ዘፍጥረት 9:11-13
ዘፍጥረት 9:11-13 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ቃል ኪዳኔንም ከእናንተ ጋር አጸናለሁ፤ ሥጋ ያለውም ሁሉ ዳግመኛ በጥፋት ውኃ አይጠፋም፤ ምድርንም ለማጥፋት ዳግመኛ የጥፋት ውኃ አይሆንም።” እግዚአብሔር አምላክም ለኖኅ አለው፥ “በእኔና በእናንተ መካከል፥ ከእናንተም ጋር ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል፥ ለዘለዓለም ትውልድ የማደርገው የቃል ኪዳኔ ምልክት ይህ ነው፤ ቀስቴን በደመና አኖራለሁ፤ የቃል ኪዳኔም ምልክት በእኔና በምድር መካከል ይሆናል።
ዘፍጥረት 9:11-13 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከእንግዲህ ሕይወት ያለው ፍጡር ሁሉ በጥፋት ውሃ እንደማይጠፋ፣ ዳግመኛም ምድርን የሚያጠፋ ውሃ ከቶ እንደማይመጣ ከእናንተ ጋራ ኪዳን እገባለሁ።” እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ “በእኔና በእናንተ መካከል፣ ከእናንተም ጋራ ካሉ ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ጋራ ከሚመጣውም ትውልድ ሁሉ ጋራ፣ የማደርገው የኪዳኑ ምልክት ይህ ነው፤ ቀስተ ደመናዬን በደመና ላይ አደርጋለሁ፤ ይህም በእኔና በምድር መካከል ለገባሁት ኪዳን ምልክት ይሆናል።
ዘፍጥረት 9:11-13 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ቃል ኪዳንርንም ለእናንተ አቆማልሁ ሥጋ ያለውም ሁሉ ዳግመኝ በጥፋት ውኃ አይጠፉም ምድርንም ለማጥፋት ዳግመኛ የጥፋት ውኅ አይሆንም። እግዚአብሔርም አለ፤ በእኔና በእናንተ መካከላ፤ ከእናንትም ጋር ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል፥ ለዘላለም የማደርገው የቃል ኪዳን ምልክት ይህ ነው። ቀስቴን በደመና አድርጌአለሁ፥ የቃል ኪዳኑም ምልክት በእኔና በምድር መካከል ይሆናል።
ዘፍጥረት 9:11-13 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
በዚህም በገባሁላችሁ ቃል ኪዳን መሠረት፥ ከእንግዲህ ወዲህ ሕያዋን ፍጥረቶች ሁሉ በጥፋት ውሃ ከቶ አይደመሰሱም፤ ምድርም ዳግመኛ በጥፋት ውሃ አትጠፋም።” እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፦ “ከእናንተና ከሕያዋን ፍጥረቶች ሁሉ ጋር ለምገባው ለዚህ ለዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን ምልክት ይሆን ዘንድ፥ ቀስቴን በደመናዎች ላይ አደርጋለሁ፤ ይህም ቀስት ከምድር ጋር ለገባሁት ቃል ኪዳን ምልክት ሆኖ ይኖራል።
ዘፍጥረት 9:11-13 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ቃል ኪዳኔንም ለእናንተ እመሰርታለሁ፥ ሕያው ፍጥረት ሁሉ ዳግመኛ በጥፋት ውኃ አይጠፉም፥ ምድርንም ለማጥፋት ዳግመኛ የጥፋት ውኃ አይመጣም።” እንዲህም ሲል እግዚአብሔር ተናገረ፦ “በእኔና በእናንተ፥ ከእናንተም ጋር ባለው በሕያው ፍጥረት ሁሉ መካከል፥ ለዘለዓለም የማደርገው፥ የቃል ኪዳን ምልክት ይህ ነው፥ ቀስቴን በደመና አደርጋለሁ፥ ይህም በእኔና በምድር መካከል የቃል ኪዳን ምልክት ይሆናል።