የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኢሳይያስ 40:1-8

ኢሳይያስ 40:1-8 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

አጽ​ናኑ፤ ሕዝ​ቤን አጽ​ናኑ፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ካህ​ናት ሆይ፥ ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ልቧ የሚ​ገባ ነገ​ርን ተና​ገሩ፤ ውር​ደቷ እንደ ተፈ​ጸመ፥ ኀጢ​አ​ቷም እንደ ተሰ​ረየ፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ ስለ ኀጢ​አቷ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀ​በ​ለች አጽ​ና​ኑ​አት። የዐ​ዋጅ ነጋሪ ቃል በም​ድረ በዳ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ ጥረጉ፤ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም ጎዳና በበ​ረሃ አስ​ተ​ካ​ክሉ። ሸለ​ቆው ሁሉ ይሙላ፤ ተራ​ራ​ውና ኮረ​ብ​ታ​ውም ሁሉ ዝቅ ይበል፤ ጠማ​ማ​ውም ይቅና፤ ሰር​ጓ​ጕ​ጡም ሜዳ ይሁን፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ይገ​ለጥ፤ ሥጋ ለባ​ሹም ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትድ​ግና ይይ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።” “ጩኽ” የሚል ሰው ቃል፤ “ምን ብዬ ልጩኽ?” አልሁ። “ሥጋ ለባሽ ሁሉ ሣር ነው፤ የሰ​ውም ክብሩ ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እስ​ት​ን​ፋስ ይነ​ፍ​ስ​በ​ታ​ልና ሣሩ ይደ​ር​ቃል፤ አበ​ባ​ውም ይረ​ግ​ፋል፤ በእ​ው​ነት ሕዝቡ ሣር ነው። ሣሩ ይደ​ር​ቃል፤ አበ​ባ​ውም ይረ​ግ​ፋል፤ የአ​ም​ላ​ካ​ችን ቃል ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ጸንቶ ይኖ​ራል።”

ኢሳይያስ 40:1-8 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

አጽናኑ፤ ሕዝቤን አጽናኑ፤ ይላል አምላካችሁ። ለኢየሩሳሌም አለዝባችሁ ንገሯት፤ ዐውጁላትም፤ በባርነት ያገለገለችበት ዘመን አብቅቷል፤ የኀጢአቷም ዋጋ ተከፍሏል፤ ስለ ኀጢአቷ ሁሉ ከእግዚአብሔር እጅ ሁለት ዕጥፍ ተቀብላለች። የዐዋጅ ነጋሪ ድምፅ እንዲህ ይላል፤ “የእግዚአብሔርን መንገድ፣ በምድረ በዳ አዘጋጁ፤ ለአምላካችን አውራ ጐዳና፣ በበረሓ አስተካክሉ። ሸለቆው ሁሉ ከፍ ይላል፤ ተራራውና ኰረብታው ሁሉ ዝቅ ይላል፤ ወጣ ገባው ምድር ይስተካከላል፤ ሰርጓጕጡም ሜዳ ይሆናል። የእግዚአብሔርም ክብር ይገለጣል፤ ሰው ሁሉ በአንድነት ያየዋል፤ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሯልና።” ድምፅም፣ “ጩኽ” አለኝ፤ እኔም፣ “ምን ብዬ ልጩኽ?” አልሁ። “ሰው ሁሉ እንደ ሣር ነው፤ ክብሩም ሁሉ እንደ ሜዳ አበባ ነው። ሣሩ ይደርቃል፤ አበባውም ይረግፋል፤ የእግዚአብሔር እስትንፋስ ነፍሶበታልና፤ ሕዝቡ በርግጥ ሣር ነው። ሣሩ ይደርቃል፤ አበባውም ይረግፋል፤ የአምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።”

ኢሳይያስ 40:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

አጽናኑ፥ ሕዝቤን አጽናኑ ይላል አምላካችሁ። ለኢየሩሳሌም ልብ ተናገሩ፥ የተቀጠረችበት ወራት እንደ ተፈጸመ፥ ኃጢአትዋም እንደ ተሰረየ፥ ከእግዚአብሔርም እጅ ስለ ኃጢአትዋ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀበለች ወደ እርስዋ ጩኹ። የአዋጅ ነጋሪ ቃል፦ የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ ጥረጉ፥ ለአምላካችንም ጎዳና በበረሀ አስተካክሉ። ሸለቆው ሁሉ ከፍ ይላል፥ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይላል፥ ጠማማውም ይቃናል፥ ስርጓጕጡም ሜዳ ይሆናል፥ የእግዚአብሔርም ክብር ይገለጣል፥ ሥጋ ለባሹም ሁሉ በአንድነት ያየዋል፥ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና። ጩኽ የሚል ሰው ቃል፥ ምን ብዬ ልጩኽ? አልሁ። ሥጋ ለባሽ ሁሉ ሣር ነው፥ ክብሩም ሁሉ እንደ ምድረ በዳ አበባ ነው። የእግዚአብሔር እስትንፋስ ይነፍስበታልና ሣሩ ይደርቃል አበባውም ይረግፋል፥ በእውነት ሕዝቡ ሣር ነው። ሣሩ ይደርቃል አበባውም ይረግፋል፥ ያምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች።

ኢሳይያስ 40:1-8 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤን አጽናኑ! ሕዝቤን አጽናኑ! የባርነት ጊዜዋ እንዳለቀ፥ ለፈጸመችው ኃጢአት ሁሉ ከእግዚአብሔር ዘንድ እጥፍ ቅጣት እንደ ተቀበለችና ኃጢአትዋም ይቅር እንደ ተባለላት ለኢየሩሳሌም በለሰለሰ አነጋገር ንገሯት።” እንዲህ የሚል ድምፅ ይሰማል፦ “በምድረ በዳ የእግዚአብሔርን መንገድ አዘጋጁ! በበረሓም ለአምላካችን ጥርጊያ ጐዳና አብጁ! ጐድጓዳውና ሸለቆው ይሙላ፤ ተራራውና ኰረብታው ሁሉ ዝቅ ብሎ ይደልደል፤ ኮረብታውና ወጣ ገባ የሆነው ምድር ሁሉ ይስተካከል። በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር ክብር ይገለጣል፤ እግዚአብሔር ይህን የተናገረ ስለ ሆነ ሰዎች ሁሉ ይህን በአንድነት ሆነው ያዩታል።” አንድ ድምፅ “የዐዋጅ ቃል ተናገር!” እያለ ይጮኻል። እኔም “ምን ብዬ ላውጅ!” ስል ጠየቅሁ። ያም ድምፅ “እንዲህ ብለህ ዐውጅ” አለኝ፦ “ሰው ሁሉ እንደ ሣር ነው፤ ክብሩም ሁሉ እንደ ሜዳ አበባ ነው፤ የእግዚአብሔር ነፋስ በሚነፍስበት ጊዜ፥ ሣሩ እንደሚደርቅና አበባውም እንደሚረግፍ ሰውም እንዲሁ ረጋፊ ነው። በእርግጥ ሣር ይደርቃል፤ አበባም ይረግፋል፤ የአምላካችን ቃል ግን ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል።”