የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘፍጥረት 41:46-57

ዘፍጥረት 41:46-57 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ዮሴፍ የግብጽ ንጉሥ ፈርዖንን ማገልገል ሲጀምር፣ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበር። ዮሴፍም ከፈርዖን ፊት ወጥቶ የግብጽን ምድር በሙሉ ዞረ። በሰባቱም የጥጋብ ዓመታት ምድሪቱ የተትረፈረፈ ሰብል ሰጠች። በእነዚያ ሰባት የጥጋብ ዓመታት፣ ዮሴፍ በግብጽ አገር የተገኘውን ምርት ሰብስቦ በየከተሞቹ አከማቸ፤ በእያንዳንዱ ከተማ ከየአቅራቢያው የተመረተውን እህል እንዲከማች አደረገ። ዮሴፍ ብዛቱ እንደ ባሕር አሸዋ የሚሆን የእህል ሰብል አከማቸ፤ ሰብሉ እጅግ ከመብዛቱ የተነሣ ልኩን መስፈርና መመዝገብ አልቻለም ነበር። ሰባቱ የራብ ዓመታት ከመምጣቱ በፊት፣ የሄልዮቱ ካህን የጶጥፌራ ልጅ አስናት ለዮሴፍ ሁለት ወንዶች ልጆች ወለደችለት። ዮሴፍም፣ “እግዚአብሔር መከራዬን ሁሉ፣ የአባቴንም ቤት እንድረሳ አድርጎኛል” በማለት የመጀመሪያ ልጁን ስም ምናሴ አለው። እንደዚሁም፣ “መከራ በተቀበልሁበት ምድር እግዚአብሔር ፍሬያማ አደረገኝ” ሲል ሁለተኛ ልጁን ኤፍሬም አለው። በግብጽ ምድር የነበረው ሰባቱ የጥጋብ ዘመን ዐለፈና ዮሴፍ አስቀድሞ እንደ ተናገረው የሰባቱ ዓመት የራብ ዘመን ጀመረ። ሌሎች አገሮች ሁሉ ሲራቡ፣ በመላው የግብጽ ምድር ግን ምግብ ነበር። ራቡ በመላው የግብጽ ምድር መስፋፋት ሲጀምር፣ ሕዝቡ ምግብ ይሰጠን በማለት ወደ ፈርዖን ጮኸ። ፈርዖንም ግብጻውያኑን፣ “ወደ ዮሴፍ ሂዱና የሚላችሁን አድርጉ” አላቸው። ራቡ በአገሩ ላይ እየተስፋፋ ስለ ሄደ፣ ዮሴፍ ጐተራዎቹን ከፍቶ እህሉ ለግብጻውያን እንዲሸጥ አደረገ፤ ምክንያቱም ራቡ በመላዪቱ ግብጽ ጸንቶ ነበር። ራቡ በመላው ዓለም ጸንቶ ስለ ነበር፣ የየአገሩ ሰዎች ሁሉ ከዮሴፍ ዘንድ እህል ለመሸመት ወደ ግብጽ ምድር መጡ።

ዘፍጥረት 41:46-57 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ዮሴፍም በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ፊት በቆመ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበረ። ዮሴፍም ከፈርዖን ፊት ወጣ የግብፅ ምድርንም ሁሉ ዞረ። በሰባቱም በጥጋብ ዓመታት የምድሪቱ ፍሬ ክምር ሆነ። በግብፅ ምድር ሁሉ ያለውን የሰባቱን ዓመታ እህል ሁሉ ሰበሰበ እህልንም በከተማቹ አደለበ፤ በየከተማይቱ ዙሪያ ያለውን የእርሻውን እህል ሁሉ በዚያው ከተተ። ዮሴፍም እንደ ባሕር አሸዋ እጅግ ብዙ የሆነ ስንዴን አከማቸ መሰፈርን