የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሕዝቅኤል 35:1-15

ሕዝቅኤል 35:1-15 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! ፊት​ህን ወደ ሴይር ተራራ መልስ፤ ትን​ቢ​ትም ተና​ገ​ር​በት፤ እን​ዲ​ህም በለው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የሴ​ይር ተራራ ሆይ! እነሆ በአ​ንተ ላይ ነኝ፤ እጄን እዘ​ረ​ጋ​ብ​ሃ​ለሁ፤ ባድ​ማና ውድ​ማም አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ። ከተ​ሞ​ች​ህ​ንም አፈ​ራ​ር​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አን​ተም ባድማ ትሆ​ና​ለህ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ለህ። የዘ​ለ​ዓ​ለም ጠላት ሁነ​ሃ​ልና፥ በመ​ከ​ራ​ቸ​ውም ጊዜ በኀ​ይ​ለ​ኛ​ይቱ የኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ቀጠሮ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በሰ​ይፍ እጅ ጥለ​ሃ​ቸ​ዋ​ልና፤ ስለ​ዚህ እኔ ሕያው ነኝ! በደም እንደ በደ​ልህ ደም ያሳ​ድ​ድ​ሃል፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። የሴ​ይ​ር​ንም ተራራ ውድማ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ ሰው​ንና እን​ስ​ሳ​ው​ንም አጠ​ፋ​ለሁ። ተራ​ሮ​ች​ህ​ንም በተ​ገ​ደ​ሉት ሰዎች እሞ​ላ​ለሁ፤ በኮ​ረ​ብ​ቶ​ች​ህና በሸ​ለ​ቆ​ዎ​ችህ፥ በፈ​ሳ​ሾ​ች​ህም ሁሉ ላይ በሰ​ይፍ የተ​ገ​ደ​ሉት ሁሉ ይወ​ድ​ቃሉ። ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ባድማ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ፤ ከተ​ሞ​ች​ህም ሰው የማ​ይ​ኖ​ር​ባ​ቸው ይሆ​ናሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ለህ። “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚያ ሳለ፥ አንተ፥ እነ​ዚህ ሁለቱ ሕዝ​ቦች፥ እነ​ዚ​ህም ሁለቱ ሀገ​ሮች ለእኔ ይሆ​ናሉ፤ እኔም እወ​ር​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ ብለ​ሃ​ልና፤ ስለ​ዚህ እኔ ሕያው ነኝ! እንደ ቍጣህ መጠን፥ እነ​ር​ሱ​ንም ጠል​ተህ እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ኸው እንደ ቅን​አ​ትህ መጠን እኔ እፈ​ር​ድ​ብ​ሃ​ለሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በፈ​ረ​ድ​ሁ​ብ​ህም ጊዜ በእ​ነ​ርሱ ዘንድ የታ​ወ​ቅሁ እሆ​ና​ለሁ። አን​ተም፦ ፈር​ሰ​ዋል፤ መብ​ልም ሆነው ለእኛ ተሰ​ጥ​ተ​ዋል ብለህ በእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ላይ የተ​ና​ገ​ር​ኸ​ውን ስድብ ሁሉ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሰማ​ሁት ታው​ቃ​ለህ። አንተ አፍ​ህን በእኔ ላይ ከፍ ከፍ እንደ አደ​ረ​ግህ እኔ ሰም​ቼ​አ​ለሁ።” ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ ይላል፥ “ምድር ሁሉ ደስ ሲላት አን​ተን ባድማ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ። የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ርስት ባድማ ስለ ሆነ በላዩ ደስ እን​ዳ​ለህ፥ እን​ዲሁ አደ​ር​ግ​ብ​ሃ​ለሁ፤ የሴ​ይር ተራራ ሆይ! አን​ተና መላው ኤዶ​ም​ያስ ባድማ ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ለህ።”

