ዘፍጥረት 41:41-46

ዘፍጥረት 41:41-46 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ፈር​ዖ​ንም ዮሴ​ፍን፥ “በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ላይ ሾም​ሁህ” አለው። ፈር​ዖን ቀለ​በ​ቱን ከእጁ አወ​ለቀ፤ በዮ​ሴ​ፍም እጅ አደ​ረ​ገው፤ የነጭ ሐር ልብ​ስ​ንም አለ​በ​ሰው፤ በአ​ን​ገ​ቱም የወ​ርቅ ዝር​ግ​ፍን አደ​ረ​ገ​ለት፤ የእ​ር​ሱም በም​ት​ሆን በሁ​ለ​ተ​ኛ​ይቱ ሰረ​ገላ አስ​ቀ​መ​ጠው፤ ስገዱ እያ​ለም በፊት በፊቱ አዋጅ ነጋሪ እን​ዲ​ሄድ አደ​ረገ፤ በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ላይም ሾመው። ፈር​ዖ​ንም ዮሴ​ፍን አለው፥ “እኔ ራሴ ፈር​ዖን ነኝ፤ በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ ያለ አንተ ማንም እጁን አያ​ንሣ።” ፈር​ዖ​ንም የዮ​ሴ​ፍን ስም “እስ​ፍ​ን​ቶ​ፎ​ኔህ” ብሎ ጠራው፤ የሄ​ል​ዮቱ ከተማ ካህን የጴ​ጤ​ፌራ ልጅ የም​ት​ሆን አስ​ኔ​ት​ንም ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ ሰጠው። ዮሴ​ፍም በግ​ብፅ ንጉሥ በፈ​ር​ዖን ፊት በቆመ ጊዜ ዕድ​ሜው ሠላሳ ዓመት ነበረ። ዮሴ​ፍም ከፈ​ር​ዖን ፊት ወጣ፤ የግ​ብፅ ምድ​ር​ንም ሁሉ ዞረ።

ዘፍጥረት 41:41-46 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ከዚያም፣ ፈርዖን ዮሴፍን፣ “በመላዪቱ የግብጽ ምድር ላይ ኀላፊ አድርጌሃለሁ” አለው። ፈርዖንም ባለማኅተሙን ቀለበት ከጣቱ አውልቆ በዮሴፍ ጣት ላይ አደረገው፤ እንዲሁም ከጥሩ የተልባ እግር የተሠራ ልብስ አለበሰው፤ በዐንገቱም የወርቅ ሐብል አጠለቀለት። በማዕርግ ከርሱ ሁለተኛ ሰው አድርጎ፣ በሠረገላ ላይ አስቀመጠው። ሰዎችም በፊቱ፣ “እጅ ንሡ” እያሉ ይጮኹ ነበር፤ በዚህ ሁኔታም በግብጽ ምድር ሁሉ ላይ ሾመው። ከዚህ በኋላ ፈርዖን ዮሴፍን፣ “እኔ ፈርዖን ነኝ፤ ሆኖም በመላዪቱ ግብጽ ያላንተ ትእዛዝ እጁንም ሆነ እግሩን ልውስ የሚያደርግ አይኖርም” አለው። ፈርዖንም ዮሴፍን ጸፍናት ፐዕናህ ብሎ ስም አወጣለት። እንዲሁም የሄልዮቱ ኦን ከተማ ካህን የጶጥፌራ ልጅ አስናትን አጋባው። ዮሴፍም በመላዪቱ የግብጽ ምድር ተዘዋወረ። ዮሴፍ የግብጽ ንጉሥ ፈርዖንን ማገልገል ሲጀምር፣ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበር። ዮሴፍም ከፈርዖን ፊት ወጥቶ የግብጽን ምድር በሙሉ ዞረ።

ዘፍጥረት 41:41-46 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እነሆ! አሁን በመላው የግብጽ ምድር ላይ አስተዳዳሪ አድርጌሃለሁ።” ንጉሡ የሥልጣኑ ምልክት ያለበትን የማኅተም ቀለበት ከጣቱ አውልቆ በዮሴፍ ጣት ላይ አደረገው፤ ከጥሩ ሐር የተሠራ ልብስ አለበሰው፤ በአንገቱም የወርቅ ሐብል አደረገለት። በንጉሡ ሁለተኛ ሠረገላ ላይ እንዲቀመጥ አደረገው፤ የንጉሡም የክብር ዘብ ከፊት ፊት እየሄደ “እጅ ንሡ! እጅ ንሡ!” ይል ነበር፤ ዮሴፍ በግብጽ ምድር ላይ አስተዳዳሪ ሆኖ የተሾመው በዚህ ዐይነት ነበር። ንጉሡም “እኔ ንጉሥ ብሆንም በግብጽ ምድር ሁሉ ላይ ያለ አንተ ፈቃድ ማንም ሰው እጁን ወይም እግሩን ማንቀሳቀስ አይችልም” አለው። ፈርዖን ለዮሴፍ “ጻፍናት ፐዕናሕ” የሚል መጠሪያ ስም አወጣለት፤ አስናት ተብላ የምትጠራውን የጶጢፌራን ልጅ በሚስትነት ሰጠው፤ ጶጢፌራ ኦን ተብሎ በሚጠራው ከተማ ካህን ነበር። ዮሴፍ የግብጽን ንጉሥ ፈርዖንን ማገልገል ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበር፤ ዮሴፍ ከቤተ መንግሥት ወጥቶ በመላው የግብጽ ምድር በመዘዋወር ጒብኝት ያደርግ ነበር፤

ዘፍጥረት 41:41-46 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ከዚያም፥ ፈርዖን ዮሴፍን “በመላዪቱ የግብጽ ምድር ላይ ኀላፊ አድርጌሃለሁ” አለው። ፈርዖንም ባለማኅተሙን ቀለበት ከጣቱ አውልቆ በዮሴፍ ጣት ላይ አደረገው፤ እንዲሁም ከጥሩ የተልባ እግር የተሠራ ልብስ አለበሰው፤ በዐንገቱም የወርቅ ሐብል አጠለቀለት። በማዕረግ ከእርሱ ሁለተኛ ሰው አድርጎ፥ በሠረገላ ላይ አስቀመጠው። ሰዎችም በፊቱ፥ “እጅ ንሡ” እያሉ ይጮኹ ነበር፤ በዚህ ሁኔታም በግብጽ ምድር ሁሉ ላይ ሾመው። ከዚህ በኋላ ፈርዖን ዮሴፍን፥ “እኔ ፈርዖን ነኝ፤ ሆኖም በመላዪቱ ግብጽ ያላንተ ትእዛዝ እጁንም ሆነ እግሩን ልውስ የሚያደርግ አይኖርም” አለው። ፈርዖንም ዮሴፍን “ጸፍናት ፐዕናህ” ብሎ ስም አወጣለት። እንዲሁም የሄልዮቱጠ ከተማ ካህን የጶጥፌራ ልጅ አስናትን አጋባው። ዮሴፍም በመላዪቱ የግብጽ ምድር ተዘዋወረ። ዮሴፍ የግብጽ ንጉሥ ፈርዖንን ማገልገል ሲጀምር፥ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበር። ዮሴፍም ከፈርዖን ፊት ወጥቶ የግብጽን ምድር በሙሉ ዞረ።