የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዕብራውያን 11:8-17

ዕብራውያን 11:8-17 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

አብ​ር​ሃም በተ​ጠራ ጊዜ ርስት አድ​ርጎ ይወ​ር​ሰው ዘንድ ወዳ​ለው ሀገር ለመ​ሄድ በእ​ም​ነት ታዘዘ፤ ወዴት እን​ደ​ሚ​ደ​ር​ስም ሳያ​ውቅ ሄደ። በእ​ም​ነ​ትም ከሀ​ገሩ ወጥቶ ተስፋ በሰ​ጠው ሀገር እንደ ስደ​ተኛ በድ​ን​ኳን፥ ተስ​ፋ​ውን ከሚ​ወ​ር​ሱ​አት ከይ​ስ​ሐ​ቅና ከያ​ዕ​ቆብ ጋር ኖረ። መሠ​ረት ያላ​ትን ሠሪ​ዋና ፈጣ​ሪዋ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሆ​ነ​ላ​ትን ከተማ ደጅ ይጠኑ ነበ​ርና። ራስዋ ሳራም መካን ሳለች ባረ​ጀ​ች​በት ወራት ዘር ታስ​ገኝ ዘንድ በእ​ም​ነት ኀይ​ልን አገ​ኘች፤ ተስፋ የሰ​ጣት የታ​መነ እንደ ሆነ አም​ና​ለ​ችና። ስለ​ዚ​ህም ደግሞ በብ​ዛ​ታ​ቸው እንደ ሰማይ ኮከብ፥ እን​ደ​ማ​ይ​ቈ​ጠ​ርም በባ​ሕር ዳር እን​ዳለ አሸዋ የነ​በ​ሩት የሞ​ተን ሰው እንኳ ከመ​ሰ​ለው ከአ​ንዱ ተወ​ለዱ። እነ​ዚህ ሁሉ አም​ነው ሞቱ፤ ተስ​ፋ​ቸ​ው​ንም አላ​ገ​ኙም፤ ነገር ግን ከሩቅ አይ​ተው እጅ ነሱ​ኣት፤ በም​ድ​ሪ​ቱም ላይ እነ​ርሱ እን​ግ​ዶ​ችና መጻ​ተ​ኞች እንደ ሆኑ ዐወቁ። እን​ዲህ የሚሉ ግን ሀገ​ራ​ቸ​ውን እን​ደ​ሚሹ ያሳ​ያሉ። ከእ​ር​ስዋ የወ​ጡ​ባ​ትን ሀገር ቢሹ ኖሮስ፥ ወደ እር​ስዋ ሊመ​ለሱ በተ​ቻ​ላ​ቸው ነበር። አሁን ግን፥ በሰ​ማ​ያት ያለ​ች​ውን የም​ት​በ​ል​ጠ​ውን ሀገር ተስፋ ያደ​ርጉ እንደ ነበር ታወቀ፤ ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ቸው ተብሎ ይጠራ ዘንድ በእ​ነ​ርሱ አያ​ፍ​ርም፤ ተስፋ ያደ​ረ​ጉ​አ​ትን ሀገር አዘ​ጋ​ጅ​ቶ​ላ​ቸ​ዋ​ልና። አብ​ር​ሃ​ምም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ተ​ነው ጊዜ ልጁን ይስ​ሐ​ቅን ይሠ​ዋው ዘንድ በእ​ም​ነት ወሰ​ደው።