እስኪተው ድረስ ሊሰፈር አልተቻለምና። ለዮሴፍም የሄልዮቱ ከተማ ካህን የዾጥፌራ ልጅ አስናት የወለደችለት ሁለት ልጆች የራብ ዘመን ገና ሳይመጣ ተወለዱለት። ዮሴፍም የበኵር ልጅን ስም ምናሴ ብሎ ጠራው እንዲህ ሲል እግዚአብሔር መከራዬን ሁሉ የአባቴንም ቤት አስረስኝ የሁለተኛውንም ስም ኤፍሬም ብሎ ጠራው እንዲህ ሲል፦ እግዚአብሔር በመከራዬ አገር አፈራኝ። በግብፅ ምድር የነበረውም የሰባቱ ዓመት ጥጋብ አለፈ፥ ዮሴፍም እንደ ተናገረ የሰባቱ ዓመት ራብ ጀመረ። በየአገሩም ሁሉ ራብ ሆነ በግብፅ ምድር ሁሉ ግን እህል ነበረ። የግብፅ ምድርም ሁሉ ተራበ ሕዝቡም ስለ እህል ወደ ፈርዖን ጮኽ ፈርዖንም የግብፅ ሰዎችን ሁሉ፦ ወደ ዮሴፍ ሂዱ፥ እርሱ ያላችሁንም ሁሉ አድርጉ አላቸው። በምድርም ሁሉ ላይ ራብ ሆነ ዮሴፍም እህል ያለበትን ጎተራ ሁሉ ከፍቶ ለግብፅ ሰዎች ሁሉ ይሸጥ ነበር፤ ራብም በግብፅ ምድር ጸንቶ ነበር። አገሮችም ሁሉ እህል ይገዙ ዘንድ ወደ ግብፅ ወደ ዮሴፍ መጡ በምድር ሁሉ ራብ እጅግ ጸንቶ ነበርና።

ዘፍጥረት 41:46-57 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ዮሴ​ፍም በግ​ብፅ ንጉሥ በፈ​ር​ዖን ፊት በቆመ ጊዜ ዕድ​ሜው ሠላሳ ዓመት ነበረ። ዮሴ​ፍም ከፈ​ር​ዖን ፊት ወጣ፤ የግ​ብፅ ምድ​ር​ንም ሁሉ ዞረ። በሰ​ባ​ቱም የጥ​ጋብ ዓመ​ታት ግብፅ ያስ​ገ​ኘ​ችው እህል ሁሉ ክምር ሆነ። በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ያለ​ውን የሰ​ባ​ቱን የጥ​ጋብ ዓመ​ታት እህል ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ እህ​ል​ንም በከ​ተ​ሞቹ አደ​ለበ፤ በየ​ከ​ተ​ማ​ይ​ቱም ዙሪያ ያለ​ውን የእ​ር​ሻ​ውን እህል ሁሉ በዚ​ያው ከተተ። ዮሴ​ፍም እንደ ባሕር አሸዋ እጅግ ብዙ የሆነ ስን​ዴን አከ​ማቸ፤ መስ​ፈር እስ​ኪ​ሳ​ና​ቸው ድረስ፤ ሊሰ​ፈር አል​ተ​ቻ​ለ​ምና። ለዮ​ሴ​ፍም የሄ​ል​ዮቱ ከተማ ካህን የጴ​ጤ​ፌራ ልጅ አስ​ኔት የወ​ለ​ደ​ች​ለት ሁለት ልጆች የራብ ዘመን ገና ሳይ​መጣ ተወ​ለ​ዱ​ለት። ዮሴ​ፍም የበ​ኵር ልጁን ስም ምናሴ ብሎ ጠራው፤ እን​ዲህ ሲል፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መከ​ራ​ዬን ሁሉ የአ​ባ​ቴ​ንም ቤት እን​ድ​ረሳ አደ​ረ​ገኝ፤” የሁ​ለ​ተ​ኛ​ው​ንም ስም ኤፍ​ሬም ብሎ ጠራው፤ እን​ዲህ ሲል፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ከ​ራዬ ሀገር አብ​ዝ​ቶ​ኛ​ልና።” በግ​ብፅ ምድር የነ​በ​ረ​ውም ሰባቱ የጥ​ጋብ ዓመት አለፈ፤ ዮሴ​ፍም እንደ ተና​ገረ ሰባቱ የራብ ዓመት መም​ጣት