የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘፍጥረት 32:24-32

ዘፍጥረት 32:24-32 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ያዕ​ቆብ ግን ለብ​ቻው ቀረ፤ አንድ ሰውም እስከ ንጋት ድረስ ይታ​ገ​ለው ነበር። እን​ዳ​ላ​ሸ​ነ​ፈ​ውም ባየ ጊዜ የጭ​ኑን ሹልዳ ያዘው፤ የያ​ዕ​ቆ​ብም የጭኑ ሹልዳ ሲታ​ገ​ለው ደነ​ዘዘ። እን​ዲ​ህም አለው፥ “ሊነጋ ጎሕ ቀድ​ዶ​አ​ልና ልቀ​ቀኝ።” እር​ሱም “ከአ​ል​ባ​ረ​ክ​ኸኝ አል​ለ​ቅ​ህም” አለው። እን​ዲ​ህም አለው፥ “ስምህ ማን ነው?” እር​ሱም፥ “ያዕ​ቆብ ነኝ” አለው። አለ​ውም፥ “ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ስምህ እስ​ራ​ኤል ይባል እንጂ ያዕ​ቆብ አይ​ባል፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና ከሰው ጋር ታግ​ለህ በር​ት​ተ​ሃ​ልና።” ያዕ​ቆ​ብም፥ “ስም​ህን ንገ​ረኝ” ብሎ ጠየ​ቀው። እር​ሱም፥ “ስሜን ለምን ትጠ​ይ​ቃ​ለህ? ድንቅ ነውና” አለው። በዚ​ያም ስፍራ ባረ​ከው። ያዕ​ቆ​ብም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፊት ለፊት አየሁ፤ ሰው​ነ​ቴም ዳነች” ሲል የዚ​ያን ቦታ ስም “ራእየ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” ብሎ ጠራው። ራእየ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በተወ ጊዜ ፀሐይ ወጣ​ች​በት። እር​ሱም በጭኑ ምክ​ን​ያት ያነ​ክስ ነበር። ስለ​ዚ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እስከ ዛሬ ድረስ የወ​ር​ችን ሹልዳ አይ​በ​ሉም፤ የያ​ዕ​ቆ​ብን ጭን ይዞ የወ​ር​ቹን ሹልዳ አደ​ን​ዝ​ዞ​አ​ልና።

ዘፍጥረት 32:24-32 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ያዕቆብ ግን ብቻውን እዚያው ቀረ፤ አንድ ሰውም እስኪነጋ ድረስ ሲታገለው ዐደረ። ያም ሰው ያዕቆብን ታግሎ ማሸነፍ እንዳቃተው በተረዳ ጊዜ፣ የጭኑን ሹልዳ ነካው፤ በግብግቡም የያዕቆብ ጭን ከመጋጠሚያው ላይ ተናጋ። በዚያን ጊዜ ሰውየው፣ “እንግዲህ መንጋቱ ስለሆነ ልቀቀኝና ልሂድ” አለው። ያዕቆብም፣ “ካልባረክኸኝ አልለቅህም” አለው። ሰውየውም፣ “ስምህ ማን ነው?” አለው። እርሱም፣ “ያዕቆብ ነው” አለ። ሰውየውም፣ “ከእግዚአብሔርም (ኤሎሂም)፣ ከሰዎችም ጋር ታግለህ አሸንፈሃልና ከእንግዲህ ስምህ እስራኤል እንጂ፣ ያዕቆብ አይባልም” አለው። ያዕቆብም፣ “እባክህ ስምህን ንገረኝ” ብሎ ጠየቀው። ሰውየውም፣ “ስሜን ለማወቅ ለምን ፈለግህ?” አለው፤ በዚያም ስፍራ ባረከው። ስለዚህ ያዕቆብ፣ “እግዚአብሔርን (ኤሎሂም) ፊት ለፊት አይቼ እንኳ ሕይወቴ ተርፋለች” ሲል፣ የዚያን ቦታ ስም ጵኒኤል አለው። ጵኒኤልንም እንዳለፈ ፀሓይ ወጣችበት፤ እርሱም በጭኑ ምክንያት ያነክስ ነበር። ከዚህም የተነሣ የእስራኤል ልጆች እስከ ዛሬ ድረስ ሹልዳን ከጭኑ ጋር የሚያገናኘውን ሥጋ አይበሉም፤ ምክንያቱም በጭኑ መጋጠሚያ ላይ ያለው የያዕቆብ ሹልዳ ተነክቶ ነበር።

