የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘፍጥረት 21:1-9

ዘፍጥረት 21:1-9 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገ​ረው ሣራን ጐበ​ኛት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገ​ረው ለሣራ አደ​ረ​ገ​ላት። ሣራም ፀነ​ሰች፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በተ​ና​ገ​ረው ወራት ለአ​ብ​ር​ሃም በእ​ር​ጅ​ናዋ ወንድ ልጅን ወለ​ደ​ች​ለት። አብ​ር​ሃ​ምም ሣራ የወ​ለ​ደ​ች​ለ​ትን የል​ጁን ስም ይስ​ሐቅ ብሎ ጠራው። አብ​ር​ሃ​ምም ልጁን ይስ​ሐ​ቅን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን ገረ​ዘው። አብ​ር​ሃ​ምም ልጁ ይስ​ሕቅ በተ​ወ​ለ​ደ​ለት ጊዜ መቶ ዓመቱ ነበረ። ሣራም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ አሰ​ኘኝ፤ ይህን የሚ​ሰማ ሁሉ በእኔ ምክ​ን​ያት ደስ ይሰ​ኛ​ልና” አለች። ደግ​ሞም ሣራ “በእ​ር​ጅ​ናዋ የወ​ለ​ደ​ች​ውን ሕፃን እን​ድ​ታ​ጠባ ለአ​ብ​ር​ሃም ማን በነ​ገ​ረው?” አለች። ሕፃ​ኑም አደገ፤ ጡት​ንም አስ​ጣ​ሉት፤ አብ​ር​ሃ​ምም ይስ​ሐ​ቅን ጡት ባስ​ጣ​ለ​በት ቀን ትልቅ ግብ​ዣን አደ​ረገ። ሣራም ግብ​ፃ​ዊቱ አጋር ለአ​ብ​ር​ሃም የወ​ለ​ደ​ች​ለ​ትን ልጅ ይስ​ማ​ኤ​ልን ከል​ጅዋ ከይ​ስ​ሐቅ ጋር ሲጫ​ወት አየ​ችው።

ዘፍጥረት 21:1-9 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ስለዚህ እግዚአብሔር በተናገረው መሠረት ለሣራ መልካም በማድረግ የገባውን ቃል ኪዳን ፈጸመላት። ስለዚህም ፀንሳ በእርጅናው ጊዜ ለአብርሃም ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ ልጁም የተወለደው “በዚህ ጊዜ ይወለዳል” ብሎ እግዚአብሔር በተናገረበት ጊዜ ነው። አብርሃም ሚስቱ ሣራ የወለደችለትን ልጅ “ይስሐቅ” ብሎ ስም አወጣለት፤ ይስሐቅ ከተወለደ ከስምንት ቀን በኋላ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት አብርሃም ገረዘው። ይስሐቅ በተወለደ ጊዜ አብርሃም መቶ ዓመት ሆኖት ነበር። ሣራ “እግዚአብሔር ደስታና ሳቅ አመጣልኝ፤ ስለዚህ ይህን ነገር የሚሰማ ሁሉ ከእኔ ጋር ይስቃል” አለች። ቀጥላም “ ‘ሣራ ለአብርሃም ልጅ ወልዳ ታጠባለች’ ብሎ የሚናገር ከቶ ማን ነበር? አሁን ግን እነሆ በእርጅናው ዘመን ወንድ ልጅ ወለድኩለት” አለች። ልጁም አድጎ ጡት መጥባት ተወ፤ ጡት ባስጣሉበትም ቀን አብርሃም ታላቅ ግብዣ አደረገ። ግብጻዊትዋ አጋር ለአብርሃም የወለደችለት እስማኤል ከዕለታት አንድ ቀን ሣራ ከልጅዋ ከይስሐቅ ጋር ሲጫወት አየችው፤