ዘፍጥረት 1:28-29
ዘፍጥረት 1:28-29 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እግዚአብሔርም ባረካቸው፤ እንዲህም አላቸው፥ “ብዙ፤ ተባዙ፤ ምድርንም ሙሉአት፤ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሣዎችንና የምድር አራዊትን፥ የሰማይ ወፎችንና እንስሳትንም ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው።” እግዚአብሔርም አለ፥ “እነሆ፥ መብል ይሆናችሁ ዘንድ በየዘሩ የሚዘራውንና የሚበቅለውን፥ በምድር ሁሉ ላይ የምትዘሩትን የእህል ፍሬ፥ ዘሩ በውስጡ ያለውን ቡቃያ፥ በየፍሬውም የሚዘራውን ዛፍ ሁሉ ሰጠኋችሁ።
ዘፍጥረት 1:28-29 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እግዚአብሔርም (ኤሎሂም)፣ “ብዙ ተባዙ፤ ምድርን ሙሏት፤ ግዟትም፤ የባሕርን ዓሦች፣ የሰማይን ወፎች፣ እንዲሁም በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትን ሕያዋን ፍጡራንን ሁሉ ግዟቸው” ብሎ ባረካቸው። እግዚአብሔርም (ኤሎሂም) እንዲህ አለ፤ “በምድር ላይ ያሉትን ዘር የሚሰጡ ተክሎችን ሁሉ፣ በፍሬያቸው ውስጥ ዘር ያለባቸውን ዛፎች ሁሉ ምግብ ይሆኑላችሁ ዘንድ ሰጥቻችኋለሁ።
ዘፍጥረት 1:28-29 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እግዚአብሔርም ባረካቸዉ፤ እንዲህም አላቸው ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሉአት፤ ግዙአትም የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትም ሁሉ ግዙአቸዉ። እግዚአብሔርም አለ፤ እነሆ መብል ይሆናችሁ ዘንድ በምድር ፊት ሁሉ ላይ ዘሩ በእርሱ ያለዉን ሐመለማል ሁሉ የዛፍን ፍሬ የሚያፈራዉንና ዘር ያለውንም ዛፍ ሁሉ ሰጠኋችሁ፤
ዘፍጥረት 1:28-29 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እግዚአብሔርም “ብዙ፤ ተባዙ፤ ዘራችሁ ምድርን ይሙላ፤ ምድርም በቊጥጥራችሁ ሥር ትሁን፤ በባሕር ውስጥ በሚኖሩ ዓሣዎች፥ በሰማይ በሚበርሩ ወፎችና በምድር ላይ በሚንቀሳቀሱ ሕያዋን ፍጥረቶች ሁሉ ላይ ሥልጣን ይኑራችሁ” ብሎ ባረካቸው። እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “ምግብ እንዲሆኑአችሁ በምድር ገጽ ላይ የሚገኙትን የእህል አዝርዕትንና ዘር በውስጡ ያለውን ፍራፍሬ የሚያስገኙ ተክሎችን ሁሉ ሰጥቻችኋለሁ።