ጀመረ። በየ​ሀ​ገ​ሩም ሁሉ ራብ ሆነ፤ በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ግን እህል ነበረ። የግ​ብፅ ምድ​ርም ሁሉ ተራበ፤ ሕዝ​ቡም ስለ እህል ወደ ፈር​ዖን ጮኸ፤ ፈር​ዖ​ንም የግ​ብፅ ሰዎ​ችን ሁሉ፥ “ወደ ዮሴፍ ሂዱ፤ እርሱ ያላ​ች​ሁ​ንም ሁሉ አድ​ርጉ” አላ​ቸው። በም​ድ​ርም ሁሉ ላይ ራብ ሆነ፤ ዮሴ​ፍም እህል ያለ​በ​ትን ጎተራ ሁሉ ከፍቶ ለግ​ብፅ ሰዎች ሁሉ ይሸጥ ነበር። ሀገ​ሮ​ችም ሁሉ ከዮ​ሴፍ እህል ይገዙ ዘንድ ወደ ግብፅ ወጡ፤ በም​ድር ሁሉ ራብ እጅግ ጸንቶ ነበ​ርና።

ዘፍጥረት 41:46-57 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ዮሴፍ የግብጽ ንጉሥ ፈርዖንን ማገልገል ሲጀምር፣ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበር። ዮሴፍም ከፈርዖን ፊት ወጥቶ የግብጽን ምድር በሙሉ ዞረ። በሰባቱም የጥጋብ ዓመታት ምድሪቱ የተትረፈረፈ ሰብል ሰጠች። በእነዚያ ሰባት የጥጋብ ዓመታት፣ ዮሴፍ በግብጽ አገር የተገኘውን ምርት ሰብስቦ በየከተሞቹ አከማቸ፤ በእያንዳንዱ ከተማ ከየአቅራቢያው የተመረተውን እህል እንዲከማች አደረገ። ዮሴፍ ብዛቱ እንደ ባሕር አሸዋ የሚሆን የእህል ሰብል አከማቸ፤ ሰብሉ እጅግ ከመብዛቱ የተነሣ ልኩን መስፈርና መመዝገብ አልቻለም ነበር። ሰባቱ የራብ ዓመታት ከመምጣቱ በፊት፣ የሄልዮቱ ካህን የጶጥፌራ ልጅ አስናት ለዮሴፍ ሁለት ወንዶች ልጆች ወለደችለት። ዮሴፍም፣ “እግዚአብሔር መከራዬን ሁሉ፣ የአባቴንም ቤት እንድረሳ አድርጎኛል” በማለት የመጀመሪያ ልጁን ስም ምናሴ አለው። እንደዚሁም፣ “መከራ በተቀበልሁበት ምድር እግዚአብሔር ፍሬያማ አደረገኝ” ሲል ሁለተኛ ልጁን ኤፍሬም አለው። በግብጽ ምድር የነበረው ሰባቱ የጥጋብ ዘመን ዐለፈና ዮሴፍ አስቀድሞ እንደ ተናገረው የሰባቱ ዓመት የራብ ዘመን ጀመረ። ሌሎች አገሮች ሁሉ ሲራቡ፣ በመላው የግብጽ ምድር ግን ምግብ ነበር። ራቡ በመላው የግብጽ ምድር መስፋፋት ሲጀምር፣ ሕዝቡ ምግብ ይሰጠን በማለት ወደ ፈርዖን ጮኸ። ፈርዖንም ግብጻውያኑን፣ “ወደ ዮሴፍ ሂዱና የሚላችሁን አድርጉ” አላቸው። ራቡ በአገሩ ላይ እየተስፋፋ ስለ ሄደ፣ ዮሴፍ ጐተራዎቹን ከፍቶ እህሉ ለግብጻውያን እንዲሸጥ አደረገ፤ ምክንያቱም ራቡ በመላዪቱ ግብጽ ጸንቶ ነበር። ራቡ በመላው ዓለም ጸንቶ ስለ ነበር፣ የየአገሩ ሰዎች ሁሉ ከዮሴፍ ዘንድ እህል ለመሸመት ወደ ግብጽ ምድር መጡ።

