ዘፍጥረት 26:24
ዘፍጥረት 26:24 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በዚያችም ሌሊት እግዚአብሔር ተገለጠለት፤ እንዲህም አለው፥ “እኔ የአባትህ የአብርሃም አምላክ ነኝ፤ አትፍራ፤ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና፤ እባርክሃለሁ፤ ስለ አባትህ ስለ አብርሃም ዘርህን አበዛዋለሁ።”
ዘፍጥረት 26:24 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በዚያም ሌሊት እግዚአብሔር ተገለጠለትና፣ “እኔ የአባትህ የአብርሃም አምላክ ነኝ፤ ከአንተ ጋራ ነኝና አትፍራ፤ እባርክሃለሁ፤ ስለ አገልጋዬም ስለ አብርሃም ስል ዘርህን አበዛለሁ” አለው።
ዘፍጥረት 26:24 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በዚያችም ሌሊት እግዚአብሔር ተገለጠለት፥ እንዲህም አለው፦ እኔ የአባትህ የአብርሃም አምላክ ነኝ አትፍራ፥ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና እባርክሃለሁ ስለ ባሪያዬ ስለ አብርሃም ዘርህን አበዛለሁ።