​ሁም፤ ለልጅ ልጅ ቃል ኪዳን፥ ለአ​ሕ​ዛ​ብም ብር​ሃን አድ​ርጌ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ። የዕ​ው​ራ​ን​ንም ዐይን ትከ​ፍት ዘንድ፥ የተ​ጋ​ዙ​ት​ንም ከግ​ዞት ቤት፥ በጨ​ለ​ማም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ከወ​ህኒ ቤት ታወጣ ዘንድ።

ኢሳይያስ 42:1-7 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔ የምደግፈው የመረጥኩትና በእርሱም ደስ የሚለኝ አገልጋዬ ይህ ነው፤ መንፈሴ በእርሱ እንዲያድርበት አደርጋለሁ፤ እርሱ ለሕዝቦች ሁሉ ትክክለኛ ፍርድን ያመጣል። ጮኾ አይናገርም፤ ድምጡንም በየአደባባዩ እንዲሰማ አያደርግም። የተቀጠቀጠ ሸምበቆን እንኳ አይሰብርም፤ ሊጠፋ የተቃረበውንም መብራት አያጠፋም፤ በታማኝነት ፍትሕን ያስገኛል። በምድር ላይ ፍትሕን እስኪመሠርት ድረስ እርሱ አይታክትም፤ ተስፋም አይቈርጥም፤ በሩቅ ያሉ ሕዝቦችም የእርሱን ትምህርት ለመስማት ይናፍቃሉ።” ሰማይን የፈጠረና ከዳር እስከ ዳር የዘረጋው፥ ምድርንና በውስጥዋ የሚኖሩትን ሁሉ የሠራ፥ ሕይወትንና እስትንፋስንም የሰጣቸው፥ እግዚአብሔር አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እኔ እግዚአብሔር በጽድቅ ጠርቼሃለሁ፤ እጅህን ይዤ ጠብቄሃለሁ፤ ለወገኖቼ እንደ ቃል ኪዳን፥ ለአሕዛብ እንደ ብርሃን አድርጌ ሰጥቼሃለሁ። ስለዚህ የዕውሮችን ዐይን ታበራለህ፤ በጨለማው ጒድጓድ እስር ቤት ውስጥ ያሉትን እስረኞችን ታወጣለህ።