ዘፍጥረት 41:46-57 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ዮሴፍም በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ፊት በቆመ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበረ። ዮሴፍም ከፈርዖን ፊት ወጣ የግብፅ ምድርንም ሁሉ ዞረ። በሰባቱም በጥጋብ ዓመታት የምድሪቱ ፍሬ ክምር ሆነ። በግብፅ ምድር ሁሉ ያለውን የሰባቱን ዓመታ እህል ሁሉ ሰበሰበ እህልንም በከተማቹ አደለበ፤ በየከተማይቱ ዙሪያ ያለውን የእርሻውን እህል ሁሉ በዚያው ከተተ። ዮሴፍም እንደ ባሕር አሸዋ እጅግ ብዙ የሆነ ስንዴን አከማቸ መሰፈርን እስኪተው ድረስ ሊሰፈር አልተቻለምና። ለዮሴፍም የሄልዮቱ ከተማ ካህን የዾጥፌራ ልጅ አስናት የወለደችለት ሁለት ልጆች የራብ ዘመን ገና ሳይመጣ ተወለዱለት። ዮሴፍም የበኵር ልጅን ስም ምናሴ ብሎ ጠራው እንዲህ ሲል እግዚአብሔር መከራዬን ሁሉ የአባቴንም ቤት አስረስኝ የሁለተኛውንም ስም ኤፍሬም ብሎ ጠራው እንዲህ ሲል፦ እግዚአብሔር በመከራዬ አገር አፈራኝ። በግብፅ ምድር የነበረውም የሰባቱ ዓመት ጥጋብ አለፈ፥ ዮሴፍም እንደ ተናገረ የሰባቱ ዓመት ራብ ጀመረ። በየአገሩም ሁሉ ራብ ሆነ በግብፅ ምድር ሁሉ ግን እህል ነበረ። የግብፅ ምድርም ሁሉ ተራበ ሕዝቡም ስለ እህል ወደ ፈርዖን ጮኽ ፈርዖንም የግብፅ ሰዎችን ሁሉ፦ ወደ ዮሴፍ ሂዱ፥ እርሱ ያላችሁንም ሁሉ አድርጉ አላቸው። በምድርም ሁሉ ላይ ራብ ሆነ ዮሴፍም እህል ያለበትን ጎተራ ሁሉ ከፍቶ ለግብፅ ሰዎች ሁሉ ይሸጥ ነበር፤ ራብም በግብፅ ምድር ጸንቶ ነበር። አገሮችም ሁሉ እህል ይገዙ ዘንድ ወደ ግብፅ ወደ ዮሴፍ መጡ በምድር ሁሉ ራብ እጅግ ጸንቶ ነበርና።

ዘፍጥረት 41:46-57 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ዮሴፍ የግብጽን ንጉሥ ፈርዖንን ማገልገል ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበር፤ ዮሴፍ ከቤተ መንግሥት ወጥቶ በመላው የግብጽ ምድር በመዘዋወር ጒብኝት ያደርግ ነበር፤ በሰባቱ የጥጋብ ዓመቶች ምድሪቱ እጅግ ብዙ ሰብል ሰጠች። በግብጽ አገር በእነዚያ ሰባት የጥጋብ ዓመቶች የተገኘውን ሰብል ሰብስቦ በየከተሞች አከማቸ፤ በየእያንዳንዱ ከተማ ያከማቸው እህል በዙሪያው ከሚገኙት እርሻዎች የተመረተ ነበር። በዚህ ዐይነት ዮሴፍ ብዛቱ እንደ ባሕር ዳር አሸዋ የሆነ እጅግ ብዙ እህል አከማቸ፤ እህሉ እጅግ ብዙ ከመሆኑ የተነሣ እየሰፈረ መጠኑን ለማወቅ የነበረውን ዕቅድ ተወ። ሰባቱ የራብ ዓመቶች ከመጀመራቸው በፊት፥ ዮሴፍ ከጶጢፌራ ልጅ ከአስናት ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ጶጢፌራ ኦን ተብሎ በሚጠራው ከተማ ካህን ነበረ። ዮሴፍ “እግዚአብሔር የደረሰብኝን መከራና ዘመዶቼን እንድረሳ አደረገኝ” በማለት የመጀመሪያ ልጁን