ዕብራውያን 11:1-10

ዕብራውያን 11:1-10 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እም​ነ​ትስ ተስፋ ስለ​ም​ና​ደ​ር​ገው ነገር የም​ታ​ረ​ጋ​ግጥ፥ የማ​ና​የ​ው​ንም ነገር የም​ታ​ስ​ረዳ ናት። በዚ​ህም ለሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎች ተመ​ሰ​ከ​ረ​ላ​ቸው። ዓለም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እንደ ተፈ​ጠረ፥ የሚ​ታ​የ​ውም ነገር ከማ​ይ​ታ​የው እንደ ሆነ በእ​ም​ነት እና​ው​ቃ​ለን። አቤል ከቃ​ኤል ይልቅ የሚ​በ​ልጥ መሥ​ዋ​ዕ​ትን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ም​ነት አቀ​ረበ፤ በዚ​ህም ጻድቅ እንደ ሆነ ተመ​ሰ​ከ​ረ​ለት፤ ምስ​ክ​ሩም መሥ​ዋ​ዕ​ቱን በመ​ቀ​በል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው። በዚ​ህም ከሞተ በኋላ እንኳ ተና​ገረ። ሄኖክ ሞትን እን​ዳ​ያይ በእ​ም​ነት ተወ​ሰደ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ወሰ​ደው አል​ተ​ገ​ኘም፤ ሳይ​ወ​ሰ​ድም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ እንደ አሰ​ኘው ተመ​ስ​ክ​ሮ​ለ​ታል። ያለ እም​ነ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ ማሰ​ኘት አይ​ቻ​ልም፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ርብ ሰው አስ​ቀ​ድሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳለ፥ ለሚ​ሹ​ትም ዋጋ እን​ደ​ሚ​ሰ​ጣ​ቸው ሊያ​ምን ይገ​ባ​ዋል። ኖኅም ስለ​ማ​ይ​ታ​የው ነገር የነ​ገ​ሩ​ትን ባመነ ጊዜ ፈራ፤ ቤተ ሰቡ​ንም ያድን ዘንድ ክፍል ያላት መር​ከ​ብን ሠራ፤ በዚ​ህም ዓለ​ምን አስ​ፈ​ረ​ደ​በት፤ በእ​ም​ነ​ትም የሚ​ገ​ኘ​ውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ። አብ​ር​ሃም በተ​ጠራ ጊዜ ርስት አድ​ርጎ ይወ​ር​ሰው ዘንድ ወዳ​ለው ሀገር ለመ​ሄድ በእ​ም​ነት ታዘዘ፤ ወዴት እን​ደ​ሚ​ደ​ር​ስም ሳያ​ውቅ ሄደ። በእ​ም​ነ​ትም ከሀ​ገሩ ወጥቶ ተስፋ በሰ​ጠው ሀገር እንደ ስደ​ተኛ በድ​ን​ኳን፥ ተስ​ፋ​ውን ከሚ​ወ​ር​ሱ​አት ከይ​ስ​ሐ​ቅና ከያ​ዕ​ቆብ ጋር ኖረ። መሠ​ረት ያላ​ትን ሠሪ​ዋና ፈጣ​ሪዋ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሆ​ነ​ላ​ትን ከተማ ደጅ ይጠኑ ነበ​ርና።

