የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘፍጥረት 45:3-11

ዘፍጥረት 45:3-11 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ዮሴ​ፍም ለወ​ን​ድ​ሞቹ፥ “እኔ ወን​ድ​ማ​ችሁ ዮሴፍ ነኝ፤ አባቴ እስከ አሁን በሕ​ይ​ወቱ ነውን?” አላ​ቸው። ወን​ድ​ሞ​ቹም ይመ​ል​ሱ​ለት ዘንድ አል​ቻ​ሉም፤ ደን​ግ​ጠው ነበ​ርና። ዮሴ​ፍም ወን​ድ​ሞ​ቹን፥ “ወደ እኔ ቅረቡ” አላ​ቸው። ወደ እር​ሱም ቀረቡ። እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ወደ ግብፅ የሸ​ጣ​ች​ሁኝ እኔ ወን​ድ​ማ​ችሁ ዮሴፍ ነኝ። አሁ​ንም ወደ​ዚህ ስለ​ሸ​ጣ​ች​ሁኝ አት​ፍሩ፤ አት​ቈ​ር​ቈ​ሩም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሕ​ይ​ወት ከእ​ና​ንተ በፊት ልኮ​ኛ​ልና። እነሆ፥ ይህ ሁለቱ ዓመት በም​ድር ላይ ራብ የሆ​ነ​በት ነውና፤ የማ​ይ​ታ​ረ​ስ​በ​ትና የማ​ይ​ታ​ጨ​ድ​በት አም​ስት ዓመት ገና አለ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በም​ድር ላይ እን​ድ​ት​ድ​ኑና እን​ድ​ት​ተ​ርፉ እመ​ግ​ባ​ችሁ ዘንድ ከእ​ና​ንተ በፊት ላከኝ። አሁ​ንም እና​ንተ ወደ​ዚህ የላ​ካ​ች​ሁኝ አይ​ደ​ላ​ች​ሁም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላከኝ እንጂ፤ ለፈ​ር​ዖ​ንም እንደ አባት አደ​ረ​ገኝ፤ በቤ​ቱም ሁሉ ላይ ጌታ፥ በግ​ብፅ ምድ​ርም ሁሉ ላይ አለቃ አደ​ረ​ገኝ። አሁ​ንም ፈጥ​ና​ችሁ ወደ አባቴ ሂዱ፤ እን​ዲ​ህም በሉት፦ ልጅህ ዮሴፍ የሚ​ለው ነገር ይህ ነው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ላይ ጌታ አደ​ረ​ገኝ፤ ወደ እኔ ና፤ በዚ​ያም አት​ዘ​ግይ፤ በዐ​ረብ በኩል በጌ​ሤም ምድ​ርም ትቀ​መ​ጣ​ለህ፤ ወደ እኔም ትቀ​ር​ባ​ለህ። አን​ተና ልጆ​ችህ የል​ጆ​ች​ህም ልጆች፥ በጎ​ች​ህና ላሞ​ችህ፥ የአ​ንተ የሆ​ነው ሁሉ፥ በዚ​ያም አን​ተና የቤ​ትህ ሰዎች የአ​ንተ የሆ​ነው ሁሉ እን​ዳ​ት​ቸ​ገሩ እመ​ግ​ብ​ሃ​ለሁ፤ የራቡ ዘመን ገና አም​ስት ዓመት ቀር​ቶ​አ​ልና፤

