ሕዝቅኤል 36:34-35
ሕዝቅኤል 36:34-35 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ባድማ የነበረች፥ በመንገደኛም ሁሉ ዐይን ዘንድ ባድማ የነበረች ምድር ትታረሳለች። ሰዎችም ባድማ የነበረች ይህች ምድር እንደ ዔድን ገነት ሆናለች፤ የፈረሱት፥ ባድማ የሆኑት፥ የጠፉትም ከተሞች ተመሽገዋል፤ ሰውም የሚኖርባቸው ሆነዋል ይላሉ።
Share
ሕዝቅኤል 36 ያንብቡሕዝቅኤል 36:34-35 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በዐላፊ አግዳሚው ዐይን ጠፍ ሆኖ ይታይ የነበረው ባድማ መሬት ይታረሳል። እነርሱም፣ “ጠፍ የነበረው ይህ ምድር እንደ ዔድን ገነት መሰለ፤ የተደመሰሱ፣ የፈራረሱና ባድማ የሆኑት ከተሞች አሁን መኖሪያና ምሽግ ሆነዋል” ይላሉ።
Share
ሕዝቅኤል 36 ያንብቡሕዝቅኤል 36:34-35 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ባድማ የነበረች በመንገደኛም ሁሉ ዓይን ዘንድ ባድማ የነበረች ምድር ትታረሳለች። ሰዎችም፦ ባድማ የነበረች ይህች ምድር እንደ ዔድን ገነት ሆናለች፥ የፈረሱት ባድማ የሆኑት የጠፉትም ከተሞች ተመሽገዋል ሰውም የሚኖርባቸው ሆነዋል ይላሉ።
Share
ሕዝቅኤል 36 ያንብቡ