ዘፍጥረት 2:23-25
ዘፍጥረት 2:23-25 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ያን ጊዜም አዳም አለ፥ “ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፤ ሥጋዋም ከሥጋዬ ናት፤ እርስዋ ከባልዋ ተገኝታለችና ሚስት ትሁነኝ።” ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፤ ሚስቱንም ይከተላል ፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ። አዳምና ሚስቱም ዕራቁታቸውን ነበሩ፤ አይተፋፈሩም ነበር።
ያጋሩ
ዘፍጥረት 2 ያንብቡዘፍጥረት 2:23-25 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
አዳምም እንዲህ አለ፤ “እነሆ፤ ይህች ዐጥንት ከዐጥንቴ፣ ሥጋም ከሥጋዬ ናት። ከወንድ ተገኝታለችና ‘ሴት’ ትባል።” ስለዚህ ሰው ከአባቱና ከእናቱ ተለይቶ ከሚስቱ ጋራ ይጣመራል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ። አዳምና ሚስቱ፣ ሁለቱም ዕራቍታቸውን ነበሩ፤ ይሁን እንጂ አይተፋፈሩም ነበር።
ያጋሩ
ዘፍጥረት 2 ያንብቡዘፍጥረት 2:23-25 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
አዳምም አለ፤ ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፤ ሥጋም ከሥጋዬ ናት፤ እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል። ስለዚህ ሰዉ አባቱንና እናቱን ይተዋል፤ በሚስቱም ይጣበቃ፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ። አዳምና ሚስቱ ሁለቱም ዕራቁታቸውን ነበሩ፤ አይተፋፈሩም ነበር።
ያጋሩ
ዘፍጥረት 2 ያንብቡ