የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘፍጥረት 41:33-40

ዘፍጥረት 41:33-40 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

“እንግዲህ ፈርዖን ብልኅና አስተዋይ ሰው ፈልጎ፣ በመላው የግብጽ ምድር ላይ አሁኑኑ ይሹም። እንደዚሁም በሰባቱ የጥጋብ ዓመታት ከሚገኘው ምርት፣ አንድ ዐምስተኛው እንዲሰበሰብ የሚያደርጉ ኀላፊዎችን ይሹም። እነርሱም በሚመጡት የጥጋብ ዓመታት ከሚገኘው ምርት ሁሉ ይሰብስቡ፤ በፈርዖንም ሥልጣን ሥር ያከማቹ፤ ለምግብ እንዲሆኑም በየከተማው ይጠበቁ። የሚከማቸው እህል፣ ወደ ፊት በግብጽ አገር ላይ ለሚመጣው የሰባት ዓመት ራብ መጠባበቂያ ይሁን፤ በዚህም ሁኔታ አገሪቱ በራብ አትጠፋም።” ዕቅዱንም ፈርዖንና ሹማምቱ ሁሉ መልካም ሆኖ አገኙት። ፈርዖንም፣ “የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት እንደዚህ ያለ ሰው ማንን ልናገኝ እንችላለን?” ብሎ ጠየቃቸው። ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ስለ ገለጠልህ፣ እንደ አንተ ያለ አስተዋይና ብልኅ ሰው የለም። አንተ በቤተ መንግሥቴ የበላይ ትሆናለህ፤ ሕዝቤም ሁሉ ለሥልጣንህ ይገዛል፤ እኔ ከአንተ የምበልጠው በዙፋኔ ብቻ ይሆናል።”

ዘፍጥረት 41:33-40 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

አሁ​ንም ብል​ህና ዐዋቂ ሰውን ለአ​ንተ ፈልግ፤ በግ​ብፅ ምድር ላይም ሹመው። ፈር​ዖን በግ​ብፅ ምድር ላይ ሹሞ​ችን ይሹም፤ በሰ​ባ​ቱም የጥ​ጋብ ዓመ​ታት ከሚ​ገ​ኘው ፍሬ በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ከአ​ም​ስት እጅ አን​ደ​ኛ​ውን ይው​ሰድ። የሚ​መ​ጡ​ትን የመ​ል​ካ​ሞ​ቹን ሰባት ዓመ​ታት እህ​ላ​ቸ​ውን ያከ​ማቹ፤ ስን​ዴ​ው​ንም ከፈ​ር​ዖን እጅ በታች ያኑሩ፤ እህ​ሎ​ችም በከ​ተ​ሞች ይጠ​በቁ። በግ​ብፅ ምድር ስለ​ሚ​ሆ​ነው ስለ ሰባቱ ዓመ​ታት ራብ እህሉ ለሀ​ገሩ ሁሉ ተጠ​ብቆ ይኑር፥ ምድ​ሪ​ቱም በራብ አት​ጠ​ፋም።” ነገ​ሩም ፈር​ዖ​ን​ንና ሰዎ​ቹን ሁሉ ደስ አሰ​ኛ​ቸው፤ ፈር​ዖ​ንም ሎሌ​ዎ​ቹን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “በውኑ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ያለ​በ​ትን እን​ደ​ዚህ ያለ ሰውን እና​ገ​ኛ​ለን?” ፈር​ዖ​ንም ዮሴ​ፍን አለው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ሁሉ ገል​ጦ​ል​ሃ​ልና ከአ​ንተ ይልቅ ብል​ህና ዐዋቂ ሰው የለም። አንተ በቤቴ ላይ ተሾም፤ ሕዝ​ቤም ሁሉ ለቃ​ልህ ይታ​ዘዝ፤ እኔም ከዙ​ፋኔ በቀር ከአ​ንተ የም​በ​ል​ጥ​በት የለም።”

ዘፍጥረት 41:33-40 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

“እንግዲህ ጥበብና ማስተዋል ያለውን ሰው መርጠህ በአገሪቱ አስተዳዳሪ አድርገህ ሹመው፤ በሰባቱ የጥጋብ ዓመቶች አንድ አምስተኛውን ሰብል የሚሰበስቡ ሰዎችን መርጠህ ሹም። እነርሱ በሚመጡት የጥጋብ ዓመቶች ትርፍ የሆነውን ሰብል ሁሉ እንዲሰበስቡ እዘዛቸው፤ በየከተማውም እህል በጐተራ እንዲያከማቹና እንዲጠብቁት ሥልጣን ስጣቸው። ይህም የሚከማቸው እህል በግብጽ ምድር ላይ ወደፊት በሚመጡት ሰባት የራብ ዓመቶች ለአገሪቱ መጠባበቂያ ይሆናል፤ በዚህ ሁኔታ አገሪቱ በራብ ከመጐዳት ትድናለች።” ዕቅዱም ለፈርዖንና ለባለሟሎቹ ሁሉ መልካም ሆኖ ታያቸው፤ ንጉሡም “የእግዚአብሔር መንፈስ ካደረበት ከዮሴፍ የተሻለ ሰው ከቶ አናገኝም” አላቸው። ስለዚህ ንጉሡ ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “ይህን ሁሉ የገለጠልህ እግዚአብሔር ነው፤ ከማንኛውም ሰው ይልቅ አስተዋይና ብልኅ መሆንህ የተረጋገጠ ነው፤ ስለዚህ አንተን በአገሬ ላይ አስተዳዳሪ አድርጌ እሾምሃለሁ፤ ሕዝቡም ሁሉ ይታዘዝሃል፤ በሥልጣንም ከእኔ በቀር የሚበልጥህ የለም።

ዘፍጥረት 41:33-40 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

እንግዲህ ፈርዖን ብልኅና አስተዋይ ሰው ፈልጎ፥ በመላው የግብጽ ምድር ላይ አሁኑኑ ይሹም። እንደዚሁም በሰባቱ የጥጋብ ዓመታት ከሚገኘው ምርት፥ አንድ አምስተኛው እንዲሰበሰብ የሚያደርጉ ኀላፊዎችን ይሹም። እነርሱም በሚመጡት የጥጋብ ዓመታት ከሚገኘው ምርት ሁሉ ይሰብስቡ፤ በፈርዖንም ሥልጣን ሥር ያከማቹ፤ ለምግብ እንዲሆኑም በየከተማው ይጠበቁ። የሚከማቸው እህል፥ ወደ ፊት በግብጽ አገር ላይ ለሚመጣው የሰባት ዓመት ራብ መጠባበቂያ ይሁን፤ በዚህም ሁኔታ አገሪቱ በራብ አትጠፋም።” ዕቅዱንም ፈርዖንና ሹማምንቱ ሁሉ መልካም ሆኖ አገኙት። ፈርዖንም፥ “የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት እንደዚህ ያለ ሰው ማንን ልናገኝ እንችላለን?” ብሎ ጠየቃቸው። ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ስለ ገለጠልህ፥ እንዳንተ ያለ አስተዋይና ብልኅ ሰው የለም። አንተ በቤተ መንግሥቴ የበላይ ትሆናለህ፤ ሕዝቤም ሁሉ ለሥልጣንህ ይገዛል፤ እኔ ከአንተ የምበልጠው በዙፋኔ ብቻ ይሆናል።”