ዘፍጥረት 3:10-14
ዘፍጥረት 3:10-14 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
አዳምም አለ፥ “በገነት ስትመላለስ ድምፅህን ሰማሁ፤ ዕራቁቴንም ስለሆንሁ ፈራሁ፤ ተሸሸግሁም።” እግዚአብሔርም አለው፥ “ዕራቁትህን እንደሆንህ ማን ነገረህ? ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍ በውኑ በላህን?” አዳምም አለ፥ “ከእኔ ጋር እንድትሆን የሰጠኸኝ ሴት እርስዋ ከዛፉ ሰጠችኝና በላሁ።” እግዚአብሔር አምላክም ሴቲቱን፥ “ይህን ለምን አደረግሽ?” አላት። ሴቲቱም አለች፥ “እባብ አሳተኝና በላሁ።” እግዚአብሔር አምላክም እባቡን አለው፥ “ይህን ስላደረግህ ከእንስሳት ሁሉ፥ ከምድር አራዊትም ሁሉ ተለይተህ አንተ የተረገምህ ሁን ፤ በደረትህና በሆድህም ትሄዳለህ፤ በሕይወትህም ዘመን ሁሉ አፈርን ትበላለህ።
ዘፍጥረት 3:10-14 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
አዳምም፣ “ድምፅህን በአትክልቱ ስፍራ ሰማሁ፤ ዕራቍቴን ስለሆንሁ ፈራሁ፤ ተሸሸግሁም” ብሎ መለሰ። እግዚአብሔርም፣ (ያህዌ)፣ “ዕራቍትህን መሆንህን ማን ነገረህ? ‘ከእርሱ እንዳትበላ’ ብዬ ካዘዝሁህ ዛፍ በላህን?” አለው። አዳምም፣ “ይህች ከእኔ ጋር እንድትኖር የሰጠኸኝ ሴት፣ እርሷ ከዛፉ ፍሬ ሰጠችኝና በላሁ” አለ። እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) ሴቲቱን፣ “ይህ ያደረግሽው ምንድን ነው?” አላት። እርሷም፣ “እባብ አሳሳተኝና በላሁ” አለች። እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) እባብን እንዲህ አለው፤ “ይህን ስለ ሠራህ፣ “ከከብቶችና ከዱር እንስሳት ሁሉ ተለይተህ የተረገምህ ሁን፤ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፣ በደረትህ እየተሳብህ ትሄዳለህ፤ ዐፈርም ትበላለህ።
ዘፍጥረት 3:10-14 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እርሱም አለ፦ በገነት ድምጽህን ሰማሁ፤ ዕራቁቴንም ስለ ሆንሁ ፈራሁ፤ ተሸሸግሁም። እግዚእብሔርም አለው፤ ዕራቁትህን እንደ ሆንህ ማን ነገርህ? ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍ በውኑ በላህን? አዳምም አለ፦ ከእኔ ጋር እንድትሆን የስጠኽኝ ሴት እርስዋ ከዛፉ ሰጠችኝና በላሁ። እግዚአብሔር አምላክም ሴቲቱን፦ ይህ ያደረግሽው ምንድር ነው? አላት። ሴቲቱም አለች፦ እባብ አሳተኝና በላሁ። እግዚአብሔር አምላክም እባቡን አለው፦ ይህን ስላደረገህ ከእንስሳት ከምድር አራዊትም ሁሉ ተለይተህም ትሄዳለህ፤ አፈርንም በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ትበላለህ።
ዘፍጥረት 3:10-14 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
አዳምም “በአትክልቱ ቦታ ውስጥ የአንተን ድምፅ ሰማሁ፤ እራቁቴንም ስለ ሆንኩ በመፍራት ተደበቅሁ” አለ። እግዚአብሔርም “እራቁትህን እንደ ሆንክ ማን ነገረህ? አትብላ ካልኩህ ዛፍ ፍሬ ወስደህ በላህን?” አለው። አዳምም “ይህች አብራኝ እንድትኖር የሰጠኸኝ ሴት ፍሬውን ከዛፉ ወስዳ ሰጠችኝና በላሁ” አለ። እግዚአብሔር አምላክም ሴቲቱን “ይህ ያደረግሽው ምንድን ነው?” ብሎ ጠየቃት። እርስዋም “እባብ አታለለኝና በላሁ” አለች። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ እባቡን እንዲህ አለው፦ “ይህን በማድረግህ ከእንስሶችና ከአራዊት ሁሉ ተለይተህ የተረገምክ ሁን፤ ከዛሬ ጀምሮ በደረትህ እየተሳብክ ሂድ፤ ዕድሜህን ሙሉ ዐፈር ብላ፤
ዘፍጥረት 3:10-14 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
እርሱም፥ “በገነት ድምጽህን ሰማሁ፥ ዕራቁቴንም ስለ ሆንኩ ፈራሁ፥ ተሸሸግሁም።” አለ። እግዚእብሔርም፦ “ዕራቁትህን እንደሆንህ ማን ነገረህ? እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍ በውኑ ከእርሱ በላህን?” አለው። አዳምም፦ “ከእኔ ጋር እንድትሆን የሰጠኽኝ ሴት እርሷ ከዛፉ ሰጠችኝና በላሁ” አለ። ጌታ እግዚአብሔርም ሴቲቱን፦ “ይህ ያደረግሽው ምንድነው?” አላት። ሴቲቱም፥ “እባብ አሳተኝና በላሁ” አለች። ጌታ እግዚአብሔርም እባቡን አለው፦ “ይህን በማድረግህ፥ ከእንስሳት ከምድር አራዊትም ሁሉ ተለይተህ አንተ የተረገምህ ትሆናለህ፤ በሆድህም ትሄዳለህ፥ በሕይወትህም ዘመን ሁሉ አፈርን ትበላለህ።