ዕብራውያን 11:8-17 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

አብርሃም ርስት አድርጎ ወደሚቀበለው ስፍራ እንዲሄድ በተጠራ ጊዜ በእምነት ታዘዘ፤ ወዴት እንደሚሄድ ባያውቅም፣ እሺ ብሎ ሄደ። በባዕድ አገር እንዳለ መጻተኛ በተስፋዪቱ ምድር በእምነት ተቀመጠ፤ የተስፋውን ቃል አብረውት እንደሚወርሱት እንደ ይስሐቅና እንደ ያዕቆብ በድንኳን ኖረ፤ ምክንያቱም መሠረት ያላትን፣ እግዚአብሔር የሠራትንና የፈጠራትን ከተማ ይጠባበቅ ነበር። አብርሃም ምንም እንኳ ዕድሜው ቢገፋም፣ ሣራም ራሷ መካን ብትሆንም፣ ተስፋን የሰጠውን ታማኝ አድርጎ ስለ ቈጠረ በእምነት የልጅ አባት ለመሆን በቃ። ስለዚህ እንደ ሞተ ሰው ከሚቈጠር ከዚህ ከአንድ ሰው፣ እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛና እንደ ባሕር ዳር አሸዋ ተቈጥሮ የማያልቅ ዘር ተገኘ። እነዚህ ሁሉ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል ሳያገኙ እምነታቸውን እንደ ጠበቁ ሞቱ፤ ሆኖም ከሩቅ አይተው ሰላም አሉት፤ በዚህ ምድር ሲኖሩ መጻተኞችና እንግዶች መሆናቸውን ተገንዝበው ነበርና። እንደዚህ የሚሉት ሰዎች የራሳቸው የሆነውን አገር እንደሚጠባበቁ ያሳያሉ። ትተውት የወጡትን አገር ቢያስቡ ኖሮ፣ ወደዚያ የመመለስ ዕድል ነበራቸው። አሁን ግን ከዚህ የሚበልጠውን ሰማያዊ አገር ይናፍቃሉ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካቸው ተብሎ ሊጠራ አላፈረም፤ ከተማን አዘጋጅቶላቸዋልና። አብርሃም እግዚአብሔር በፈተነው ጊዜ፣ ይስሐቅን መሥዋዕት አድርጎ በእምነት አቀረበ፤ የተስፋን ቃል የተቀበለው እርሱ፣ አንድ ልጁን ሊሠዋ ዝግጁ ነበር፤

ዕብራውያን 11:8-18 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

አብርሃም የተባለው ርስት አድርጎ ሊቀበለው ወዳለው ስፍራ ለመውጣት በእምነት ታዘዘ፥ ወዴትም እንደሚሄድ ሳያውቅ ወጣ። ለእንግዶች እንደሚሆን በተስፋ ቃል በተሰጠው አገር በድንኳን ኖሮ፥ ያን የተስፋ ቃል አብረውት ከሚወርሱ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር፥ እንደ መጻተኛ በእምነት ተቀመጠ፤ መሠረት ያላትን፥ እግዚአብሔር የሠራትንና የፈጠራትን ከተማ ይጠብቅ ነበርና። ተስፋ የሰጠው የታመነ እንደ ሆነ ስለ ቍኦጠረች፥ ሣራ ራስዋ ደግሞ ዕድሜዋ እንኳ ካለፈ በኋላ ዘርን ለመፅነስ ኃይልን በእምነት አገኘች። ስለዚህ ደግሞ በብዛታቸው እንደ ሰማይ ኮከብ እንደማይቍኦጠርም በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ የነበሩት የሞተን ሰው እንኳ ከመሰለው ከአንዱ ተወለዱ። እነዚህ ሁሉ አምነው ሞቱ፥ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል አላገኙምና፤ ዳሩ ግን ከሩቅ ሆነው አዩትና ተሳለሙት፥ በምድሪቱም እንግዶችና መጻተኞች እንዲሆኑ ታመኑ። እንዲህ የሚሉት ለእነርሱ የሚሆነውን አገር እንዲፈልጉ ያመለክታሉና። ያን የወጡበትን አገር አስበው ቢሆኑ፥ ሊመለሱ ጊዜ በሆነላቸው ነበር፤ አሁን ግን የሚበልጠውን እርሱም ሰማያዊ አገር ይናፍቃሉ። ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካቸው ተብሎ ሊጠራ በእነርሱ አያፍርም፥ ከተማን አዘጋጅቶላቸዋልና። አብርሃም በተፈተነበት ጊዜ ይስሐቅን በእምነት አቀረበ፥ የተስፋን ቃል የተቀበለው፦ በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃል የተባለለት እርሱም አንድ ልጁን አቀረበ፤

