ሕዝቅኤል 37:1-3
ሕዝቅኤል 37:1-3 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
የእግዚአብሔርም እጅ በላዬ ነበረ፤ እግዚአብሔርም በመንፈሱ አወጣኝ፤ አጥንቶችም በሞሉበት ሸለቆ መካከል አኖረኝ። በእነርሱም አንጻር በዙሪያቸው አዞረኝ፤ እነሆም በሜዳው እጅግ ነበሩ፤ እነሆም እጅግ ደርቀው ነበር። እርሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! እነዚህ አጥንቶች በሕይወት ይኖራሉን?” አለኝ። እኔም፥ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ታውቃለህ” አልሁ።
Share
ሕዝቅኤል 37 ያንብቡሕዝቅኤል 37:1-3 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
የእግዚአብሔር እጅ በላዬ ነበረ፤ እርሱም በእግዚአብሔር መንፈስ አወጣኝ፤ በሸለቆ መካከልም አኖረኝ፤ ሸለቆውም በዐጥንቶች ተሞልቶ ነበር። በእነርሱም መካከል ወደ ፊትና ወደ ኋላ አመላለሰኝ፤ በሸለቆውም ወለል ላይ በጣም የደረቁ እጅግ ብዙ ዐጥንቶች አየሁ። እርሱም፣ “የሰው ልጅ ሆይ፤ እነዚህ ዐጥንቶች በሕይወት ሊኖሩ ይችላሉን?” ሲል ጠየቀኝ። እኔም፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ብቻ ታውቃለህ” አልሁ።
Share
ሕዝቅኤል 37 ያንብቡሕዝቅኤል 37:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
የእግዚአብሔርም እጅ በላዬ ነበረ እግዚአብሔርም በመንፈሱ አወጣኝ አጥንቶችም በሞሉባት ሸለቆ መካከል አኖረኝ። በእነርሱም አንጻር በዙሪያቸው አሳለፈኝ፥ እነሆም፥ በሸለቆው ፊት እጅግ ብዙ ነበሩ፥ እነሆም፥ እጅግ ደርቀው ነበር። እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ አጥንቶች በሕይወት ይኖራሉን? አለኝ። እኔም፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ ታውቃለህ አልሁ።
Share
ሕዝቅኤል 37 ያንብቡ