ሕዝቅኤል 35:1-15 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ “የሰው ልጅ ሆይ፤ ፊትህን ወደ ሴይር ተራራ አዙር፤ ትንቢትም ተናገርበት፤ እንዲህም በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ የሴይር ተራራ ሆይ፤ በአንተ ላይ ተነሥቻለሁ፤ እጄን በአንተ ላይ እዘረጋለሁ፤ ባድማና ጠፍ አደርግሃለሁ። ከተሞችህን ፍርስራሽ አደርጋቸዋለሁ፤ ባድማ ትሆናለህ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃለህ። “ ‘እስራኤላውያን ቅጣታቸው እጅግ መራራ ከሆነ ደረጃ ላይ ደርሶ ፍዳቸውን በሚቀበሉበት ጊዜ፣ የጥንቱን ቂም ቋጥረህ ለሰይፍ ስለ ዳረግሃቸው፤ በሕያውነቴ እምላለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ለደም ማፍሰስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ፤ እርሱም ያሳድድሃል። ደም ማፍሰስን ስላልጠላህ፣ ደም ማፍሰስ ያሳድድሃል። የሴይርን ተራራ ባድማና ጠፍ አደርጋለሁ፤ በእርሱም ላይ የሚወጡትንና የሚወርዱትን አስቀራለሁ። ተራሮችህን በሬሳ እሞላለሁ፤ በሰይፍ የተገደሉት ሁሉ በተራሮችህ፣ በሸለቆዎችህና በውሃ መውረጃዎችህ ሁሉ ላይ ይወድቃሉ። ለዘላለም ባድማ አደርግሃለሁ፤ ከተሞችህ መኖሪያ አይሆኑም። ከዚያም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ። “ ‘እኔ እግዚአብሔር በዚያ እያለሁ፣ “እነዚህ ሁለት ሕዝቦችና ሁለት አገሮች የእኛ ይሆናሉ፤ እኛም እንወርሳቸዋለን።” ብለሃልና፤ ስለዚህ በሕያውነቴ እምላለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ከጥላቻችሁ የተነሣ በእነርሱ ላይ በገለጣችሁት ቍጣና ቅናት ልክ እፈርድባችኋለሁ፤ በእናንተም ላይ በምፈርድበት ጊዜ፣ ማንነቴ በእነርሱ መካከል እንዲታወቅ አደርጋለሁ። ከዚያም ስለ እስራኤል ተራሮች፣ “ጠፍ ሆነዋል፤ ቦጫጭቀን እንድንበላቸው ለእኛ ተሰጥተዋል” ብለህ በንቀት የተናገርኸውን እኔ እግዚአብሔር እንደ ሰማሁ በዚያን ጊዜ ታውቃለህ። በእኔ ላይ ታብየሃል፤ በድፍረትም በእኔ ላይ ተናግረሃል፤ እኔም ሰምቼዋለሁ። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ መላዪቷ ምድር በምትደሰትበት ጊዜ፣ አንተን ባድማ አደርግሃለሁ። የእስራኤል ቤት ርስት ባድማ በሆነች ጊዜ ስለ ተደሰትህ፣ እኔም እንዲሁ አደርግብሃለሁ። የሴይር ተራራ ሆይ፤ አንተና መላዋ ኤዶም ባድማ ትሆናላችሁ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’ ”

ሕዝቅኤል 35:1-15 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ ሴይር ተራራ አድርግ፥ ትንቢትም ተናገርበት፥ እንዲህም በለው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሴይር ተራራ ሆይ፥ እነሆ፥ በአንተ ላይ ነኝ፥ እጄንም እዘረጋብሃለሁ ባድማና ውድማም አደርግሃለሁ። ከተሞችህንም አፈራርሳቸዋለሁ፥ አንተም ባድማ ትሆናለህ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃለህ። የዘላለም ጥል ስላለህ በመከራቸውም ጊዜ በኋለኛይቱ የኃጢአታቸው ቀጠሮ ጊዜ የእስራኤልን ልጆች በሰይፍ እጅ ጥለሃቸዋልና ስለዚህ እኔ ሕያው ነኝና ለደም አሳልፌ እሰጥሃለሁ ደምም ያሳድድሃል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ ደምን ስላልጠላህ ደም ያሳድድሃል። የሴይርንም ተራራ ውድማ አደርገዋለሁ፥ የሚሄደውንና የሚመለሰውንም ከእርሱ አጠፋለሁ። ተራሮቹንም በተገደሉት ሰዎች እሞላለሁ፥ በኮረብቶችህና በሸለቆችህ በፈሳሾችህም ሁሉ ላይ በሰይፍ የተገደሉት ሁሉ ይወድቃሉ። ለዘላለምም ባድማ አደርግሃለሁ ከተሞችህም ሰው የማይኖርባቸው ይሆናሉ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ። እግዚአብሔርም በዚያ ሳለ፥ አንተ፦ እነዚህ ሁለቱ ሕዝቦች እነዚህም ሁለቱ አገሮች ለእኔ ይሆናሉ እኛም እንወርሳቸዋለን ብለሃልና ስለዚህ እኔ ሕያው ነኝና እንደ ቍጣህ መጠን እነርሱንም ጠልተህ እንዳደረግኸው እንደ ቅንዓትህ መጠን እኔ እሠራለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ በፈረድሁብህም ጊዜ በእነርሱ ዘንድ የታወቅሁ እሆናለሁ። አንተም፦ ፈርሰዋል መብልም ሆነው ለእኛ ተሰጥተዋል ብለህ በእስራኤል ተራሮች ላይ የተናገርኸውን ስድብ ሁሉ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሰማሁት ታውቃለህ። በአፋችሁም ተመካችሁብኝ፥ ቃላችሁንም አበዛችሁብኝ፥ እኔም ሰምቼዋለሁ። ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ ምድር ሁሉ ደስ ሲላት አንተን ባድማ አደርግሃለሁ። የእስራኤል ቤት ርስት ባድማ ስለ ሆነ በላዩ ደስ እንዳለህ፥ እንዲሁ አደርግብሃለሁ፥ የሴይር ተራራ ሆይ፥ አንተና ኤዶምያስ ሁሉ ሁለንተናውም ባድማ ትሆናላችሁ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።

ሕዝቅኤል 35:1-15 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! ፊትህን ወደ ኤዶም ተራራ መልሰህ በሕዝቡም ላይ ትንቢት ተናገር፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምለውንም ሁሉ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘የኤዶም ሕዝብ ሆይ! እነሆ እኔ እናንተን እቃወማለሁ፤ ምድራችሁንም ባድማና ወና ላደርግ በእናንተ ላይ ተነሥቼአለሁ። ከተሞቻችሁንም አፈራርሳለሁ፤ ምድራችሁንም ባድማ አደርጋታለሁ፤ ከዚያም በኋላ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ታውቃላችሁ። “ ‘ለብዙ ጊዜ ከቈየው ጥላቻችሁ የተነሣ በኃጢአቱ ምክንያት በደረሰበት የመጨረሻ ቅጣትና በመከራው ጊዜ የእስራኤልን ሕዝብ ለሰይፍ አሳልፋችሁ ሰጣችሁ። ስለዚህ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ሕያው እንደ መሆኔ ለግድያ አዘጋጃችኋለሁ፤ ገዳይም ያሳድዳችኋል፤ ደም ማፍሰስን ስላልጠላችሁ ገዳይ ያሳድዳችኋል። እኔ የኤዶምን ተራራማ አገር ባድማና ወና አደርጋለሁ፤ በዚያም በኩል ማንም ሰው እንዳያልፍ አደርጋለሁ፤ ተራራዎችን ሁሉ በተገደሉ ሰዎች ሬሳ እሸፍናለሁ፤ በጦርነት የተገደለውም ሬሳ ኰረብቶቻችሁና ሸለቆዎቻችሁን ወንዞቻችሁንም ሁሉ ይሸፍናል፤ እኔ ለዘለዓለሙ ምድራችሁን ባድማ አደርጋለሁ፤ ዳግመኛም በከተሞቻችሁ የሚኖር አይገኝም፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ታውቃላችሁ። “ ‘እኔ እግዚአብሔር እዚያ ያለሁ ብሆንም እንኳ ሁለቱን ሕዝቦች፥ ማለት ይሁዳንና እስራኤልን፥ እንዲሁም ምድራቸውን ጭምር የእናንተ አድርጋችሁ ለመውረስ አስባችሁ ነበር። ስለዚህም እኔ ልዑል እግዚአብሔር ሕያው እንደ መሆኔ በሕዝቤ ላይ ባላችሁ ጥላቻ ምክንያት ያሳያችሁት ቊጣና ምቀኝነት ሁሉ ተገቢውን ቅጣት እሰጣችኋለሁ። እነርሱም እናንተን በምቀጣበት ጊዜ የምቀጣችሁ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን እንዲያውቁ አደርጋለሁ። እነርሱ ባድማ የተደረጉ ስለ ሆነ በእኛ ቊጥጥር ሥር እንዲሆኑ ተሰጥተውናል’ ብላችሁ በእስራኤል ተራራዎች ላይ የተናገራችሁትን የንቀት ንግግር እኔ እግዚአብሔር የሰማሁ መሆኔን ወደፊት ታውቃላችሁ። በእኔ ላይ መገዳደራችሁንና ያለ ገደብም በእኔ ላይ መናገራችሁን ሰምቼአለሁ።” ስለዚህም እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምለው ይህ ነው፦ “ዓለም ሁሉ ሲደሰት የእናንተን አገር ግን ባድማ አደርጋታለሁ። የእስራኤል ምድር ባድማ በመሆኑ እንደ ተደሰታችሁ እኔም የሴኢርን ተራራና የኤዶምን ግዛት ሁሉ ባድማ አደርጋለሁ፤ ከዚያ በኋላ ሁሉም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃል።”

ሕዝቅኤል 35:1-15 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ ሴይር ተራራ አድርግ፥ ትንቢትም ተናገርበት፥ እንዲህም በለው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሴይር ተራራ ሆይ፥ እነሆ በአንተ ላይ ነኝ፥ እጄን እዘረጋብሃለሁ ባድማና ውድማም አደርግሃለሁ። ከተሞችህን ፍርስራሽ አደርጋቸዋለሁ፥ አንተም ባድማ ትሆናለህ፥ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃለህ። የዘለዓለም ጥል ስላለህ በመጨረሻው የፍርዳቸው ጊዜ፥ በመከራቸው ጊዜ የእስራኤልን ልጆች በሰይፍ እጅ ጥለሃቸዋልና፥ ስለዚህ እኔ ሕያው ነኝና ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ ለደም አሳልፌ እሰጥሃለሁ ደምም ያሳድድሃል፥ ደምን ስላልጠላህ ደም ያሳድድሃል። የሴይርን ተራራ ውድማና ባድማ አደርገዋለሁ፥ የሚሄደውንና የሚመለሰውንም ከእርሱ አጠፋለሁ። ተራሮቹንም በተገደሉት ሰዎች እሞላለሁ፤ በኮረብቶችህ፥ በሸለቆዎችህና በውሃ መውረጃዎችህ ሁሉ ላይ በሰይፍ የተገደሉት ይወድቃሉ። ለዘለዓለም ባድማ አደርግሃለሁ፥ ከተሞችህም ሰው አይኖርባቸውም፥ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ። ጌታ በዚያ ሳለ፥ አንተ ግን፦ “እነዚህ ሁለቱ ሕዝቦችና እነዚህ ሁለቱ አገሮች ለእኔ ይሆናሉ እኛም እንወርሳቸዋለን” ብለሃልና፥ ስለዚህ እኔ ሕያው ነኝና ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ እነርሱን ጠልተህ እንዳደረግኸው እንደ ቁጣህና እንደ ቅናትህ መጠን አደርጋለሁ፤ በፈረድሁብህም ጊዜ በእነርሱ መካከል ማንነቴን አስታውቃለሁ። በእስራኤል ተራሮች ላይ “ፈርሰዋል እንድንበላቸው ለእኛ ተሰጥተዋል” ብለህ የተናገርኸውን ስድብ ሁሉ እኔ ጌታ እንደ ሰማሁት ታውቃለህ። በአፋችሁ ታበያችሁብኝ፥ ንግግራችሁንም በእኔ ላይ አበዛችሁ፤ እኔም ሰምቼዋለሁ። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ምድር ሁሉ ስትደሰት አንተን ባድማ አደርግሃለሁ። የእስራኤል ቤት ርስት ባድማ በመሆኑ እንደተደሰትህ፥ እንዲሁ አደርግብሃለሁ፤ የሴይር ተራራ ሆይ፥ አንተ፥ ኤዶም ሁሉና ሁለንተናዋ ባድማ ትሆናላችሁ፤ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።