ዘፍጥረት 45:3-11 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ዮሴፍም ወንድሞቹን፣ “እኔ ዮሴፍ ነኝ፤ ለመሆኑ አባቴ እስካሁን በሕይወት አለ?” ሲል ጠየቃቸው። ወንድሞቹ ግን በፊቱ ተደናግጠው ስለ ነበር መልስ ሊሰጡት አልቻሉም። ዮሴፍም ወንድሞቹን፣ “እስቲ ወደ እኔ ቀረብ በሉ” አላቸው፤ ወደ እርሱም በቀረቡ ጊዜ እንዲህ አለ፤ “ወደ ግብፅ የሸጣችሁኝ ወንድማችሁ እኔ ዮሴፍ ነኝ፤ አሁንም በመሸጣችሁ አትቈጩ፤ በራሳችሁም አትዘኑ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ሕይወት ለማዳን ሲል ከእናንተ አስቀድሞ እኔን ወደዚህ ልኮኛል። በምድር ላይ ራብ ከገባ ይኸው ሁለት ዓመት ሆነ፤ ከዚህ በኋላም የማይታረስባቸውና ሰብል የማይሰበሰብባቸው አምስት ዓመታት ገና አሉ። ነገር ግን እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ሕይወታችሁን በታላቅ ማዳን ለመታደግና ዘራችሁ ከምድር ላይ እንዳይጠፋ በማሰብ ከእናንተ አስቀድሞ ወደዚህ ላከኝ። “ስለዚህ አሁን ወደዚህ የላከኝ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) እንጂ እናንተ አይደላችሁም፤ እርሱም ለፈርዖን እንደ አባት፣ በቤት ንብረቱ ላይ ጌታ፣ እንዲሁም በግብፅ ምድር ላይ ገዥ አደረገኝ። አሁንም በፍጥነት ወደ አባቴ ተመልሳችሁ እንዲህ በሉት፤ ልጅህ ዮሴፍ እንዲህ ይላል፤ ‘እግዚአብሔር (ኤሎሂም) የመላው ግብፅ ጌታ አድርጎኛል፤ ስለዚህ ሳትዘገይ ወደ እኔ ና። ልጆችህን፣ የልጅ ልጆችህን፣ በጎችህን፣ ፍየሎችህን፣ ከብቶችህንና ያለህን ሁሉ ይዘህ በአቅራቢያዬ በጌሤም ትኖራለህ። ገና ወደ ፊት የሚመጣ የአምስት ዓመት ራብ ስላለ፣ በዚያ የሚያስፈልጋችሁን እኔ እሰጣችኋለሁ፤ ያለበለዚያ ግን አንተና ቤተ ሰዎችህ ያንተም የሆነው ሁሉ፣ ችግር ላይ ትወድቃላችሁ።’

ዘፍጥረት 45:3-11 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ዮሴፍም ለወንድሞቹ፦ እኔ ዮሴፍ ነኝ አባቴ እስከ አሁን በሕይወቱ ነውን? አለ። ወንድሞቹም ይመጠው ነበርና። ዮሴፍም ወንድሞቹን፦ ወደ እኔ ቅረቡ አለ። ወደ እርሱም ቀረቡ እንዲህም አላቸው፦ ወደ ግብፅ የሸጣችሁኝ እኔ ወንድማችሁ ዮሴፍ ነኝ። አሁንም ወደዚህ ስለ ሸጣችሁኝ አትዘኑ አትቆርቆሩም እግዚአብሔር ሕይወትን ለማዳን ከእናንተ በፊት ሰድዶኛልና። ይህ ሁለቱ ዓመት በምድር ላይ ራብ የሆነበት ነውና የማይታረስበትና የማይታጨድበት አምስት ዓመት ገና ቀረ። እግዚአብሔርም በምድር ላይ ቅሬታን አስቀርላችሁ ዘንድ በታላቅ መድኃኒትም አድናችሁ ዘንድ ከእናንተ በፊት ላከኝ። አሁንም እናንተ ወደዚህ የላካችሁኝ አይደላችሁም እግዚአብሔር ላከኝ እንጂ ለፈርዖንም እንደ አባት አደረገኝ በቤቱምም ሁሉ ላይ ጌታ በግብፅ ምድርም ሁሉ ላይ አለቃ አደረገኝ። አሁንም ፈጥናችሁ ወደ አባቴ ውጡ እንዲህም በሉት፦ ልጅህ ዮሴፍ የሚለው ነገር ይህ ነው፦ እግዚአብሔር በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ጌታ አደረገኝ፥ ወደ እኔ ና አትዘግይ በጌሤምም ምድር ትቀመጣለህ ወደ እኔም ትቀርባለህ አንተና ልጆችህ የልጆችህም ልጆች በጎችህና ላሞችህ ከብትህም ሁሉ፤ በዚያም አንተና የቤትህ ሰዎች የአንተ የሆነው ሁሉ እንዳትቸገሩ እመግብሃለሁ የራቡ ዘመን ገና አምስት ዓመት ቀርቶአልና።

ዘፍጥረት 45:3-11 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ዮሴፍ ወንድሞቹን “እኔ ዮሴፍ ነኝ፤ አባቴ እስከ አሁን በሕይወት አለን?” አላቸው። ወንድሞቹ የተናገረውን በሰሙ ጊዜ እጅግ ደነገጡ፤ መልስ መስጠትም ተሳናቸው። በዚህ ጊዜ ዮሴፍ “እስቲ ወደ እኔ ቀረብ በሉ” አላቸው፦ ከቀረቡም በኋላ እንዲህ አላቸው፦ “እኔ ወደ ግብጽ የሸጣችሁኝ ወንድማችሁ ዮሴፍ ነኝ፤ ነገር ግን ይህን በማድረጋችሁ በመጸጸት አትበሳጩ፤ እግዚአብሔር እኔን አስቀድሞ የላከኝ የሰዎችን ሕይወት እንዳተርፍ ነው። በምድር ላይ ራብ ከገባ ሁለተኛ ዓመቱን ይዞአል፤ ሰዎች አርሰው መከር መሰብሰብ የማይችሉባቸው አምስት ዓመቶች ገና ይመጣሉ። እግዚአብሔር አስቀድሞ ወደዚህ የላከኝ በዚህ በአስደናቂ ዘዴ የእናንተን ሕይወት በማዳን በምድር ላይ ዘር እንዲቀርላችሁ አስቦ ነው። “ስለዚህ ወደዚህ የላከኝ ራሱ እግዚአብሔር እንጂ እናንተ አይደላችሁም፤ እግዚአብሔር ለፈርዖን እንደ መካሪ አባት፥ በቤት ንብረቱ ላይ ጌታና የመላው ግብጽ አገር ገዢ አደረገኝ። አሁን በፍጥነት ተመልሳችሁ ወደ አባቴ ሂዱና ልጅህ ዮሴፍ እንዲህ ይልሃል በሉት፤ ‘እግዚአብሔር የመላው ግብጽ ገዢ አድርጎኛል፤ ስለዚህ ሳትዘገይ ወደ እኔ ና፤ ልጆችህን፥ የልጅ ልጆችህን፥ በጎችህን፥ ፍየሎችህን፥ ከብቶችህን ሌላም ያለህን ነገር ሁሉ ይዘህ ና፥ በእኔው አቅራቢያ በሚገኘው በጌሴም ምድር ትኖራለህ። አምስት የራብ ዓመቶች ገና ስለሚቀሩ አንተና ቤተሰብህ እንስሶችህም ጭምር ራብ እንዳይደርስባችሁ በጌሴም እመግብሃለሁ።’ ”

ዘፍጥረት 45:3-11 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ዮሴፍም ለወንድሞቹ “እኔ ዮሴፍ ነኝ፥ አባቴ እስከ አሁን በሕይወቱ አለን?” አለ። ወንድሞቹም፥ በፊቱ ደንግጠው ነበርና፥ ሊመልሱለት አልቻሉም። ዮሴፍም ወንድሞቹን “እስቲ ወደ እኔ ቅረቡ” አለ። ወደ እርሱም ቀረቡ። እንዲህም አላቸው “ወደ ግብጽ የሸጣችሁኝ እኔ ወንድማችሁ ዮሴፍ ነኝ። አሁንም ወደዚህ ስለ ሸጣችሁኝ አትዘኑ፥ አትቈርቈሩም፥ እግዚአብሔር ሕይወትን ለማዳን ከእናንተ በፊት ልኮኛልና። ይህ በምድር ላይ ሁለት ዓመት ራብ የሆነበት ነው፥ ገና የማይታረስበትና የማይታጨድበት አምስት ዓመት ይመጣል። እግዚአብሔርም በምድር ላይ ቅሬታን አስቀርላችሁ ዘንድ በታላቅ መድኃኒትም አድናችሁ ዘንድ ከእናንተ በፊት ላከኝ። አሁንም እናንተ ወደዚህ የላካችሁኝ አይደላችሁም፥ እግዚአብሔር ላከኝ እንጂ፥ ለፈርዖንም እንደ አባት አደረገኝ፥ በቤቱምም ሁሉ ላይ ጌታ፥ በግብጽ ምድርም ሁሉ ላይ አለቃ አደረገኝ። አሁንም ፈጥናችሁ ወደ አባቴ ውጡ፥ እንዲህም በሉት፦ ‘ልጅህ ዮሴፍ የሚለው ነገር ይህ ነው፦ እግዚአብሔር በግብጽ ምድር ሁሉ ላይ ጌታ አደረገኝ፥ ወደ እኔ ና አትዘግይ፥ አንተና ልጆችህ የልጆችህም ልጆች፥ በጎችህና ላሞችህ ከብትህም ሁሉ፥ ከእኔም በቅርበት፥ በጌሤምም ምድር ትቀመጣለህ። በዚያም፥ የራቡ ዘመን ገና አምስት ዓመት ቀርቶአልና፥ አንተና የቤትህ ሰዎች የአንተ የሆነው ሁሉ እንዳትቸገሩ እመግብሃለሁ።’