ሕዝቅኤል 23:40-49
ሕዝቅኤል 23:40-49 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“ከዚህም በላይ ወንዶች ከሩቅ እንዲመጡላቸው መልእክተኛ ላኩ፤ እነርሱም መጡ። አንቺም ገላሽን ታጥበሽ፣ ዐይንሽን ተኵለሽና በጌጣጌጥ ተውበሽ ጠበቅሻቸው። በተዋበ ዐልጋ ላይ ተቀመጥሽ፤ ዕጣኔንና ዘይቴን ያኖርሽበትንም ጠረጴዛ ከዐልጋው ፊት ለፊት አደረግሽ። “የሚፈነጥዙ ሰዎች ድምፅ በዙሪያዋ ነበር፤ ከሚያውኩ ሰዎች ጋራ ከበረሓ የመጡ ሰካራሞች ነበሩ፤ በሴትየዋና በእኅቷም ላይ አንባር፣ በራሳቸውም ላይ የተዋበ አክሊል አደረጉላቸው። እኔም በአመንዝራነት ሰውነቷ ስላለቀው፣ ‘እርሷ ሕይወቷ ይኸው ስለ ሆነ እንደ ዝሙት ዐዳሪ ይጠቀሙባት’ አልሁ። እነርሱም ከርሷ ጋራ ተኙ፤ ሰው ከአመንዝራ ሴት ጋራ እንደሚተኛ ከእነዚያ ባለጌ ሴቶች፣ ከኦሖላና ከኦሖሊባ ጋራ ተኙ። ጻድቃን ግን ለአመንዝራና ለነፍሰ ገዳይ ሴቶች የሚገባቸውን ፍርድ ይፈርዱባቸዋል። አመንዝሮች ናቸውና፤ እጃቸውም በደም ተበክሏል። “ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ሕዝብን ቀስቅሰህ አምጣባቸው፤ ለሽብርና ለዝርፊያም አሳልፈህ ስጣቸው። ሕዝቡ በድንጋይ ይወግራቸዋል፤ በገዛ ሰይፋቸው ይቈራርጣቸዋል፤ ወንድና ሴት ልጆቻቸውን ይገድላል፤ ቤቶቻቸውንም ያቃጥላል። “ስለዚህ ሴቶች ሁሉ እንዲጠነቀቁና መጥፎ ፈለጋችሁን እንዳይከተሉ፣ ሴሰኛነትን ከምድሪቱ አጠፋለሁ። የሴሰኝነታችሁን ዋጋ ታገኛላችሁ፤ ጣዖት በማምለክ ለፈጸማችሁት ኀጢአት ቅጣት ትሸከማላችሁ፤ በዚያ ጊዜ እኔ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።”
ሕዝቅኤል 23:40-49 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
“ወንዶችን ከሩቅ አገር ጋብዘው እንዲያመጡላቸው ደጋግመው መልእክተኞችን ላኩ፤ የፈለጓቸውም ወንዶች መጡላቸው፤ ሁለቱ እኅትማማቾች ገላቸውን ታጠቡ፤ ዐይናቸውን ተኳሉ፤ ጌጣጌጦቻቸውንም አደረጉ፤ በተዋቡም ድንክ አልጋዎች ላይ በፊት ለፊታቸው ተቀመጡ፤ እኔ የሰጠኋቸው ዕጣንና የወይራ ዘይት ሳይቀር ብዙ መልካም ነገሮችን በጠረጴዛ ላይ ደረደሩ። የብዙ ሁከተኞች ድምፅ በአካባቢአቸው ነበር፤ ከእነርሱም ጋር ከበረሓ የመጡ ሰካራሞች ነበሩ፤ ሰካራሞቹም በሴቶቹ ክንዶች ላይ አምባር፥ በራሶቻቸውም ላይ የተዋቡ አክሊሎችን አደረጉላቸው። እኔም በልቤ ‘እነዚህ ወንዶች ዝሙት የሚፈጽሙት በአመንዝራነት ሰውነትዋ ካለቀ ሴት ጋር ነው’ አልኩ። ወንዶች ወደ አመንዝራ ሴቶች እንደሚሄዱ ሁሉ፥ እነዚያም ከበረሓ የመጡ ወንዶች ኦሆላና ኦሆሊባ ከተባሉት ከእነዚያ ከረከሱ ሴቶች ጋር አመነዘሩ። ማመንዘር ስለ ለመዱና እጆቻቸውም በደም ስለ ተበከሉ፥ በእነዚያ በአመንዝሮቹና በነፍሰ ገዳዮቹ ላይ ጻድቃን ይፈርዱባቸዋል።” ልዑል እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ “በእነርሱ ላይ ሁከተኞችን ሰብስብ፤ እነርሱንም ለብዝበዛና ለሽብር አሳልፈህ ስጣቸው። ሁከተኞችንም በድንጋይ ይውገራቸው፤ በሰይፍም ይቈራርጧቸው፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ይግደሉ። ቤቶቻቸውንም በእሳት ያቃጥሉ። እናንተ ሁለት እኅትማማቾች እንዳመነዘራችሁ ሁሉ ሴቶች ከእንግዲህ ወዲህ እንዳያመነዝሩ መቀጣጫ ይሆን ዘንድ ከምድሪቱ ሁሉ ላይ የሴሰኝነት ስድነት እንዲወገድ አደርጋለሁ። እናንተም ሁለት እኅትማማቾች ስለ ስድነታችሁና ለጣዖቶች በመስገድ ስለ ፈጸማችሁት ኃጢአት እቀጣችኋለሁ፤ በዚያን ጊዜ እኔ ልዑል እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።”
ሕዝቅኤል 23:40-49 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ከሩቅ ሀገርም ወደመጡ ሰዎች መልእክተኞችን ላኩ፤ እነርሱም በደረሱ ጊዜ ይታጠባሉ፤ ዐይኖቻቸውንም ይኳላሉ፤ ያጌጣሉም። በክብር አልጋ ላይ ይቀመጣሉ፤ በፊት ለፊታቸውም ማዕድ ተዘጋጅታ ነበር፤ በዕጣኔና በዘይቴም ደስ ይላቸዋል። የበገናውን አውታር ድምፅ ይቃኛሉ፤ ከብዙ ሰዎችም ጉባኤ ጋር ሰካራሞቹ ከምድረ በዳ መጡ፤ በእጃቸው አንባር፥ በራሳቸውም የተዋበ አክሊል አደረጉ። እኔም፦ ‘አሁን ከእርስዋ ጋር ያመነዝራሉ፤ እርስዋም ከእነርሱ ጋር ታመነዝራለች፤’ አልሁ። ወደ ጋለሞታ እንደሚገቡም ወደ እርስዋ ገቡ፤ እንዲሁ ይሰስኑ ዘንድ ወደ ሐላና ወደ ሐሊባ ገቡ። ሴቶቹ አመንዝሮች ናቸውና፥ በእጃቸውም ደም አለና ጻድቃን ሰዎች በአመንዝሮቹና በደም አፍሳሾቹ ሴቶች ላይ በሚፈረደው ፍርድ ይፈርዱባቸዋል።” ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ጉባኤን አመጣባቸዋለሁ፤ ለመበተንና ለመበዝበዝም አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ። ጉባኤውም በድንጋይ ይወግሩአቸዋል፤ በሰይፋቸውም ይቈርጡአቸዋል፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም ይገድላሉ፤ ቤቶቻቸውንም በእሳት ያቃጥላሉ። ሴቶችም ሁሉ እንደ ኀጢአታችሁ እንዳይሠሩ ይማሩ ዘንድ ሴሰኝነትን ከምድር ላይ አጠፋለሁ። እንግዲህ በደላችሁ በላያችሁ ላይ ይመለሳል፤ እናንተም የጣዖቶቻችሁን ኀጢአት ትሸከማላችሁ፤ እኔም ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።”