ዘፍጥረት 32:24-32 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እርሱ ግን በስተማዶ ለብቻው ቀረ፤ ከዚህ በኋላ ሌሊቱ እስኪነጋ ድረስ አንድ ሰው ሲታገለው ዐደረ። ያ ሰው ያዕቆብን በትግል ማሸነፍ እንዳቃተው ባየ ጊዜ የጭኑን ሹልዳ መታው፤ ያዕቆብም በሚታገልበት ጊዜ ጭኑ ከመገጣጠሚያው ላይ ተለያየ፤ ከዚህ በኋላ ሰውየው “ሌሊቱ ሊነጋ ስለ ሆነ ልቀቀኝ” አለ። ያዕቆብም “ካልባረክኸኝ አለቅህም” አለው። ሰውየውም “ስምህ ማን ነው?” አለው። “ስሜ ያዕቆብ ነው” አለው። ሰውየውም፥ “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ ያዕቆብ አይባልም፤ ከእግዚአብሔርም ከሰውም ጋር ታግለህ አሸንፈሃል፤ ስለዚህ ስምህ ‘እስራኤል’ ይባላል” አለው። ያዕቆብም “አንተስ ስምህ ማን ነው?” አለው። ሰውየውም “ስሜን ለማወቅ የምትፈልገው ለምንድን ነው?” አለውና ያዕቆብን ባረከው። ያዕቆብም “እኔ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አይቼ እነሆ፥ በሕይወት እገኛለሁ” አለ። በዚህም ምክንያት ያንን ቦታ “ጵንኤል” ብሎ ጠራው። ያዕቆብ ከጵንኤል ተነሥቶ ሲሄድ ፀሐይ ወጥታ ነበር፤ በጭኑም ሕመም ምክንያት ያነክስ ነበር። ያዕቆብ ከሰውየው ጋር ሲታገል ሰውየው ሹልዳውን መቶት ስለ ነበር እስራኤላውያን እስከ ዛሬ ድረስ በጭን መጋጠሚያ ላይ ያለውን የሹልዳ ሥጋ አይበሉም።

ዘፍጥረት 32:24-32 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ያዕቆብ ግን ለብቻው ቀረ፥ አንድ ሰውም እስከ ንጋት ድረስ ሲታገለው አደረ። ያ ሰው ያዕቆብን እንዳላሸነፈውም ባየ ጊዜ፥ የጭኑን ሹልዳ ነካው፥ ያዕቆብም ሲታገለው የጭኑ ሹልዳ ከመገጣጠሚያው ላይ ተለያየ፤። ከዚያ ሰውየው፦ “የንጋት ጎህ ሊቀድ ነውና ልቀቀኝ” አለው። እርሱም፦ “ካልባረክኸኝ አልለቅህም” አለው። ሰውየውም፦ “ስምህ ማን ነው?” አለው። እርሱም፦ “ያዕቆብ ነኝ” አለው። ሰውየውም፦ “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ ያዕቆብ አይባልም፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ከሰውም ጋር ታግለህ አሸንፈሃልና እስራኤል ይባላል” አለው። ያዕቆብም፦ “ልለምንህ፥ ስምህን ንገረኝ” ብሎ ጠየቀው። እርሱም፦ “ስሜን ለምን ትጠይቃለህ?” አለው። በዚያም ስፍራ ባረከው። ስለዚህ ያዕቆብ፦ “እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፥ ሆኖም ሕይወቴ ተርፋለች” ሲል የዚያን ቦታ ስም “ጵኒኤል” ብሎ ጠራው። ጵኒኤልንም ሲያልፍ ፀሐይ ወጣችበት፥ እርሱም በጭኑ ምክንያት ያነክስ ነበር። ስለዚህም የያዕቆብን ጭን ይዞ የወርቹን ሹልዳ ነክቶታልና፥ የእስራኤል ልጆች እስከ ዛሬ ድረስ የወርችን (በጭን መጋጠሚያ ላይ ያለውን) ሹልዳ አይበሉም።