ዘፍጥረት 7:1-6
ዘፍጥረት 7:1-6 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እግዚአብሔር አምላክም ኖኅን አለው፥ “አንተ ቤተሰቦችህን ሁሉ ይዘህ ወደ መርከብ ግባ፤ በዚህ ትውልድ በፊቴ ጻድቅ ሆነህ አይችሃለሁና። ከንጹሕ እንስሳ ሁሉ ሰባት ስባት ተባትና እንስት፥ ንጹሕ ካልሆነም እንስሳ ሁለት ሁለት ተባትና እንስት፤ ከንጹሕ የሰማይ ወፍ ደግሞ ሰባት ሰባት ተባትና እንስት፥ ንጹሕ ካልሆነ የሰማይ ወፍም ሁለት ሁለት ተባትና እንስት እያደረግህ በምድር ላይ ለምግብና ለዘር ይቀር ዘንድ ለአንተ ትወስዳለህ። ከሰባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዝናብ አዘንባለሁና፤ የፈጠርሁትንም ፍጥረት ሁሉ ከምድር ሁሉ ላይ አጠፋለሁና።” ኖኅም እግዚአብሔር አምላክ ያዘዘውን ሁሉ አደረገ። ኖኅም የጥፋት ውኃ በምድር ላይ በሆነ ጊዜ የስድስት መቶ ዓመት ዕድሜ ነበረ።
ዘፍጥረት 7:1-6 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እግዚአብሔር (ያህዌ) ኖኅን እንዲህ አለው፤ “በዚህ ትውልድ መካከል አንተን ጻድቅ ሆነህ አግኝቼሃለሁና ቤተ ሰብህን በሙሉ ይዘህ ወደ መርከቧ ግባ። ከንጹሕ እንስሳት ሁሉ ሰባት ሰባት ተባዕትና እንስት፣ ንጹሕ ካልሆኑት እንስሳት ደግሞ ሁለት ሁለት ተባዕትና እንስት እንዲሁም ከወፎች ወገን ሁሉ ሰባት ተባዕትና ሰባት እንስት፣ በምድር ላይ ለዘር እንዲተርፉ ከአንተ ጋር ታስገባለህ። ከሰባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዝናብ አዘንባለሁ፤ የፈጠርሁትንም ሕያው ፍጡር ሁሉ ከምድር ገጽ አጠፋለሁ።” ኖኅም እግዚአብሔር (ያህዌ) ያዘዘውን ሁሉ አደረገ። የጥፋት ውሃ በምድር ላይ በወረደ ጊዜ ኖኅ የ600 ዓመት ሰው ነበር።
ዘፍጥረት 7:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እግዚአብሔርም ኖኅን አለው፤ አንተ ቤተሰቦችህን ሁሉ ይዘህ ወደ መርከብ ግባ በዚህ ትውልድ በፊቴ ጻድቅ ሆነህ አይቼሃለሁና። ከንጹሕ እንስሳ ሁሉ ሰባት ሰባት ተባትና እንስት ንጽሕ ካልሆነ እንስሳም ሁለት ሁለት ተባትና እንስት፤ ከሰማይ ወፍ ደግሞ ሰባት ሰባት ተባትና እንስት እያደረልግልህ በምድር ላይ ለዘር ይቀር ዘንድ ለአንተ ትውስዳለህ። ከሰባት ቀን በኍላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዝናብ አዘንባለሁና፤ የፈጠርሁትንም ፍጥረት ሁሉ ከምድር ላይ አጠፉለሁና። ኖኅም እግዚአብሔር እንዳዘዘው ሁሉ አደረገ። ኖኅም የጥፋት ውኂ በምድር ላይ በሆነ ጊዜ የስድስት መቶ ዓመት ዕድሜ ነበረ።
ዘፍጥረት 7:1-6 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እግዚአብሔር ኖኅን እንዲህ አለው፤ “በዚህ ዘመን ካለው ትውልድ መካከል ጻድቅ አንተ ብቻ ሆነህ ስላገኘሁህ፥ ከመላው ቤተሰብህ ጋር ወደ መርከቡ ግባ። ንጹሕ ከሆኑት ወንዶችና ሴቶች እንስሶች ሁሉ ሰባት ወንድ፥ ሰባት ሴት ከአንተ ጋር ወደ መርከቡ አስገባ፤ ንጹሕ ካልሆኑት ወንዶችና ሴቶች እንስሶች ሁሉ ግን፥ አንድ ወንድ አንድ ሴት አስገባ። ከያንዳንዱ ዐይነት ወፍ ወንድና ሴት ሰባት ወንድ ሰባት ሴት አስገባ፤ ይህንንም የምታደርገው እያንዳንዱ ዐይነት እንስሳና ወፍ በሕይወት እንዲኖርና በምድር ላይ ለዘር እንዲተርፍ ነው። የፈጠርኩትን ሕያው ፍጡር ሁሉ ከምድር ገጽ ላይ ለማጥፋት ከሰባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ሙሉ ዝናብ አዘንባለሁ።” ኖኅም እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ አደረገ። የጥፋት ውሃ በምድር ላይ በመጣ ጊዜ የኖኅ ዕድሜ 600 ዓመት ነበር።
ዘፍጥረት 7:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ጌታም ኖኅን እንዲህ አለው፦ “በዚህ ዘመን ካለው ትውልድ መካከል ጻድቅ አንተ ሆነህ አይቼሃለሁና፥ አንተ ቤተሰቦችህን ሁሉ ይዘህ ወደ መርከብ ግባ። ከንጹሕ እንስሳ ሁሉ ሰባት ሰባት ተባዕትና እንስት፥ ንጹሕ ካልሆነ እንስሳም ሁለት ሁለት ተባዕትና እንስት፤ ከሰማይ ወፍ ደግሞ ሰባት ሰባት ተባዕትና እንስት እያደረግህ በምድር ላይ ለዘር ይቀር ዘንድ ለአንተ ትወስዳለህ። የፈጠርሁትንም ፍጥረት ሁሉ ከምድር ላይ ለማጥፋት ከሰባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዝናብ አዘንባለሁ።” ኖኅም እግዚአብሔር እንዳዘዘው ሁሉ አደረገ። የጥፋት ውኃ በምድር ላይ በመጣ ጊዜ የኖኅ ዕድሜ ስድስት መቶ ዓመት ነበረ።