የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሕዝቅኤል 37:15-28

ሕዝቅኤል 37:15-28 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ “አንተ የሰው ልጅ ሆይ! አንድ በትር ውሰ​ድና፦ ይሁ​ዳ​ንና ባል​ን​ጀ​ሮ​ቹን፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች በላዩ ጻፍ፤ ሌላም በትር ውሰ​ድና፦ የኤ​ፍ​ሬም በትር ለዮ​ሴ​ፍና ለባ​ል​ን​ጀ​ሮቹ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሁሉ ብለህ በላዩ ጻፍ። አንድ በት​ርም እን​ዲ​ሆኑ አን​ዱን ከሁ​ለ​ተ​ኛው ጋር ለአ​ንተ አጋ​ጥም፤ በእ​ጅ​ህም ውስጥ አንድ ይሁኑ። የሕ​ዝ​ብ​ህም ልጆች፦ ይህ የም​ታ​ደ​ር​ገው ነገር ምን ማለት እንደ ሆነ አት​ነ​ግ​ረ​ን​ምን? ብለው በተ​ና​ገ​ሩህ ጊዜ፥ አንተ፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በኤ​ፍ​ሬም እጅ ያለ​ውን የዮ​ሴ​ፍን በትር ባል​ን​ጀ​ሮ​ቹ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ነገ​ዶች እወ​ስ​ዳ​ለሁ፤ ከእ​ር​ሱም ከይ​ሁዳ በትር ጋር አጋ​ጥ​ማ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አንድ በት​ርም አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ጄም ውስጥ አንድ ይሆ​ናሉ በላ​ቸው። የም​ት​ጽ​ፍ​ባ​ቸ​ውም በት​ሮች በፊ​ታ​ቸው በእ​ጅህ ውስጥ ይሆ​ናሉ። አን​ተም እን​ዲህ ትላ​ቸ​ዋ​ለህ፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከገ​ቡ​ባ​ቸው ከአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል እወ​ስ​ዳ​ለሁ፤ ከስ​ፍ​ራም ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ምድር አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በም​ድ​ርም ላይ በእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ላይ አንድ ሕዝብ አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ፥ አንድ ንጉ​ሥም በሁ​ላ​ቸው ላይ ይነ​ግ​ሣል፤ ከዚያ ወዲያ ሁለት ሕዝብ አይ​ሆ​ኑም፤ ከዚያ ወዲ​ያም ሁለት መን​ግ​ሥት ሆነው አይ​ለ​ያ​ዩም። ከዚያ ወዲ​ያም በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና በር​ኵ​ሰ​ታ​ቸው፥ በመ​ተ​ላ​ለ​ፋ​ቸ​ውም ሁሉ አይ​ረ​ክ​ሱም፤ ኀጢ​አ​ትም ከሠ​ሩ​ባት ዐመፅ ሁሉ አድ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አነ​ጻ​ቸ​ው​ማ​ለሁ፤ ሕዝ​ብም ይሆ​ኑ​ኛል፤ እኔም አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ። “ባሪ​ያ​ዬም ዳዊት በላ​ያ​ቸው ንጉሥ ይሆ​ናል፤ ለሁ​ሉም አንድ እረኛ ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል፤ በፍ​ር​ዴም ይሄ​ዳሉ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ይጠ​ብ​ቃሉ፤ ያደ​ር​ጓ​ት​ማል። አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም በኖ​ሩ​ባት፤ ለባ​ሪ​ያዬ ለያ​ዕ​ቆብ በሰ​ጠ​ኋት ምድር ይኖ​ራሉ፤ እነ​ር​ሱና ልጆ​ቻ​ቸው፥ የልጅ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ሩ​ባ​ታል፤ ባሪ​ያ​ዬም ዳዊት ለዘ​ለ​ዓ​ለም አለቃ ይሆ​ና​ቸ​ዋል። የሰ​ላ​ምም ቃል ኪዳን ከእ​ነ​ርሱ ጋር አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ቃል ኪዳን ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል፤ እኔም እባ​ር​ካ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አበ​ዛ​ቸ​ው​ማ​ለሁ፤ መቅ​ደ​ሴ​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አኖ​ራ​ለሁ። ማደ​ሪ​ያ​ዬም በላ​ያ​ቸው ላይ ይሆ​ናል፤ እኔም አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝብ ይሆ​ኑ​ኛል። መቅ​ደ​ሴም ለዘ​ለ​ዓ​ለም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው በሆነ ጊዜ፥ እኔ እስ​ራ​ኤ​ልን የም​ቀ​ድ​ሰው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ አሕ​ዛብ ያው​ቃሉ።”

ሕዝቅኤል 37:15-28 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ “የሰው ልጅ ሆይ፤ አንድ በትር ወስደህ፣ ‘የይሁዳና የተባባሪዎቹ የእስራኤላውያን’ ብለህ ጻፍበት። ከዚያም ሌላ በትር ወስደህ፣ ‘የኤፍሬም፣ የዮሴፍና የተባባሪዎቹ የእስራኤል ቤት ሁሉ’ ብለህ ጻፍበት። እንደ አንድ በትር ይሆኑ ዘንድ በእጅህ ላይ አጋጥመህ ያዛቸው። “የአገርህ ልጆች፣ ‘ይህስ ምን ማለትህ እንደ ሆነ አትነግረንምን?’ ብለው ሲጠይቁህ፣ እንዲህ በላቸው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በኤፍሬም እጅ ያለውን የዮሴፍን በትርና የተባባሪዎቹን የእስራኤላውያንን ነገድ በትር እወስዳለሁ፤ ከይሁዳ በትር ጋር አጋጥሜ አንድ ወጥ በትር አደርጋቸዋለሁ፤ እነርሱም በእጄ አንድ በትር ይሆናሉ።’ የጻፍህባቸውን በትሮች ከፊት ለፊታቸው ያዝ፤ እንዲህም በላቸው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ እስራኤላውያንን ከሄዱባቸው አሕዛብ መካከል አወጣቸዋለሁ፤ ከየስፍራው ሰብስቤ ወደ ገዛ ምድራቸው እመልሳቸዋለሁ። በምድሪቱ በእስራኤል ተራሮች ላይ አንድ ሕዝብ አደርጋቸዋለሁ፤ በሁሉም ላይ አንድ ንጉሥ ይነግሣል፤ ከእንግዲህም ሁለት ሕዝብ አይሆኑም፤ መንግሥታቸውም ከሁለት አይከፈልም። በጣዖቶቻቸው፣ በአጸያፊ ምስሎቻቸው ወይም በማንኛውም ኀጢአት ራሳቸውን አያረክሱም፤ ነገር ግን እኔን በመተው ከሠሩት ኀጢአት ሁሉ አድናቸዋለሁ፤ አነጻቸዋለሁም። እነርሱ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ። “ ‘ባሪያዬ ዳዊት በላያቸው ይነግሣል፤ ሁሉም አንድ እረኛ ይኖራቸዋል፤ ሕጌን ይከተላሉ፤ ሥርዐቴንም በጥንቃቄ ይጠብቃሉ። አባቶቻችሁ በኖሩበት፣ ለባሪያዬ ለያዕቆብ በሰጠሁት ምድር ይኖራሉ። በዚያም እነርሱ፣ ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው ለዘላለም ይኖራሉ፤ ባሪያዬ ዳዊትም ለዘላለም ንጉሣቸው ይሆናል። ከእነርሱም ጋር የሰላም ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ ቃል ኪዳኑም የዘላለም ይሆናል። አጸናቸዋለሁ፤ አበዛቸዋለሁ፤ መቅደሴንም በመካከላቸው ለዘላለም አኖራለሁ። ማደሪያዬ ከእነርሱ ጋር ይሆናል፤ አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ። መቅደሴም ለዘላለም በመካከላቸው በሚሆንበት ጊዜ፣ አሕዛብ እኔ እግዚአብሔር እስራኤልን እንደ ቀደስሁ ያውቃሉ።’ ”