ዕብራውያን 11:1-10 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እምነት ተስፋ ያደረግነው ነገር እንደሚፈጸም ርግጠኛ የምንሆንበት፣ የማናየውም ነገር እውን መሆኑን የምንረዳበት ነው። አባቶችም የተመሰከረላቸው በዚሁ ነው። ዓለማት በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተፈጠሩ በእምነት እንረዳለን፤ ስለዚህ የሚታየው ነገር የተፈጠረው ከሚታየው እንዳልሆነ እንገነዘባለን። አቤል ከቃየል ይልቅ የበለጠ መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በእምነት አቀረበ። እግዚአብሔር ስለ ስጦታው በተናገረለት ጊዜ፣ እርሱ በእምነት ጻድቅ እንደ ሆነ ተመሰከረለት፤ ቢሞትም እንኳ እስከ አሁን በእምነቱ ይናገራል። ሔኖክ ሞትን እንዳያይ በእምነት ተወሰደ፤ “እግዚአብሔርም ስለ ወሰደው አልተገኘም”፤ ከመወሰዱም በፊት እግዚአብሔርን ደስ እንዳሠኘ ተመስክሮለታልና። ደግሞም ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሠኘት አይቻልም፤ ምክንያቱም ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ሁሉ እግዚአብሔር መኖሩንና ከልብ ለሚሹትም ዋጋ እንደሚሰጥ ማመን አለበት። ኖኅ ገና ስለማይታየው ነገር እግዚአብሔር ባስጠነቀቀው ጊዜ፣ እግዚአብሔርን ፈርቶ ቤተ ሰዎቹን ለማዳን መርከብን በእምነት ሠራ፤ በእምነቱ ዓለምን ኰነነ፤ በእምነትም የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ። አብርሃም ርስት አድርጎ ወደሚቀበለው ስፍራ እንዲሄድ በተጠራ ጊዜ በእምነት ታዘዘ፤ ወዴት እንደሚሄድ ባያውቅም፣ ዕሺ ብሎ ሄደ። በባዕድ አገር እንዳለ መጻተኛ በተስፋዪቱ ምድር በእምነት ተቀመጠ፤ የተስፋውን ቃል ዐብረውት እንደሚወርሱት እንደ ይሥሐቅና እንደ ያዕቆብ በድንኳን ኖረ፤ ምክንያቱም መሠረት ያላትን፣ እግዚአብሔር የሠራትንና የፈጠራትን ከተማ ይጠባበቅ ነበር።

ዕብራውያን 11:1-10 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው። ለሽማግሌዎች የተመሰከረላቸው በዚህ ነውና። ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተዘጋጁ፥ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን። አቤል ከቃየል ይልቅ የሚበልጥን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በእምነት አቀረበ፥ በዚህም፥ እግዚአብሔር ስለ ስጦታው ሲመሰክር፥ እርሱ ጻድቅ እንደ ሆነ ተመሰከረለት፤ ሞቶም ሳለ በመሥዋዕቱ እስከ አሁን ይናገራል። ሄኖክ ሞትን እንዳያይ በእምነት ተወሰደ፥ እግዚአብሔርም ስለ ወሰደው አልተገኘም። ሳይወሰድ እግዚአብሔርን ደስ እንዳሰኘ ተመስክሮለታልና፤ ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ኖኅ ገና ስለማይታየው ነገር ተረድቶ እግዚአብሔርን እየፈራ ቤተ ስዎቹን ለማዳን መርከብን በእምነት አዘጋጀ፥ በዚህም ዓለምን ኵኦነነ፥ በእምነትም የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ። አብርሃም የተባለው ርስት አድርጎ ሊቀበለው ወዳለው ስፍራ ለመውጣት በእምነት ታዘዘ፥ ወዴትም እንደሚሄድ ሳያውቅ ወጣ። ለእንግዶች እንደሚሆን በተስፋ ቃል በተሰጠው አገር በድንኳን ኖሮ፥ ያን የተስፋ ቃል አብረውት ከሚወርሱ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር፥ እንደ መጻተኛ በእምነት ተቀመጠ፤ መሠረት ያላትን፥ እግዚአብሔር የሠራትንና የፈጠራትን ከተማ ይጠብቅ ነበርና።