ዕብራውያን 11:8-17 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

አብርሃም ወጥቶ ርስት አድርጎ ወደሚቀበለው ስፍራ እንዲሄድ በተጠራ ጊዜ ምንም እንኳ ወዴት እንደሚሄድ ባያውቅም ለመሄድ የታዘዘው በእምነት ነው። ከእርሱ ጋር የተስፋው ቃል ወራሾች ከሆኑት ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር በተስፋይቱ አገር መጻተኛ ሆኖ በድንኳን የኖረው በእምነት ነው። ይህንንም ያደረገው ጽኑ መሠረት ያላትን፥ እግዚአብሔር ያቀዳትንና የሠራትን ከተማ ይጠባበቅ ስለ ነበር ነው። ሣራም ተስፋ የሰጣት እግዚአብሔር ታማኝ መሆኑን ስላወቀች ምንም እንኳ በዕድሜ በመግፋቷ መውለድ የማትችል ብትሆን የመፅነስን ኀይል ያገኘችው በእምነት ነው። ስለዚህ እንደ ሞተ ሰው ከሚቈጠረው ከአንዱ ከአብርሃም እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛና እንደ ባሕር ዳር አሸዋ የማይቈጠር ዘር ተገኘ። እነዚህ ሁሉ በእምነት እንዳሉ ሞቱ፤ እግዚአብሔር ሊሰጣቸው ቃል የገባላቸውንም ነገር አላገኙም፤ ነገር ግን ከሩቅ አይተው ልክ እንዳገኙት አድርገው በደስታ ተቀበሉት። በምድር ላይ እንግዶችና መጻተኞች መሆናቸውንም ተገነዘቡ። እንዲህ የሚናገሩ ሰዎች የራሳቸው የሚሆነውን አገር እንደሚጠባበቁ በግልጽ ያመለክታሉ። ያንን የወጡበትን አገር አስታውሰውት ቢሆኑ ኖሮ ወደዚያ ለመመለስ በቻሉ ነበር። አሁን ግን የሚበልጠውን፥ በሰማይ ያለውን አገር ይናፍቃሉ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ከተማን ስላዘጋጀላቸው “አምላካችን” ብለው ቢጠሩት አያሳፍረውም። አብርሃም በተፈተነበት ጊዜ ይስሐቅን መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበው በእምነት ነው፤ ያ የተስፋ ቃል የተቀበለው አብርሃም አንድ ልጁን ሊሠዋው ነበር፤

ዕብራውያን 11:8-17 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

አብርሃም ርስት አድርጎ ወደሚቀበለው ስፍራ እንዲሄድ በተጠራ ጊዜ በእምነት ታዘዘ፤ ወዴትም እንደሚሄድም ሳያውቅ ሄደ። ለባዕድ አገር እያለም በተስፋ ቃል በተሰጠው ምድር፥ ያን የተስፋ ቃል አብረውት ወራሾች እንደሆኑት እንደ ይስሐቅና እንደ ያዕቆብ በእምነት በድንኳን ኖረ፤ ምክንያቱም መሠረት ያላትን፥ እግዚአብሔር የሠራትንና የፈጠራትን ከተማ ይጠብቅ ነበር። ሣራም ተስፋ የሰጠው የታመነ እንደሆነ ስለ ቈጠረች፥ ምንም እንኳን መካን ብትሆን፥ ዕድሜዋ እንኳ ካለፈ በኋላ ዘርን ለመፅነስ ኃይልን በእምነት አገኘች። ስለዚህ እንደ ሞተ ሰው ከሚቈጠር ከዚህ ከአንድ ሰው፥ እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛና እንደ ባሕር ዳር አሸዋ ተቈጥሮ የማያልቅ ዘር ተገኘ። እነዚህ ሁሉ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል ሳያገኙ እምነታቸውን እንደ ጠበቁ ሞቱ፤ ሆኖም ከርቀት አይተውት ሰላምታ አቀረቡለት፤ በዚህ ምድር ሲኖሩም እንግዶችና መጻተኞች ለመሆንም ታመኑ። እንደዚህ የሚሉት ሰዎች የራሳቸው የሆነውን አገር እንደሚጠባበቁ ያመለክታሉ። ያን ትተውት የወጡትን አገር አስበው ቢሆን ኖሮ፥ ወደዚያ የመመለስ እድል በነበራቸው ነበር። አሁን ግን የሚበልጠውን ሰማያዊ አገር ይናፍቃሉ። ስለዚህ እግዚአብሔር ከተማን አዘጋጅቶላቸዋልና አምላካቸው ተብሎ ለመጠራት በእነርሱ አያፍርም። አብርሃም በተፈተነ ጊዜ ይስሐቅን በእምነት አቀረበ፤ የተስፋን ቃል የተቀበለው እርሱም አንድ ልጁን ሊሠዋ ዝግጁ ነበር፤