የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዕብራውያን 7:1-10

ዕብራውያን 7:1-10 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

የሳ​ሌም ንጉሥ፥ የል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ካህን የሆነ፥ ይህ መልከ ጼዴቅ፥ አብ​ር​ሃም ነገ​ሥ​ታ​ትን ድል ነሥቶ በተ​መ​ለሰ ጊዜ ከእ​ርሱ ጋር ተገ​ና​ኝቶ ባረ​ከው። አብ​ር​ሃ​ምም ከገ​ን​ዘቡ ሁሉ ከዐ​ሥር አንድ ሰጠው፤ መጀ​መ​ሪያ የስሙ ትር​ጓሜ የጽ​ድቅ ንጉሥ ነበር፤ በኋ​ላም የሳ​ሌም ንጉሥ ተባለ፤ የሰ​ላም ንጉሥ ማለት ነው። አባት የለ​ውም፤ እና​ትም የለ​ች​ውም፤ ትው​ል​ዱም አይ​ታ​ወ​ቅም፤ ለዘ​መኑ መጀ​መ​ሪያ፥ ለሕ​ይ​ወ​ቱም መጨ​ረሻ የለ​ውም፤ ክህ​ነቱ የወ​ልደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምሳሌ ሆኖ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል። የአ​ባ​ቶች አለቃ አብ​ር​ሃም ከም​ር​ኮው ሁሉ የሚ​ሻ​ለ​ውን ዐሥ​ራት የሰ​ጠ​ውን የዚ​ህን ካህን ክብር ታያ​ላ​ች​ሁን? ከሌዊ ልጆ​ችም፥ ክህ​ነ​ትን የሚ​ቀ​በ​ሉት ከሕ​ዝቡ ማለት ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው፥ እነ​ርሱ ምንም ከአ​ብ​ር​ሃም ወገብ ቢወጡ ከእ​ነ​ርሱ ዐሥ​ራ​ትን በሕግ እን​ዲ​ያ​ስ​ወጡ ትእ​ዛዝ አላ​ቸው። ወገ​ና​ቸው ላይ​ደለ ለእ​ርሱ ግን አብ​ር​ሃም ዐሥ​ራ​ትን ሰጠው፤ እር​ሱም ተስፋ ያለው አብ​ር​ሃ​ምን ባረ​ከው። ነገር ግን ታላቁ ታና​ሹን እን​ደ​ሚ​ባ​ር​ከው ያለ ጥር​ጥር ይታ​ወ​ቃል። በዚ​ህስ የሚ​ሞት ሰው ዐሥ​ራ​ትን ይቀ​በ​ላል፤ በወ​ዲ​ያው ግን ሕያው እንደ ሆነ መጽ​ሐፍ የሚ​መ​ሰ​ክ​ር​ለት እርሱ ይቀ​በ​ላል። እንደ ተነ​ገ​ረም ዐሥ​ራ​ትን የሚ​ቀ​በል ሌዊ ስን​ኳን በአ​ብ​ር​ሃም በኩል ዐሥ​ራ​ትን ሰጠ። መልከ ጼዴቅ በተ​ገ​ና​ኘው ጊዜ ገና በአ​ባቱ በአ​ብ​ር​ሃም ወገብ ነበ​ርና።