ሕዝቅኤል 23:40-49 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“ከዚህም በላይ ወንዶች ከሩቅ እንዲመጡላቸው መልእክተኛ ላኩ፤ እነርሱም መጡ። አንቺም ገላሽን ታጥበሽ፣ ዐይንሽን ተኵለሽና በጌጣጌጥ ተውበሽ ጠበቅሻቸው። በተዋበ ዐልጋ ላይ ተቀመጥሽ፤ ዕጣኔንና ዘይቴን ያኖርሽበትንም ጠረጴዛ ከዐልጋው ፊት ለፊት አደረግሽ። “የሚፈነጥዙ ሰዎች ድምፅ በዙሪያዋ ነበር፤ ከሚያውኩ ሰዎች ጋራ ከበረሓ የመጡ ሰካራሞች ነበሩ፤ በሴትየዋና በእኅቷም ላይ አንባር፣ በራሳቸውም ላይ የተዋበ አክሊል አደረጉላቸው። እኔም በአመንዝራነት ሰውነቷ ስላለቀው፣ ‘እርሷ ሕይወቷ ይኸው ስለ ሆነ እንደ ዝሙት ዐዳሪ ይጠቀሙባት’ አልሁ። እነርሱም ከርሷ ጋራ ተኙ፤ ሰው ከአመንዝራ ሴት ጋራ እንደሚተኛ ከእነዚያ ባለጌ ሴቶች፣ ከኦሖላና ከኦሖሊባ ጋራ ተኙ። ጻድቃን ግን ለአመንዝራና ለነፍሰ ገዳይ ሴቶች የሚገባቸውን ፍርድ ይፈርዱባቸዋል። አመንዝሮች ናቸውና፤ እጃቸውም በደም ተበክሏል። “ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ሕዝብን ቀስቅሰህ አምጣባቸው፤ ለሽብርና ለዝርፊያም አሳልፈህ ስጣቸው። ሕዝቡ በድንጋይ ይወግራቸዋል፤ በገዛ ሰይፋቸው ይቈራርጣቸዋል፤ ወንድና ሴት ልጆቻቸውን ይገድላል፤ ቤቶቻቸውንም ያቃጥላል። “ስለዚህ ሴቶች ሁሉ እንዲጠነቀቁና መጥፎ ፈለጋችሁን እንዳይከተሉ፣ ሴሰኛነትን ከምድሪቱ አጠፋለሁ። የሴሰኝነታችሁን ዋጋ ታገኛላችሁ፤ ጣዖት በማምለክ ለፈጸማችሁት ኀጢአት ቅጣት ትሸከማላችሁ፤ በዚያ ጊዜ እኔ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።”
ሕዝቅኤል 23:40-49 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ደግሞ መልእክተኛ ወደ ተላከባቸው ከሩቅም ወደሚመጡ ሰዎች ልካችኋል፥ እነሆም መጡ፥ አንቺም ታጠብሽላቸው ዓይኖችሽንም ተኳልሽ ጌጥም አጌጥሽ፥ በክብር አልጋ ላይ ተቀመጥሽ፥ በፊት ለፊትዋም ማዕድ ተዘጋጅታ ነበር፥ ዕጣኔንና ዘይቴንም አኖርሽባት። የደስተኞችም ድምፅ በእርስዋ ዘንድ ነበረ፥ ከብዙም ሰዎች ጉባኤ ጋር ሰካራሞቹ ከምድረ በዳ መጡ፥ በእጃቸው አንበር በራሳቸውም የተዋበ አክሊል አደረጉ። እኔም በምንዝር ላረጀችው፦ አሁን ከእርስዋ ጋር ያመነዝራሉ እርስዋም ከእነርሱ ጋር ታመነዝራለች አልሁ። ወደ ጋለሞታም እንደሚገቡ ወደ እርስዋ ገቡ፥ እንዲሁ ይሰስኑ ዘንድ ወደ ኦሖላና ወደ ኦሖሊባ ገቡ። ሴቶቹ አመንዝሮች ናቸውና፥ በጃቸውም ደም አለና ጻጽቃን ሰዎች በአመንዝሮቹና በደም አፍሳሾቹ ሴቶች ላይ በሚፈረደው ፍርድ ይፈርዱባቸዋል። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጉባኤን አመጣባቸዋለሁ፥ ለመበተንና ለመበዝበዝም አሳልፌ አሰጣቸዋለሁ። ጉባኤውም በድንጋይ ይወግሩአቸዋል በሰይፋቸውም ይቈርጡአቸዋል፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም ይገድላሉ፥ ቤቶቻቸውንም በእሳት ያቃጥላሉ። ሴቶችም ሁሉ እንደ ሴሰኝነታችሁ እንዳይሠሩ ይማሩ ዘንድ ሴሰኝነትን ከምድር ላይ አጠፋለሁ። ሴሰኝነታችሁንም በላያችሁ ላይ ይመልሳሉ፥ እናንተም የጣዖቶቻችሁን ኃጢአት ትሸከማላችሁ፥ እኔም ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
