ሆሴዕ 3:1-2
ሆሴዕ 3:1-2 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “እርሷ በሌላ ሰው የምትወደድ አመንዝራ ብትሆንም፣ አሁንም ሂድና ሚስትህን ውደዳት፤ ወደ ሌሎች አማልክት ዘወር ቢሉና ለእነርሱም የተቀደሰውን የዘቢብ ጥፍጥፍ ቢወድዱም፣ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን እንደ ወደዳቸው አንተም እርሷን ውደዳት።” ስለዚህ በዐሥራ አምስት ሰቅል ጥሬ ብርና በአንድ ቆሮስ ተኩል መስፈሪያ ገብስ ገዛኋት።
Share
ሆሴዕ 3 ያንብቡሆሴዕ 3:1-2 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እግዚአብሔርም፥ “የእስራኤል ልጆች ወደ ሌሎች አማልክት ቢመለሱና የዘቢብ ጥፍጥፍን ቢወድዱ እንኳን፥ እግዚአብሔር እንደሚወድዳቸው አንተም ክፋትና ዝሙት ያለባትን ሴት ውደድ” አለኝ። እኔም በዐሥራ አምስት ብርና በአንድ ቆሮስ መስፈሪያ ተኩል ገብስና በአንድ ፊቀን ወይን ተወዳጀኋት።
Share
ሆሴዕ 3 ያንብቡሆሴዕ 3:1-2 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እግዚአብሔርም፦ የእስራኤል ልጆች ወደ ሌሎች አማልክት ቢመለሱና የዘቢብ ጥፍጥፍን ቢወድዱ እንኳ፥ እግዚአብሔር እንደሚወድዳቸው አንተም ውሽማዋን የምትወድደውን አመንዝራይትን ሴት ውደድ አለኝ። እኔም በአሥራ አምስት ብርና በአንድ ቆሮስ መስፈሪያ ተኩል ገብስ ገዛኋት።
Share
ሆሴዕ 3 ያንብቡ