ዕብራውያን 7:1-10 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ይህ መልከጼዴቅ የሳሌም ንጉሥና የልዑል እግዚአብሔር ካህን ነበር፤ እርሱም አብርሃም ነገሥታትን ድል አድርጎ ሲመለስ አግኝቶት ባረከው፤ አብርሃምም ከሁሉ ነገር ዐሥራት አውጥቶ ሰጠው። በመጀመሪያ ስሙ “የጽድቅ ንጉሥ” ማለት ነው፤ ኋላም ደግሞ “የሳሌም ንጉሥ” ማለትም “የሰላም ንጉሥ ማለት” ነው። አባትና እናት ወይም የትውልድ ሐረግ የለውም፤ ለዘመኑ መጀመሪያ፣ ለሕይወቱም ፍጻሜ የለውም፤ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ልጅ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል። እስቲ እርሱ የቱን ያህል ታላቅ እንደ ሆነ አስቡ፤ ርእሰ አበው የሆነው አብርሃም እንኳ ካገኘው ምርኮ ዐሥራት አውጥቶ ሰጠው። ክህነት የተሰጣቸው የሌዊ ልጆች ምንም እንኳ ወንድሞቻቸው የአብርሃም ዘሮች ቢሆኑም፣ ከሕዝቡ ማለት ከገዛ ወንድሞቻቸው ዐሥራት እንዲቀበሉ ሕጉ ያዝዛል። ይህ ግን ትውልዱ ከሌዊ ወገን አይደለም፤ ይሁን እንጂ ከአብርሃም ዐሥራት ተቀበለ፤ የተስፋ ቃል የተቀበለውንም ባረከው። ትንሹ በትልቁ እንደሚባረክ ጥርጥር የለውም። በአንድ በኩል ዐሥራት የሚቀበሉት ሟች ሰዎች ናቸው፤ በሌላ በኩል ግን ሕያው ሆኖ እንደሚኖር የተመሰከረለት ይቀበላል። እንዲያውም ዐሥራት የሚቀበለው ሌዊ፣ ራሱ በአብርሃም በኩል ዐሥራት ከፍሏል ማለት ይቻላል፤ ምክንያቱም መልከጼዴቅ አብርሃምን ባገኘው ጊዜ፣ ሌዊ ገና በአባቱ በአብርሃም አብራክ ነበር።

ዕብራውያን 7:1-10 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

የሳሌም ንጉሥና የልዑል እግዚአብሔር ካህን የሆነ ይህ መልከ ጼዴቅ አብርሃም ነገሥታትን ገድሎ ሲመለስ ከእርሱ ጋር ተገናኝቶ ባረከው፤ ለእርሱም ደግሞ አብርሃም ከሁሉ አስራትን አካፈለው። የስሙም ትርጓሜ በመጀመሪያ የጽድቅ ንጉሥ ነው፥ ኋላም ደግሞ የሳሌም ንጉሥ ማለት የሰላም ንጉሥ ነው። አባትና እናት የትውልድም ቍጥር የሉትም፥ ለዘመኑም ጥንት ለህይወቱም ፍጻሜ የለውም፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ልጅ ተመስሎ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል። የአባቶች አለቃ አብርሃም ከዘረፋው የሚሻለውን አስራት የሰጠው ይህ ሰው እንዴት ትልቅ እንደ ነበረ እስኪ ተመልከቱ። ከሌዊ ልጆችም ክህነትን የሚቀበሉት ከህዝቡ ማለት ከወንድሞቻቸው፥ እነርሱ ምንም ከአብርሃም ወገብ ቢወጡ፥ ከእነርሱ አሥራትን በሕግ እንዲያስወጡ ትእዛዝ አላቸው፤ ትውልዱ ከእነርሱ የማይቍኦጠረው ግን ከአብርሃም አሥራትን አውጥቶአል፥ የተስፋ ቃል የነበረውንም ባርኮአል። ትንሹንም በታላቁ እንዲባርክ ክርክር የሌለበት ነገር ነው። በዚህስ የሚሞቱ ሰዎች አሥራትን ያስወጣሉ፥ በዚያ ግን የሚያስወጣ በሕይወት እንዲኖር የተመሰከረለት እርሱ ነው። ይህንም ለማለት ሲፈቀድ፥ አሥራትን የሚያስወጣ ሌዊ እንኳ በአብርሃም እጅ አሥራትን ሰጥቶአል፤ መልከ ጼዴቅ በተገናኘው ጊዜ ገና በአባቱ ወገብ ነበረና።

