ዘፍጥረት 27:5-13
ዘፍጥረት 27:5-13 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ርብቃም ይስሐቅ ለልጁ ለዔሳው እንደዚህ ሲነግር ትሰማ ነበር። ዔሳውም ለአባቱ አደን ሊያድን ወደ ምድረ በዳ ሄደ። ርብቃም ታናሹ ልጅዋን ያዕቆብን እንዲህ አለችው፦ “እነሆ፥ አባትህ ለወንድምህ ለዔሳው፦ እንዲህ ሲለው ሰማሁ፤ ‘ሂድና ከአደንኸው መብል አዘጋጅተህ አምጣልኝ፤ ሳልሞትም በልች በእግዚአብሔር ፊት ልባርክህ።’ አሁንም ልጄ ሆይ፥ እኔ እንደማዝዝህ ስማኝ፤ ወደ በጎቻችን ሄደህ ሁለት መልካም ጠቦቶች አምጣልኝ፤ እነርሱንም ለአባትህ እንደሚወደው መብል አደርጋቸዋለሁ፤ ለአባትህም ሳይሞት እንዲባርክህ፥ ይበላ ዘንድ ትወስድለታለህ።” ያዕቆብም እናቱን ርብቃን፥ “እነሆ ዔሳው ወንድሜ ጠጕራም ሰው ነው፥ እኔ ግን ለስላሳ ነኝ፤ ምናልባት አባቴ ቢዳስሰኝ በፊቱ እንደምንቀው እሆናለሁ፤ መርገምን በላዬ አመጣለሁ፤ በረከትንም አይደለም።” እናቱም አለችው፥ “ልጄ ሆይ፥ መርገምህ በእኔ ላይ ይሁን፥ ቃሌን ብቻ ስማኝ፤ ሂድና ያልሁህን አምጣልኝ።”
ዘፍጥረት 27:5-13 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ይስሐቅ ለልጁ የተናገረውን ርብቃ ትሰማ ስለ ነበር፣ ዔሳው የታዘዘውን ለማምጣት ለዐደን እንደ ወጣ፣ ርብቃ ለልጇ ለያዕቆብ እንዲህ አለችው፤ “አባትህ ዔሳውን፣ ‘ከመሞቴ በፊት በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት እንድመርቅህ፣ ጥሩ ጣዕም ያለው ምግብ እንድበላ አዘጋጅልኝ።’ ሲለው ሰምቻለሁ፤ ልጄ ሆይ፤ እንግዲህ የምነግርህን በጥሞና ስማኝ፤ የምልህንም አድርግ። ተነሣና ወደ መንጋው ሄደህ ሁለት ፍርጥም ያሉ የፍየል ጠቦቶች አምጣልኝ፤ እኔም አባትህ የሚወድደውን ዐይነት ምግብ አዘጋጅለታለሁ፤ እርሱም ከመሞቱ በፊት እንዲመርቅህ ይዘህለት ግባና ይብላ።” ያዕቆብም እናቱን ርብቃን እንዲህ አላት፤ “ወንድሜ ዔሳው ሰውነቱ ጠጕራም ነው፤ የእኔ ገላ ግን ለስላሳ ነው። ታዲያ፣ አባቴ ቢዳስሰኝ እንዳታለልሁት ያውቃል፤ ይህ ከሆነ ደግሞ፣ በምርቃት ፈንታ ርግማን አተርፋለሁ ማለት ነው።” እናቱም፣ “ልጄ ሆይ፤ የአንተ ርግማን በእኔ ላይ ይድረስ፤ ግድ የለህም፤ እንደ ነገርሁህ ሄደህ ጠቦቶቹን አምጣልኝ” አለችው።
ዘፍጥረት 27:5-13 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ርብቃም ይስሐቅ ለልጁ ለዔሳው ሲነግር ትሰማ ነበር። ዔሳውም አደን አድኖ ሊያመጣ ወደ ምድረ በዳ ሄደ። ርብቃም ልጅዋን ያዕቆብን እንዲይ አለችው፦ እነሆ አባትህ ለወንድምህ ለዔሳው፦ አደን አድነህ አምጣልኝ ሳልሞትም በልቼ በእግዚአብሔር ፊት እንድባርክህ የጣፈጠ መብል አድርግልኝ ብሎ ሲነግረው ሰማሁ። አሁንም ልጄ ሆይ እኔ በማዝዝህ ነገር ስማኝ ወደ መንጋ ሄደህ ሁለት መልካካም ጠቦቶች አምጣልኝ እነርሱን፥ ጣፋጭ መብል ለአባትህ እንደሚወደው አደርጋለሁ፤ ለአባትህም ሳይሞት እንዲባርክህ ይበላ ዘንድ ታገባለታለህ። ያዕቆብም ርብቃን እናቱን አላት፦ እነሆ ዔሳው ወንድሜ ጠጕራ፥ ሰው ነው እኔ ግን ለስላሳ ነኝ አባቴ ቢዳስሰኝ በፊቱ እንደሚዘብት እሆናለሁ መርገምንም በላዬ አመጣለሂ በረከትን አይደለም። እናቱም አለችው፦ ልጄ ሆይ፥ መርገምህ በእኔ ላይ ይሁን ቃሌን ብቻ ስማኝ ሂድና አምጣልኝ።
ዘፍጥረት 27:5-13 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ይስሐቅ ለልጁ ለዔሳው የሚለውን ሁሉ ርብቃ ትሰማ ነበር፤ ስለዚህ ዔሳው ወደ አደን ከሄደ በኋላ፥ ርብቃ ልጅዋን ያዕቆብን “አባትህ ወንድምህን ዔሳውን እንዲህ ሲለው ሰማሁ፤ ‘አውሬ አድነህ ሥጋ አምጣልኝ፤ ልክ እንደምወደው አድርገህ የጣፈጠ ምግብ ሥራልኝ፤ ሳልሞትም በእግዚአብሔር ፊት እመርቅሃለሁ፤’ አሁንም ልጄ ሆይ፥ የምነግርህን አድምጥ፤ የማዝህንም አድርግ፤ አባትህ እንደሚወደው አጣፍጬ ጥሩ ምግብ እንድሠራለት፥ ወደ መንጋዎች ሂድና ሁለት የሰቡ የፍየል ጠቦቶችን አምጣልኝ፥ አንተም ያዘጋጀሁትን ምግብ እንዲበላ ለአባትህ ወስደህ ታቀርብለታለህ፤ በዚህ ዐይነት አባትህ ከመሞቱ በፊት ይመርቅሃል።” ያዕቆብ ግን እናቱን ርብቃን “የወንድሜ የዔሳው ገላ ጠጒራም ነው፤ የእኔ ገላ ግን ምንም ጠጒር የሌለው ለስላሳ ነው፤ ምናልባት አባቴ ቢዳስሰኝና እንዳታለልኩት ቢያውቅ በምርቃት ፈንታ ርግማን እንደማተርፍ ታውቂ የለምን?” አላት። እናቱም “ልጄ ሆይ፥ የአንተ ርግማን በእኔ ላይ ይሁን፤ አሁንም እንደ ነገርኩህ አድርግ፤ ሄደህ ጠቦቶቹን አምጣልኝ” አለችው።
ዘፍጥረት 27:5-13 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ርብቃም ይስሐቅ ለልጁ ለዔሳው ሲነግር ትሰማ ነበር። ዔሳውም አደን አድኖ ሊያመጣ ወደ ምድረ በዳ ሄደ። ርብቃም ልጇን ያዕቆብን እንዲህ አለችው፥ “እነሆ አባትህ ለወንድምህ ለዔሳው፦ ‘አደን አድነህ አምጣልኝ፥ ሳልሞትም በልቼ በጌታ ፊት እንድባርክህ የጣፈጠ መብል ሥራልኝ፤’ ብሎ ሲነግረው ሰማሁ። አሁንም፥ ልጄ ሆይ፥ እኔ የማዝዝህ ነገር ስማኝ፥ ወደ መንጋ ሄደህ ሁለት መልካም ጠቦቶች አምጣልኝ፥ እነርሱንም ጣፋጭ መብል ለአባትህ እንደሚወደው አደርጋለሁ፥ ለአባትህም፥ ሳይሞት እንዲባርክህ፥ ይበላ ዘንድ ታስገባለታለህ።” ያዕቆብም ርብቃን እናቱን አላት፦ “እነሆ ዔሳው ወንድሜ ጠጉራም ሰው ነው፥ እኔ ግን ለስላሳ ነኝ፥ ምናልባት አባቴ ቢዳስሰኝ በፊቱ እንደሚዘብት እሆናለሁ፥ መርገምንም በላዬ አመጣለሁ፥ በረከትን አይደለም።” እናቱም አለችው፦ “ልጄ ሆይ፥ መርገምህ በእኔ ላይ ይሁን፥ ቃሌን ብቻ ስማኝ፥ ሂድና አምጣልኝ።”