ዘፍጥረት 7:1-11

ዘፍጥረት 7:1-11 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ኖኅን አለው፥ “አንተ ቤተ​ሰ​ቦ​ች​ህን ሁሉ ይዘህ ወደ መር​ከብ ግባ፤ በዚህ ትው​ልድ በፊቴ ጻድቅ ሆነህ አይ​ች​ሃ​ለ​ሁና። ከን​ጹሕ እን​ስሳ ሁሉ ሰባት ስባት ተባ​ትና እን​ስት፥ ንጹሕ ካል​ሆ​ነም እን​ስሳ ሁለት ሁለት ተባ​ትና እን​ስት፤ ከን​ጹሕ የሰ​ማይ ወፍ ደግሞ ሰባት ሰባት ተባ​ትና እን​ስት፥ ንጹሕ ካል​ሆነ የሰ​ማይ ወፍም ሁለት ሁለት ተባ​ትና እን​ስት እያ​ደ​ረ​ግህ በም​ድር ላይ ለም​ግ​ብና ለዘር ይቀር ዘንድ ለአ​ንተ ትወ​ስ​ዳ​ለህ። ከሰ​ባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በም​ድር ላይ ዝናብ አዘ​ን​ባ​ለ​ሁና፤ የፈ​ጠ​ር​ሁ​ት​ንም ፍጥ​ረት ሁሉ ከም​ድር ሁሉ ላይ አጠ​ፋ​ለ​ሁና።” ኖኅም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ አደ​ረገ። ኖኅም የጥ​ፋት ውኃ በም​ድር ላይ በሆነ ጊዜ የስ​ድ​ስት መቶ ዓመት ዕድሜ ነበረ። ኖኅም ስለ ጥፋት ውኃ ልጆ​ቹ​ንና ሚስ​ቱን፥ የል​ጆ​ቹ​ንም ሚስ​ቶች ይዞ ወደ መር​ከብ ገባ። ከን​ጹ​ሓን ወፎ​ችና ንጹ​ሓን ካል​ሆኑ ወፎች፥ ከን​ጹሕ እን​ስሳ፥ ንጹ​ሕም ካል​ሆ​ነው እን​ስሳ፥ በም​ድር ላይ ከሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሰው ሁሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኖኅን እን​ዳ​ዘ​ዘው፥ ሁለት ሁለት ተባ​ትና እን​ስት እየ​ሆኑ ወደ ኖኅ ወደ መር​ከብ ውስጥ ገቡ። ከሰ​ባት ቀን በኋ​ላም የጥ​ፋት ውኃ በም​ድር ላይ ሆነ። በኖኅ ዕድሜ በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው መቶ ዓመት በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥራ ሰባ​ተ​ኛው ዕለት፥ በዚ​ያው ቀን የታ​ላቁ ቀላይ ምን​ጮች ሁሉ ተነ​ደሉ፤ የሰ​ማይ መስ​ኮ​ቶ​ችም ተከ​ፈቱ፤

