ዘፍጥረት 35:11-12
ዘፍጥረት 35:11-12 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እግዚአብሔርም አለው፥ “አምላክህ እኔ ነኝ፤ ብዛ፤ ተባዛም፤ ሕዝብና የአሕዛብ ማኅበር ከአንተ ይሆናል፤ ነገሥታትም ከጕልበትህ ይወጣሉ። ለአብርሃምና ለይስሐቅም የሰጠኋትን ምድር ለአንተ፥ ከአንተም በኋላ ለዘርህ እሰጣለሁ።”
Share
ዘፍጥረት 35 ያንብቡዘፍጥረት 35:11-12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ደግሞም እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ያዕቆብን እንዲህ አለው፤ “እኔ ሁሉን ማድረግ የሚችል አምላክ ነኝ፤ ብዛ ተባዛ፤ ሕዝብና የሕዝቦች ማኅበር ከአንተ ይወጣሉ፤ ነገሥታትም ከአብራክህ ይከፈላሉ። ለአብርሃምና ለይስሐቅ የሰጠኋትን ምድር ለአንተ እሰጥሃለሁ፤ ከአንተም በኋላ ይህችኑ ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ።”
Share
ዘፍጥረት 35 ያንብቡዘፍጥረት 35:11-12 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እግዚአብሔር አለው፦ ሁሉን ቻይ አምላክ እኔ ነኝ ብዛ ተባዛም ሕዝብና የአሕዛብ ማኅበር ከአንተ ይሆናል ነገሥታትም ከጕልበትህ ይወጣሉ። ለአብርሃም ለይስሐቅም የሰጠኍትን ምድር ለአንተ እሰጣለሁ ከአንተም በኍላ ለዘርህ ምድሪቱን እሰጠለሁ።
Share
ዘፍጥረት 35 ያንብቡ