ዕብራውያን 7:1-10 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

መልከጼዴቅ የሳሌም ንጉሥና የልዑል እግዚአብሔር ካህን ነበር፤ ይህ መልከጼዴቅ አብርሃም ነገሥታትን አሸንፎ ሲመለስ በመንገድ ተገናኝቶ ባረከው። አብርሃምም ከያዘው ነገር ሁሉ ዐሥራት አውጥቶ ሰጠው፤ የመልከ ጼዴቅ የስሙ ትርጓሜ አንደኛው “የጽድቅ ንጉሥ” ሌላው “የሳሌም ንጉሥ” ወይም “የሰላም ንጉሥ” ማለት ነው። መልከጼዴቅ በጽሑፍ የታወቀ አባትና እናት ወይም የትውልድ ሐረግ የለውም፤ ለዘመኑ መጀመሪያ፥ ለሕይወቱም መጨረሻ የለውም፤ ይህ መልከጼዴቅ እንደ እግዚአብሔር ልጅ ምሳሌ በመሆን ለዘለዓለም ካህን ሆኖ ይኖራል። ይህ ሰው እንዴት ታላቅ እንደ ሆነ ተመልከቱ፤ የነገድ አባት የሆነው አብርሃም እንኳ በምርኮ ካገኘው ነገር ዐሥራት አውጥቶ ሰጠው። እነዚያ በክህነት ሥራ ላይ የሚመደቡት የሌዊ ዘሮች ከሕዝቡ ከአብርሃም ዘር ማለትም ከወንድሞቻቸው ዐሥራት እንዲቀበሉ በሕግ ታዞላቸዋል፤ ያ መልከጼዴቅ የሌዋውያን ዘር ባይሆንም እንኳ ከአብርሃም ዐሥራትን ተቀበለ፤ የተስፋ ቃል የተሰጠውን አብርሃምንም ባረከው። ታናሹ ከታላቁ ቡራኬን እንደሚቀበል ጥርጥር የለውም። በአንድ በኩል ዐሥራት የሚቀበሉት ሟች የሆኑት ናቸው፤ በሌላ በኩል ግን ዐሥራት የሚቀበለው ሕያው ሆኖ እንደሚኖር የተመሰከረለት መልከጼዴቅ ነው። እንግዲህ መልከጼዴቅ አብርሃምን በተገናኘው ጊዜ ሌዊ ከአባቱ ከአብርሃም ገና ስላልተወለደ ዐሥራትን መቀበል የሚገባው ሌዊ ራሱ በአብርሃም አማካይነት ዐሥራትን ከፍሎአል ማለት ነው።

ዕብራውያን 7:1-10 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

የሳሌም ንጉሥ፥ የልዑል እግዚአብሔር ካህን የሆነ፥ ይህ መልከጼዴቅ፥ አብርሃም ነገሥታትን ገድሎ ሲመለስ አግኝቶት ባረከው፤ ለእርሱም አብርሃም ከሁሉ ከዐሥር አንድ ሰጠው፥፥ የስሙ ትርጓሜ በመጀመሪያ፥ የጽድቅ ንጉሥ ነው፤ ከዚያ ደግሞ፥ የሳሌም ንጉሥ ማለት የሰላም ንጉሥ ነው። አባትና እናት የትውልድም ሐረግም የሉትም፤ ለዘመኑም መጀመሪያ ለሕይወቱም ፍጻሜ የለውም፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ልጅ ተመስሎ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል። ይህ ሰው እንዴት ታላቅ እንደሆነ እስቲ ተመልከቱ! የአባቶች አለቃ የሆነው አብርሃም እንኳ በምርኮ ካገኘው ነገር አሥራት አውጥቶ ሰጠው። ከሌዊ ልጆችም፥ ክህነትን የሚቀበሉት ከሕዝቡ ማለት ከወንድሞቻቸው፥ እነዚያ ክህነትን የሚቀበሉት የሌዊ ልጆች ከሕዝቡ ማለትም ከወንድሞቻቸው፥ እነርሱ ምንም ከአብርሃም ወገብ ቢወጡ፥ አሥራትን እንዲቀበሉ በሕግ ታዞላቸዋል። ይህ ሰው ምንም ትውልዱ ከእነርሱ ባይቆጠርም እንኳ ከአብርሃም አሥራትን ተቀብሏል፤ የተስፋ ቃል የተሰጠውን አብርሃምንም ባርኮአል። ታናሹ በታላቁ እንደሚባረክ ምንም ጥርጥር የሌለውም። በዚህ በኩል የሚሞቱ ሰዎች አሥራትን ይቀበላሉ፤ በዚያ በኩል የሚቀበለው ሕያው ሆኖ እንደሚኖር የተመሰከረለት እርሱ ነው። በመሆኑም አሥራትን የሚቀበለው ሌዊ ራሱ እንኳን፥ በአብርሃም በኩል አሥራትን ሰጥቶአል፥ ማለት ያስችላል፤ ምክንያቱም መልከጼዴቅ በተገናኘው ጊዜ ገና በአባቱ ወገብ ነበር።