ዘፍጥረት 7:1-11 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እግዚአብሔር ኖኅን እንዲህ አለው፤ “በዚህ ትውልድ መካከል አንተን ጻድቅ ሆነህ አግኝቼሃለሁና ቤተ ሰብህን በሙሉ ይዘህ ወደ መርከቧ ግባ። ከንጹሕ እንስሳት ሁሉ ሰባት ሰባት ተባዕትና እንስት፣ ንጹሕ ካልሆኑት እንስሳት ደግሞ ሁለት ሁለት ተባዕትና እንስት ውሰድ፤ እንዲሁም ከወፎች ወገን ሁሉ ሰባት ተባዕትና ሰባት እንስት፣ በምድር ላይ ለዘር እንዲተርፉ ከአንተ ጋራ ታስገባለህ። ከሰባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዝናብ አዘንባለሁ፤ የፈጠርሁትንም ሕያው ፍጡር ሁሉ ከምድር ገጽ አጠፋለሁ።” ኖኅም እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ አደረገ። የጥፋት ውሃ በምድር ላይ በወረደ ጊዜ ኖኅ የስድስት መቶ ዓመት ሰው ነበር። ኖኅና ወንዶች ልጆቹ፣ ሚስቱና የልጆቹ ሚስቶች ከጥፋት ውሃ ለመትረፍ ወደ መርከቧ ገቡ። ንጹሕ ከሆኑትና ንጹሕ ካልሆኑት እንስሳት፣ ከወፎችና በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጥረታት ሁሉ ጥንድ ጥንድ፣ ተባዕትና እንስት ሆነው ወደ ኖኅ መጡ፤ እግዚአብሔር ኖኅን ባዘዘውም መሠረት ወደ መርከቧ ገቡ። ከሰባት ቀንም በኋላ የጥፋት ውሃ በምድር ላይ መጣ። ኖኅ በተወለደ በስድስት መቶኛው ዓመት፣ በሁለተኛው ወር፣ ከወሩም በዐሥራ ሰባተኛው ቀን፣ በዚያ ቀን የታላቁ ጥልቅ ምንጮች በሙሉ ተነደሉ፤ የሰማይ መስኮቶችም ተከፈቱ፤

ዘፍጥረት 7:1-11 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እግዚአብሔርም ኖኅን አለው፤ አንተ ቤተሰቦችህን ሁሉ ይዘህ ወደ መርከብ ግባ በዚህ ትውልድ በፊቴ ጻድቅ ሆነህ አይቼሃለሁና። ከንጹሕ እንስሳ ሁሉ ሰባት ሰባት ተባትና እንስት ንጽሕ ካልሆነ እንስሳም ሁለት ሁለት ተባትና እንስት፤ ከሰማይ ወፍ ደግሞ ሰባት ሰባት ተባትና እንስት እያደረልግልህ በምድር ላይ ለዘር ይቀር ዘንድ ለአንተ ትውስዳለህ። ከሰባት ቀን በኍላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዝናብ አዘንባለሁና፤ የፈጠርሁትንም ፍጥረት ሁሉ ከምድር ላይ አጠፉለሁና። ኖኅም እግዚአብሔር እንዳዘዘው ሁሉ አደረገ። ኖኅም የጥፋት ውኂ በምድር ላይ በሆነ ጊዜ የስድስት መቶ ዓመት ዕድሜ ነበረ። ኖኅም ስለ ጥፋት ውኂ ልጆቹንና ሚስቱን የልጆቹንም ሚስቶች ይዞ ወደ መርከብ ገባ። ከንጽሕ እንስሳ ንጽሕም ካልሆነው እንስሳ ከወፎችና በምድር ላይ ከሚንቀሳቀስውም ሁሉ፤ እግዚአብሔር ኖኅን እንዳዘዘው ሁለት ሁለት ተባትና እንስት እየሆኑ ወደ ኖኅ ወደ መርከብ ውስጥ ገቡ። ከሰባት ቀንም በኍላ የጥፋት ውኂ በምድር ላይ ሆነ። በኖኅ ዕድሜ በስድስተኛው መቶ ዓመት በሁለተኛው ወር ከወሩም በአሥራ ስባተኛው ዕለት በዚያው ቀን የታላቁ ቀላይ ምንጮች ሁሉ ተነደሉ፤

