ዘፍጥረት 3:10-12
ዘፍጥረት 3:10-12 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
አዳምም አለ፥ “በገነት ስትመላለስ ድምፅህን ሰማሁ፤ ዕራቁቴንም ስለሆንሁ ፈራሁ፤ ተሸሸግሁም።” እግዚአብሔርም አለው፥ “ዕራቁትህን እንደሆንህ ማን ነገረህ? ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍ በውኑ በላህን?” አዳምም አለ፥ “ከእኔ ጋር እንድትሆን የሰጠኸኝ ሴት እርስዋ ከዛፉ ሰጠችኝና በላሁ።”
Share
ዘፍጥረት 3 ያንብቡዘፍጥረት 3:10-12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
አዳምም፣ “ድምፅህን በአትክልቱ ስፍራ ሰማሁ፤ ዕራቍቴን ስለሆንሁ ፈራሁ፤ ተሸሸግሁም” ብሎ መለሰ። እግዚአብሔርም፣ (ያህዌ)፣ “ዕራቍትህን መሆንህን ማን ነገረህ? ‘ከእርሱ እንዳትበላ’ ብዬ ካዘዝሁህ ዛፍ በላህን?” አለው። አዳምም፣ “ይህች ከእኔ ጋር እንድትኖር የሰጠኸኝ ሴት፣ እርሷ ከዛፉ ፍሬ ሰጠችኝና በላሁ” አለ።
Share
ዘፍጥረት 3 ያንብቡዘፍጥረት 3:10-12 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እርሱም አለ፦ በገነት ድምጽህን ሰማሁ፤ ዕራቁቴንም ስለ ሆንሁ ፈራሁ፤ ተሸሸግሁም። እግዚእብሔርም አለው፤ ዕራቁትህን እንደ ሆንህ ማን ነገርህ? ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍ በውኑ በላህን? አዳምም አለ፦ ከእኔ ጋር እንድትሆን የስጠኽኝ ሴት እርስዋ ከዛፉ ሰጠችኝና በላሁ።
Share
ዘፍጥረት 3 ያንብቡ