ገላትያ 4:4-7
ገላትያ 4:4-7 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ነገር ግን ቀጠሮው በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ልጁን ላከ፤ ከሴትም ተወለደ፤ የኦሪትንም ሕግ ፈጸመ። እኛ የልጅነትን ክብር እንድናገኝ በኦሪት የነበሩትን ይዋጅ ዘንድ። ልጆች እንደ መሆናችሁ መጠን እግዚአብሔር አባ አባቴ ብላችሁ የምትጠሩትን የልጁን መንፈስ በልባችሁ አሳደረ። እንኪያስ እናንተ ልጆች ናችሁ እንጂ ባሮች አይደላችሁም፤ ልጆች ከሆናችሁም በኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ወራሾች ናችሁ።
ገላትያ 4:4-7 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ነገር ግን የተወሰነው ዘመን በደረሰ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን፣ ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤ ይህም የሆነው የልጅነትን መብት እናገኝ ዘንድ ከሕግ በታች ያሉትን ለመዋጀት ነው። ልጆችም ስለ ሆናችሁ እግዚአብሔር፣ “አባ፣ አባት” ብሎ የሚጮኽ የልጁን መንፈስ ወደ ልባችን ላከ። ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም፤ ልጅም ስለ ሆንህ፣ እግዚአብሔር ወራሽ አድርጎሃል።
ገላትያ 4:4-7 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤ እንደ ልጆች እንሆን ዘንድ፥ ከሕግ በታች ያሉትን ይዋጅ ዘንድ። ልጆችም ስለ ሆናችሁ እግዚአብሔር አባ አባት ብሎ የሚጮኽ የልጁን መንፈስ በልባችሁ ውስጥ ላከ። ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም፤ ልጅም ከሆንህ ደግሞ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ወራሽ ነህ።
ገላትያ 4:4-7 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ነገር ግን የተወሰነው ዘመን በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ልጁን ላከልን፤ እርሱ ከሴት ተወለደ፤ ለሕግም ታዛዥ ሆነ። ይህንንም ያደረገው ከሕግ ሥር ያሉትን ለመዋጀትና እኛም የእግዚአብሔር ልጆች እንድንሆን ለማድረግ ነው። የእግዚአብሔር ልጆች በመሆናችንም እግዚአብሔርን “አባባ” እያለ የሚጠራውን የልጁን መንፈስ ወደ ልባችን ላከ። ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም፤ ልጅ ከሆንክም የእግዚአብሔር ወራሽ ነህ።
ገላትያ 4:4-7 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
የዘመኑ ሙላት በመጣ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግ ሥር የተወለደውን ልጁን ላከ፤ ይህም ከሕግ በታች ያሉትን ለመዋጀት፥ እኛም ልጅነትን እንድናገኝ ነው። ልጆችም ስለ ሆናችሁ እግዚአብሔር “አባ አባት” ብሎ የሚጮኽ የልጁን መንፈስ ወደ ልባችን ላከ። ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባርያ አይደለህም፤ ልጅም ከሆንህ ደግሞ በእግዚአብሔር በኩል ወራሽ ነህ።