ዘፍጥረት 7:1-11 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እግዚአብሔር ኖኅን እንዲህ አለው፤ “በዚህ ዘመን ካለው ትውልድ መካከል ጻድቅ አንተ ብቻ ሆነህ ስላገኘሁህ፥ ከመላው ቤተሰብህ ጋር ወደ መርከቡ ግባ። ንጹሕ ከሆኑት ወንዶችና ሴቶች እንስሶች ሁሉ ሰባት ወንድ፥ ሰባት ሴት ከአንተ ጋር ወደ መርከቡ አስገባ፤ ንጹሕ ካልሆኑት ወንዶችና ሴቶች እንስሶች ሁሉ ግን፥ አንድ ወንድ አንድ ሴት አስገባ። ከያንዳንዱ ዐይነት ወፍ ወንድና ሴት ሰባት ወንድ ሰባት ሴት አስገባ፤ ይህንንም የምታደርገው እያንዳንዱ ዐይነት እንስሳና ወፍ በሕይወት እንዲኖርና በምድር ላይ ለዘር እንዲተርፍ ነው። የፈጠርኩትን ሕያው ፍጡር ሁሉ ከምድር ገጽ ላይ ለማጥፋት ከሰባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ሙሉ ዝናብ አዘንባለሁ።” ኖኅም እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ አደረገ። የጥፋት ውሃ በምድር ላይ በመጣ ጊዜ የኖኅ ዕድሜ 600 ዓመት ነበር። ኖኅ፥ ሚስቱ፥ ልጆቹና ሚስቶቻቸው ከጥፋት ውሃ ለማምለጥ ወደ መርከቡ ገቡ። ንጹሕ ከሆኑትና ካልሆኑት ከያንዳንዱ ዐይነት እንስሶች ወፎች፥ በደረታቸው እየተሳቡ ከሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶች ሁሉ ጥንድ ወንድና ሴት እየሆኑ፥ እግዚአብሔር ኖኅን ባዘዘውም መሠረት ወደ ኖኅ ወደ መርከቡ ገቡ። ከሰባትም ቀን በኋላ የጥፋት ውሃ በምድር ላይ መጣ። ኖኅ 600 ዓመት በሆነው ጊዜ፥ በሁለተኛው ወር በዐሥራ ሰባተኛው ቀን ላይ ከምድር በታች ያለው የታላቁ ውሃ ምንጮች ሁሉ በድንገት ተነደሉ፤ በሰማይ ያሉት የውሃ መስኮቶች ሁሉ ተከፈቱ።

ዘፍጥረት 7:1-11 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ጌታም ኖኅን እንዲህ አለው፦ “በዚህ ዘመን ካለው ትውልድ መካከል ጻድቅ አንተ ሆነህ አይቼሃለሁና፥ አንተ ቤተሰቦችህን ሁሉ ይዘህ ወደ መርከብ ግባ። ከንጹሕ እንስሳ ሁሉ ሰባት ሰባት ተባዕትና እንስት፥ ንጹሕ ካልሆነ እንስሳም ሁለት ሁለት ተባዕትና እንስት፤ ከሰማይ ወፍ ደግሞ ሰባት ሰባት ተባዕትና እንስት እያደረግህ በምድር ላይ ለዘር ይቀር ዘንድ ለአንተ ትወስዳለህ። የፈጠርሁትንም ፍጥረት ሁሉ ከምድር ላይ ለማጥፋት ከሰባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዝናብ አዘንባለሁ።” ኖኅም እግዚአብሔር እንዳዘዘው ሁሉ አደረገ። የጥፋት ውኃ በምድር ላይ በመጣ ጊዜ የኖኅ ዕድሜ ስድስት መቶ ዓመት ነበረ። ኖኅ፥ ሚስቱ፥ ልጆቹና ሚስቶቻቸው ከጥፋት ውሃ ለማምለጥ ወደ መርከቡ ገቡ። ከንጹሕ እንስሳ ንጹሕም ካልሆነው እንስሳ፥ ከወፎችና በምድር ላይ ከሚንቀሳቀሰውም ሁሉ፥ ጥንድ ተባዕትና እንስት እየሆኑ፥ እግዚአብሔር ኖኅን ባዘዘውም መሠረት ወደ ኖኅ ወደ መርከቡ ገቡ። ከሰባት ቀንም በኋላ የጥፋት ውኃ በምድር ላይ መጣ። ኖኅ ስድስት መቶ ዓመት በሆነው፥ በሁለተኛው ወር፥ ከወሩም በዓሥራ ሰባተኛው ቀን ላይ፥ ከምድር በታች ያለው የታላቁ ጥልቅ መፍለቂያዎች ሁሉ በድንገት ተነደሉ፥ የሰማያትም መስኮቶች ተከፈቱ፥