የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘፍጥረት 50:15-20

ዘፍጥረት 50:15-20 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

የዮ​ሴ​ፍም ወን​ድ​ሞች አባ​ታ​ቸው እንደ ሞተ በአዩ ጊዜ እን​ዲህ አሉ፥ “ምና​ል​ባት ዮሴፍ ያደ​ረ​ግ​ን​በ​ትን ክፋት ያስ​ብ​ብን ይሆ​ናል፤ ባደ​ረ​ግ​ን​በ​ትም ክፋት ሁሉ ብድ​ራት ይመ​ል​ስ​ብን ይሆ​ናል።” ወደ ዮሴ​ፍም መጡ፤ እን​ዲ​ህም አሉት፥ “አባ​ትህ ገና ሳይ​ሞት እን​ዲህ ብሎ አዝ​ዟል፦ ‘ዮሴ​ፍን እን​ዲህ በሉት፦ እባ​ክህ የወ​ን​ድ​ሞ​ች​ህን በደል ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ይቅር በል፤ እነ​ርሱ በአ​ንተ ክፉ አድ​ር​ገ​ው​ብ​ሃ​ልና፤’ አሁ​ንም እባ​ክህ የአ​ባ​ትህ አም​ላክ ባሪ​ያ​ዎች የበ​ደ​ሉ​ህን ይቅር በል።” ዮሴ​ፍም ይህን ሲሉት አለ​ቀሰ። ወን​ድ​ሞቹ ደግሞ መጡ፤ “እነሆ፥ እኛ ለአ​ንተ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ነን” አሉት። ዮሴ​ፍም አላ​ቸው፥ “አት​ፍሩ፤ ይህ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ሆኖ​አ​ልና። እና​ንተ በእኔ ላይ ክፉ መከ​ራ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እን​ዲ​መ​ገብ ለማ​ድ​ረግ ለእኔ መል​ካም መከረ።

ዘፍጥረት 50:15-20 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

የዮሴፍ ወንድሞች አባታቸው ከሞተ በኋላ “ዮሴፍ ባደረስንበት በደል ሁሉ እስከ አሁንም ቂም ይዞ ሊበቀለን ቢፈልግ ምን እናደርጋለን?” ተባባሉ። ስለዚህ እንዲህ የሚል መልእክት ወደ ዮሴፍ ላኩ፤ “አባትህ ከመሞቱ በፊት፥ ‘ወንድሞችህ በበደሉህ ጊዜ ያደረሱብህን ጒዳት ሁሉ አትቊጠርባቸው ብሎሃል’ ብለን እንድንነግርህ አዞናል፤ ስለዚህ እኛ የአባትህ አምላክ አገልጋዮች ያደረስንብህን በደል ሁሉ ይቅር እንድትለን እንለምንሃለን።” ዮሴፍ ይህን በሰማ ጊዜ አለቀሰ። ከዚህ በኋላ ወንድሞቹ ራሳቸው በፊቱ ቀርበው ጐንበስ ብለው እጅ ነሡና “እነሆ እኛ ሁላችን አገልጋዮችህ ነን” አሉት። ነገር ግን ዮሴፍ እንዲህ አላቸው፤ “አይዞአችሁ አትፍሩ፤ እኔ በእግዚአብሔር ምትክ የምሆን አይደለሁም፤ በእርግጥ እናንተ ክፉ ነገር መክራችሁብኝ ነበር፤ እግዚአብሔር ግን ወደ መልካም ነገር ለወጠው፤ ይህንንም ያደረገው አሁን በሕይወት ያሉትን የብዙ ሰዎችን ሕይወት ለማትረፍ ብሎ ነው።