ምናሴ ብሎ ጠራው፤ እንዲሁም “መከራ በተቀበልኩበት ምድር እግዚአብሔር ልጆች ሰጠኝ” በማለት ሁለተኛውን ልጅ ኤፍሬም ብሎ ጠራው። በግብጽ ምድር ጥጋብ የበዛባቸው ሰባቱ ዓመቶች ተፈጸሙ፤ ዮሴፍ አስቀድሞ እንደ ተናገረው፥ ሰባቱ የራብ ዓመቶች መግባት ጀመሩ፤ በሌሎች አገሮች ሁሉ ራብ ሆነ፤ ይሁን እንጂ በመላው የግብጽ ምድር በቂ ምግብ ነበር። ራብ በመላው ግብጽ ምድር እየተስፋፋ በሄደ ጊዜ፥ ሕዝቡ ወደ ፈርዖን ሄዶ “ምግብ ስጠን!” ብሎ ጮኸ። ፈርዖንም “ወደ ዮሴፍ ሂዱና እርሱ የሚላችሁን አድርጉ” ብሎ አዘዛቸው። ራቡ በመላው ግብጽ እየተስፋፋና እየበረታ ስለ ሄደ፥ ዮሴፍ ጐተራዎቹ ሁሉ ተከፍተው እህሉ ለግብጻውያን እንዲሸጥላቸው አደረገ። በዓለም ላይ ራብ ጸንቶ ስለ ነበር የልዩ ልዩ አገር ሕዝቦች ከዮሴፍ እህል ለመግዛት ወደ ግብጽ አገር መጡ።

ዘፍጥረት 41:46-57 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ዮሴፍ የግብጽ ንጉሥ ፈርዖንን ማገልገል ሲጀምር፥ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበር። ዮሴፍም ከፈርዖን ፊት ወጥቶ የግብጽን ምድር በሙሉ ዞረ። በሰባቱም የጥጋብ ዓመታት ምድሪቱ የተትረፈረፈ ሰብል ሰጠች። በእነዚያ ሰባት የጥጋብ ዓመታት፥ ዮሴፍ በግብጽ አገር የተገኘውን ምርት ሰብስቦ በየከተሞቹ አከማቸ፤ በእያንዳንዱ ከተማ ከየአቅራቢያው የተመረተውን እህል እንዲከማች አደረገ። ዮሴፍ ብዛቱ እንደ ባሕር አሸዋ የሚሆን የእህል ሰብል አከማቸ፤ ሰብሉ እጅግ ከመብዛቱ የተነሣ ልኩን መስፈርና መመዝገብ አልቻለም ነበር። ሰባቱ የራብ ዓመታት ከመምጣቱ በፊት፥ የሄልዮቱ ካህን የጶጥፌራ ልጅ አስናት ለዮሴፍ ሁለት ወንዶች ልጆች ወለደችለት። ዮሴፍም፥ “እግዚአብሔር መከራዬን ሁሉ፥ የአባቴንም ቤት እንድረሳ አድርጎኛል” በማለት የመጀመሪያ ልጁን ስም ምናሴ አለው። እንደዚሁም፥ “መከራ በተቀበልኩበት ምድር እግዚአብሔር ፍሬያማ አደረገኝ” ሲል ሁለተኛ ልጁን ኤፍሬም አለው። በግብጽ ምድር የነበረው ሰባቱ የጥጋብ ዘመን ዐለፈና ዮሴፍ አስቀድሞ እንደ ተናገረው የሰባቱ ዓመት የራብ ዘመን ጀመረ። ሌሎች አገሮች ሁሉ ሲራቡ፥ በመላው የግብጽ ምድር ግን ምግብ ነበር። ራቡ በመላው የግብጽ ምድር መስፋፋት ሲጀምር፥ ሕዝቡ ምግብ ይሰጠን በማለት ወደ ፈርዖን ጮኸ። ፈርዖንም ግብፃውያኑን፥ “ወደ ዮሴፍ ሂዱና የሚላችሁን አድርጉ” አላቸው። ራቡ በአገሩ ላይ እየተስፋፋ ስለ ሄደ፥ ዮሴፍ ጐተራዎቹን ከፍቶ እህሉ ለግብፃውያን እንዲሸጥ አደረገ፤ ምክንያቱም ራቡ በመላዪቱ ግብጽ ጸንቶ ነበር። ራቡ በመላው ዓለም ጸንቶ ስለ ነበር፥ የየአገሩ ሰዎች ሁሉ ከዮሴፍ ዘንድ እህል ለመሸመት ወደ ግብጽ ምድር መጡ።