የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘፍጥረት 26:1-6

ዘፍጥረት 26:1-6 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በም​ድ​ርም ቀድሞ በአ​ብ​ር​ሃም ዘመን ከሆ​ነው ራብ ሌላ ራብ ሆነ፤ ይስ​ሐ​ቅም ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤም ንጉሥ ወደ አቤ​ሜ​ሌክ ወደ ጌራራ ሄደ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተገ​ለ​ጠ​ለት፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “ወደ ግብፅ አት​ው​ረድ፤ እኔ በም​ልህ ምድር ተቀ​መጥ። በዚ​ህች ምድር ተቀ​መጥ፤ ከአ​ንተ ጋርም እሆ​ና​ለሁ፤ እባ​ር​ክ​ሃ​ለ​ሁም፤ ይህ​ችን ምድር ሁሉ ለአ​ን​ተም፥ ለዘ​ር​ህም እሰ​ጣ​ለ​ሁና፥ ለአ​ባ​ት​ህም ለአ​ብ​ር​ሃም የማ​ል​ሁ​ለ​ትን መሐላ ከአ​ንተ ጋር አጸ​ና​ለሁ። ዘር​ህ​ንም እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት አበ​ዛ​ዋ​ለሁ፤ ይህ​ች​ንም ምድር ሁሉ ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ለሁ፤ የም​ድ​ርም ሕዝ​ቦች ሁሉ በዘ​ርህ ይባ​ረ​ካሉ፤ አባ​ትህ አብ​ር​ሃም ቃሌን ሰም​ቶ​አ​ልና፤ ትእ​ዛ​ዜ​ንና ፍር​ዴን፥ ሥር​ዐ​ቴ​ንና ሕጌ​ንም ጠብ​ቆ​አ​ልና።” ይስ​ሐ​ቅም በጌ​ራራ ተቀ​መጠ። የዚ​ያም ስፍራ ሰዎች ስለ ሚስቱ ስለ ርብቃ ጠየ​ቁት፤ እር​ሱም፥ “እኅቴ ናት” አላ​ቸው፤