ዘፍጥረት 3:11-13
ዘፍጥረት 3:11-13 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እግዚአብሔርም አለው፥ “ዕራቁትህን እንደሆንህ ማን ነገረህ? ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍ በውኑ በላህን?” አዳምም አለ፥ “ከእኔ ጋር እንድትሆን የሰጠኸኝ ሴት እርስዋ ከዛፉ ሰጠችኝና በላሁ።” እግዚአብሔር አምላክም ሴቲቱን፥ “ይህን ለምን አደረግሽ?” አላት። ሴቲቱም አለች፥ “እባብ አሳተኝና በላሁ።”
Share
ዘፍጥረት 3 ያንብቡዘፍጥረት 3:11-13 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እግዚአብሔርም፣ (ያህዌ)፣ “ዕራቍትህን መሆንህን ማን ነገረህ? ‘ከእርሱ እንዳትበላ’ ብዬ ካዘዝሁህ ዛፍ በላህን?” አለው። አዳምም፣ “ይህች ከእኔ ጋር እንድትኖር የሰጠኸኝ ሴት፣ እርሷ ከዛፉ ፍሬ ሰጠችኝና በላሁ” አለ። እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) ሴቲቱን፣ “ይህ ያደረግሽው ምንድን ነው?” አላት። እርሷም፣ “እባብ አሳሳተኝና በላሁ” አለች።
Share
ዘፍጥረት 3 ያንብቡዘፍጥረት 3:11-13 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እግዚእብሔርም አለው፤ ዕራቁትህን እንደ ሆንህ ማን ነገርህ? ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍ በውኑ በላህን? አዳምም አለ፦ ከእኔ ጋር እንድትሆን የስጠኽኝ ሴት እርስዋ ከዛፉ ሰጠችኝና በላሁ። እግዚአብሔር አምላክም ሴቲቱን፦ ይህ ያደረግሽው ምንድር ነው? አላት። ሴቲቱም አለች፦ እባብ አሳተኝና በላሁ።
Share
ዘፍጥረት 3 ያንብቡ