ዕብራውያን 11:1-10 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እምነት ማለት በተስፋ የሚጠበቀውን ነገር “አዎን በእውነት ይሆናል” ብሎ መቀበል ነው፤ በዐይን የማይታየውንም ነገር እንደሚታይ አድርጎ መቊጠር ነው። የቀድሞ ሰዎች የተመሰገኑት በእምነት ምክንያት ነው። ዓለም በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተፈጠረ የምንረዳው በእምነት ነው። ስለዚህ የሚታየው ነገር ሁሉ ከማይታየው እንደ ተሠራ እናውቃለን። አቤል ከቃየል መሥዋዕት የበለጠውን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ያቀረበው በእምነት ነው፤ እግዚአብሔር የአቤልን መባ በደስታ በተቀበለ ጊዜ አቤል በእምነቱ ጻድቅ መሆኑ ተመሰከረለት፤ አቤል ቢሞትም እንኳ በእምነቱ አማካይነት አሁንም እየተናገረ ነው። ሔኖክ ሞት እንዳይደርስበት ወደ ላይ የተወሰደው በእምነት ነው፤ እግዚአብሔር ስለ ወሰደውም አልተገኘም፤ ከመወሰዱ በፊት ደግሞ እግዚአብሔርን ደስ እንዳሰኘ ተመስክሮለታል። ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ሰው እግዚአብሔር መኖሩንና እርሱን ለሚፈልጉት ሰዎችም ስጦታን የሚሰጥ መሆኑን ማመን አለበት። ገና በዐይን ስለማይታዩት ነገሮች እግዚአብሔር ባስጠነቀቀው ጊዜ ኖኅ እግዚአብሔርን በመፍራት ቤተሰቡን ለማዳን መርከብን የሠራው በእምነት ነው፤ በኖኅም እምነት ዓለም ኃጢአተኛ መሆኑ ታውቆ ተፈረደበት፤ ኖኅም በእምነት የሚገኘውን ጽድቅ ወረሰ። አብርሃም ወጥቶ ርስት አድርጎ ወደሚቀበለው ስፍራ እንዲሄድ በተጠራ ጊዜ ምንም እንኳ ወዴት እንደሚሄድ ባያውቅም ለመሄድ የታዘዘው በእምነት ነው። ከእርሱ ጋር የተስፋው ቃል ወራሾች ከሆኑት ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር በተስፋይቱ አገር መጻተኛ ሆኖ በድንኳን የኖረው በእምነት ነው። ይህንንም ያደረገው ጽኑ መሠረት ያላትን፥ እግዚአብሔር ያቀዳትንና የሠራትን ከተማ ይጠባበቅ ስለ ነበር ነው።

ዕብራውያን 11:1-10 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር እርግጠኛ የምንሆንበት፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው። የቀደሙ አባቶቻችንም የተመሰከረላቸው በዚህ ነው። ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተፈጠሩ፥ የሚታየውም ነገር ከሚታዩት እንዳልተፈጠረ በእምነት እንረዳለን። አቤል ከቃየል ይልቅ የሚበልጥን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በእምነት አቀረበ፤ በዚህም እግዚአብሔር ስለ ስጦታው ሲመሰክር፥ እርሱ ጻድቅ እንደሆነ ተመሰከረለት፤ ሞቶም ሳለ በመሥዋዕቱ እስከ አሁን ይናገራል። ሄኖክ ሞትን እንዳያይ በእምነት ተወሰደ፤ እግዚአብሔርም ስለ ወሰደው አልተገኘም። ከመወሰዱም በፊት እግዚአብሔርን ደስ እንዳሰኘ ተመስክሮለታል። ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ እግዚአብሔር እንዳለና ለሚፈልጉትም ዋጋ እንደሚሰጥ ማመን አለበት። ኖኅ ገና ስለማይታየው ነገር ተረድቶ እግዚአብሔርን እየፈራ ቤተ ስዎቹን ለማዳን መርከብን በእምነት አዘጋጀ፤ በዚህም ዓለምን ኰነነ፤ በእምነትም የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ። አብርሃም ርስት አድርጎ ወደሚቀበለው ስፍራ እንዲሄድ በተጠራ ጊዜ በእምነት ታዘዘ፤ ወዴትም እንደሚሄድም ሳያውቅ ሄደ። ለባዕድ አገር እያለም በተስፋ ቃል በተሰጠው ምድር፥ ያን የተስፋ ቃል አብረውት ወራሾች እንደሆኑት እንደ ይስሐቅና እንደ ያዕቆብ በእምነት በድንኳን ኖረ፤ ምክንያቱም መሠረት ያላትን፥ እግዚአብሔር የሠራትንና የፈጠራትን ከተማ ይጠብቅ ነበር።

ዕብራውያን 11:1-10

ዕብራውያን 11:1-10 NASVዕብራውያን 11:1-10 NASVዕብራውያን 11:1-10 NASV