ሕዝቅኤል 37:15-28 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ አንተ፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ አንድ በትር ውሰድና፦ ለይሁዳና ለባንጀሮቹ ለእስራኤል ልጆች ብለህ በላዩ ጻፍ፥ ሌላም በትር ውሰድና፦ የኤፍሬም በትር ለዮሴፍና ለባልንጀሮቹ ለእስራኤል ቤት ሁሉ ብለህ በላዩ ጻፍ። አንድ በትርም እንዲሆኑ አንዱን ከሁለተኛው ጋር ለአንተ አጋጥም፥ በእጅህም ውስጥ አንድ ይሁኑ። የሕዝብህም ልጆች፦ ይህ የምታደርገው ነገር ምን ማለት እንደሆነ አትነግረንምን? ብለው በተናገሩህ ጊዜ፥ አንተ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በኤፍሬም እጅ ያለውን የዮሴፍን በትር ባልንጀሮቹንም የእስራኤልን ነገዶች እወስዳለሁ፥ ከእርሱም ከይሁዳ በትር ጋር አጋጥማቸዋለሁ አንድ በትርም አደርጋቸዋለሁ፥ በእጄም ውስጥ አንድ ይሆናሉ በላቸው። የምትጽፍባቸውም በትሮች በዓይናቸው ፊት በእጅህ ውስጥ ይሆናሉ። አንተም እንዲህ ትላቸዋለህ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የእስራኤልን ልጆች ከሄዱባቸው ከአሕዛብ መካከል እወስዳለሁ ከስፍራም ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ ወደ ገዛ ምድራቸውም አመጣቸዋለሁ፥ በምድርም ላይ በእስራኤል ተራሮች ላይ አንድ ሕዝብ አደርጋቸዋለሁ፥ አንድ ንጉሥም በሁላቸው ላይ ይነግሣል፥ ከዚያ ወዲያ ሁለት ሕዝብ አይሆኑም፥ ከዚያ ወዲያም ሁለት መንግሥቶች ሆነው አይለዩም። ከዚያ ወዲያም በጣዖቶቻቸውና በርኵሰታቸው በመተላለፋቸውም ሁሉ አይረክሱም፥ ኃጢአትም ከሠሩባት ዓመፅ ሁሉ አድናቸዋለሁ አነጻቸውማለሁ፥ ሕዝብም ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ። ባሪያዬም ዳዊት ንጉሥ ይሆናቸዋል፥ ለሁሉም አንድ እረኛ ይሆንላቸዋል፥ በፍርዴም ይሄዳሉ ትእዛዜንም ይጠብቃሉ ያደርጓትማል። አባቶቻችሁም በኖሩባት ለባሪያዬ ለያዕቆብ በሰጠኋት ምድር ይኖራሉ፥ እነርሱና ልጆቻቸው የልጅ ልጆቻቸውም ለዘላለም ይኖሩባታል፥ ባሪያዬም ዳዊት ለዘላለም አለቃ ይሆናቸዋል። የሰላምም ቃል ኪዳን ከእነርሱ ጋር አደርጋለሁ፥ የዘላለምም ቃል ኪዳን ይሆንላቸዋል፥ እኔም እባርካቸዋለሁ አበዛቸውማለሁ መቅደሴንም ለዘላለም በመካከላቸው አኖራለሁ። ማደሪያዬም በላያቸው ላይ ይሆናል፥ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል። መቅደሴም ለዘላለም በመካከላቸው በሆነ ጊዜ፥ እኔ እስራኤልን የምቀድሰው እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ አሕዛብ ያውቃሉ።

ሕዝቅኤል 37:15-28 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! አንድ በትር ወስደህ ‘በእርሱ ላይ ለይሁዳና ከእርሱ ጋር ለተባበሩ እስራኤላውያን’ ብለህ ጻፍ፤ ከዚያም ሌላ በትር ወስደህ በእርሱ ላይ ‘ለዮሴፍ ማለት ለኤፍሬምና ከእርሱ ጋር ለተባበሩ እስራኤላውያን’ ብለህ ጻፍ። ከዚህ በኋላ በእጅህ አንድ ይሆኑ ዘንድ ሁለቱን በትሮች በአንድነት አገጣጥመህ ያዛቸው። ሕዝብህም ይህ ምን መሆኑን እንድትነግራቸው በሚጠይቁህ ጊዜ፥ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ብሏል ብለህ ንገራቸው፦ በኤፍሬም እጅ ያለውን የዮሴፍን ከእነርሱ ጋር የተባበሩትን የእስራኤልን በትር ወስጄ አንድ በትር እንዲሆኑ ከይሁዳ በትር ጋር አጋጥማቸውና በእጄ አንድ ይሆናሉ። “የጻፍክባቸውንም ሁለቱን በትሮች በእጅህ ይዘህ ሕዝቡ እንዲያዩአቸው አድርግ። እኔ ልዑል እግዚአብሔር ሕዝቤን ሁሉ ከተበተኑባቸው ሕዝቦች መካከል በአንድነት ሰብስቤ ወደገዛ ምድራቸው መልሼ የማመጣቸው መሆኔን ንገራቸው። በእስራኤል ምድርና በተራሮችዋ አንድ መንግሥት እንዲሆኑ አደርጋለሁ፤ ሁሉንም በአንድነት የሚያስተዳድር አንድ ንጉሥ ይኖራቸዋል፤ ዳግመኛ ሁለት ሕዝብ አይሆኑም፤ መንግሥታቸውም በሁለት አይከፈልም። ዳግመኛ በጣዖቶቻቸው፥ በአጸያፊ ነገሮቻቸው፥ ወይም በሌሎች ኃጢአቶቻቸው ራሳቸውን አያረክሱም፤ ከወደቁበት ክሕደት አውጥቼ አነጻቸዋለሁ። በዚያን ጊዜ እነርሱ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ። እንደ አገልጋዬ እንደ ዳዊት ያለ ንጉሥ ይኖራቸዋል፤ በአንድ መሪ ሥር ተጠቃለው ሕጎቼንና ሥርዓቴን በታማኝነት ይፈጽማሉ። ለአገልጋዬ ለያዕቆብ በሰጠሁትና የቀድሞ አባቶቻቸውም በኖሩባት ምድር ይኖራሉ፤ በዚያችም ምድር እነርሱና ልጆቻቸው ዘሮቻቸውም ሳይቀሩ ለዘለዓለም ይኖራሉ፤ እንደ አገልጋዬ እንደ ዳዊት ያለ ንጉሥ በእነርሱ ላይ ለዘለዓለም ይነግሣል። ከእነርሱ ጋር የሰላም ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ ያም ቃል ኪዳን ዘለዓለማዊ ነው፤ እነርሱንም እንደገና መሥርቼ የሕዝቡን ቊጥር አበዛለሁ፤ ቤተ መቅደሴንም ለዘለዓለም ጸንቶ በሚቈይበት ስፍራ በምድራቸው አኖራለሁ። እኔም በዚያ ከእነርሱ ጋር እኖራለሁ፤ እኔ አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ። ቤተ መቅደሴ በመካከላቸው ለዘለዓለም እንዲኖር በማደርግበት ጊዜ፤ ለእኔ እስራኤልን ለራሴ የተለየ ሕዝብ የማደርግ መሆኔን አሕዛብ ያውቃሉ።”

ሕዝቅኤል 37:15-28 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ አንተ የሰው ልጅ ሆይ፥ አንድ በትር ለራስህ ውሰድ፥ በላዩ “ለይሁዳና ለተባባሪዎቹ የእስራኤል ልጆች” ብለህ ጻፍበት፤ ሌላም በትር ውሰድ፦ በላዩም “የኤፍሬም በትር ለሆነው ለዮሴፍና ለተባባሪዎቹ፥ ለመላው የእስራኤል ቤት” ብለህ ጻፍበት። በእጅህ ውስጥ አንድ በትር እንዲሆኑ አንዱ ከአንዱ ጋር አጋጥመህ ያዛቸው። የሕዝብህ ልጆች፦ “እነዚህ ለአንተ ምን እንደ ሆኑ አትነግረንምን?” ሲሉህ፥ እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በኤፍሬም እጅና በተባባሪዎቹ በእስራኤል ነገዶች ያለውን የዮሴፍን በትር እወስዳለሁ፥ ከይሁዳ በትር ጋር አስቀምጣቸዋለሁ፥ አንድ በትር አደርጋቸዋለሁ፥ በእጄም አንድ ይሆናሉ። በላያቸው የምትጽፍባቸው በትሮች በዓይናቸው ፊት በእጅህ ይሆናሉ። አንተም እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የእስራኤልን ልጆች ከሄዱባቸው ሕዝቦች መካከል እወስዳለሁ፥ ከየስፍራውም እሰበስባቸዋለሁ፥ ወደ ገዛ ምድራቸውም አመጣቸዋለሁ። በምድሪቱ በእስራኤል ተራሮች ላይ አንድ ሕዝብ አደርጋቸዋለሁ፥ አንድ ንጉሥ ለሁሉም ንጉሥ ይሆናል፤ ዳግመኛ ሁለት ሕዝብ አይሆኑም፥ ከዚያ ወዲያም ሁለት መንግሥቶች ሆነው አይከፈሉም። በጣዖቶቻቸው፥ በአጸያፊ ነገሮቻቸውና በመተላለፋቸው ሁሉ ዳግመኛ አይረክሱም፤ ኃጢአት ከሠሩባቸው መኖሪያ ቤቶቻቸው ሁሉ አድናቸዋለሁ፥ አነጻቸዋለሁም፤ እነርሱ ለእኔ ሕዝብ ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ። አገልጋዬ ዳዊት ንጉሥ ይሆናቸዋል፤ ሁሉም አንድ እረኛ ይኖራቸዋል፤ በፍርዴ ይሄዳሉ፥ ትእዛዜን ይጠብቃሉ ይፈጽሟቸዋልም። ለአገልጋዬ ለያዕቆብ በሰጠኋት፥ አባቶቻችሁም በኖሩባት ምድር ይኖራሉ፤ እነርሱ፥ ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው ለዘለዓለም በእርሷ ይኖራሉ፤ አገልጋዬ ዳዊት ለዘለዓለም ልዑላቸው ይሆናል። የሰላም ቃል ኪዳን ከእነርሱ ጋር አደርጋለሁ፥ የዘለዓለም ቃል ኪዳን ይሆንላቸዋል፤ አጸናቸዋለሁ፥ አበዛቸዋለሁ፥ መቅደሴንም በመካከላቸው ለዘለዓለም አኖራለሁ። ማደሪያዬ በላያቸው ላይ ይሆናል፤ እኔ አምላካቸው እሆናለሁ፥ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ። መቅደሴም ለዘለዓለም በመካከላቸው በሆነ ጊዜ፥ እስራኤልን የቀደስኩ እኔ ጌታ እንደሆንሁ አሕዛብ ያውቃሉ።