ሕዝቅኤል 23:40-49 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
“ወንዶችን ከሩቅ አገር ጋብዘው እንዲያመጡላቸው ደጋግመው መልእክተኞችን ላኩ፤ የፈለጓቸውም ወንዶች መጡላቸው፤ ሁለቱ እኅትማማቾች ገላቸውን ታጠቡ፤ ዐይናቸውን ተኳሉ፤ ጌጣጌጦቻቸውንም አደረጉ፤ በተዋቡም ድንክ አልጋዎች ላይ በፊት ለፊታቸው ተቀመጡ፤ እኔ የሰጠኋቸው ዕጣንና የወይራ ዘይት ሳይቀር ብዙ መልካም ነገሮችን በጠረጴዛ ላይ ደረደሩ። የብዙ ሁከተኞች ድምፅ በአካባቢአቸው ነበር፤ ከእነርሱም ጋር ከበረሓ የመጡ ሰካራሞች ነበሩ፤ ሰካራሞቹም በሴቶቹ ክንዶች ላይ አምባር፥ በራሶቻቸውም ላይ የተዋቡ አክሊሎችን አደረጉላቸው። እኔም በልቤ ‘እነዚህ ወንዶች ዝሙት የሚፈጽሙት በአመንዝራነት ሰውነትዋ ካለቀ ሴት ጋር ነው’ አልኩ። ወንዶች ወደ አመንዝራ ሴቶች እንደሚሄዱ ሁሉ፥ እነዚያም ከበረሓ የመጡ ወንዶች ኦሆላና ኦሆሊባ ከተባሉት ከእነዚያ ከረከሱ ሴቶች ጋር አመነዘሩ። ማመንዘር ስለ ለመዱና እጆቻቸውም በደም ስለ ተበከሉ፥ በእነዚያ በአመንዝሮቹና በነፍሰ ገዳዮቹ ላይ ጻድቃን ይፈርዱባቸዋል።” ልዑል እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ “በእነርሱ ላይ ሁከተኞችን ሰብስብ፤ እነርሱንም ለብዝበዛና ለሽብር አሳልፈህ ስጣቸው። ሁከተኞችንም በድንጋይ ይውገራቸው፤ በሰይፍም ይቈራርጧቸው፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ይግደሉ። ቤቶቻቸውንም በእሳት ያቃጥሉ። እናንተ ሁለት እኅትማማቾች እንዳመነዘራችሁ ሁሉ ሴቶች ከእንግዲህ ወዲህ እንዳያመነዝሩ መቀጣጫ ይሆን ዘንድ ከምድሪቱ ሁሉ ላይ የሴሰኝነት ስድነት እንዲወገድ አደርጋለሁ። እናንተም ሁለት እኅትማማቾች ስለ ስድነታችሁና ለጣዖቶች በመስገድ ስለ ፈጸማችሁት ኃጢአት እቀጣችኋለሁ፤ በዚያን ጊዜ እኔ ልዑል እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።”
ሕዝቅኤል 23:40-49 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ደግሞም መልእክተኛ ወደ ተላከባቸው፥ ከሩቅም ወደሚመጡ ሰዎች ልከዋል፥ እነሆም መጡ፤ ታጠብሽላቸው ዓይንሽን ተኳልሽ፥ ጌጥም አደረግሽ፤ ክብር ባለው አልጋ ላይ ተቀመጥሽ፥ በፊት ለፊቱም ማዕድ ተዘጋጅቶ ነበር፥ ዕጣኔንና ዘይቴንም በዚያ ላይ አስቀመጥሽ። የደስተኞችም ድምፅ በእርሷ ዘንድ ነበረ፥ ከብዙም ሰዎች ጉባኤ ጋር ሰካራሞቹ ከምድረበዳ መጡ፥ በእጃቸው አንበር በራሳቸውም የተዋበ አክሊል አደረጉ። እኔም በዝሙት ላረጀችው፦ አሁን ከእርሷ ጋር ያመነዝራሉ፥ እርሷም ታመነዝራለች አልሁ። ሰው ወደ አመንዝራ እንደሚገባ ወደ እርሷ ገቡ፤ ስለዚህ አመንዝራ ወደ ሆኑት ወደ ኦሆላና ወደ ኦሆሊባ ገቡ። ጻጽቃን ሰዎች በአመንዝሮቹና በደም አፍሳሾቹ ሴቶች ላይ በሚፈረደው ፍርድ ይፈርዱባቸዋል፤ ምክንያቱም አመንዝሮች ናቸውና፥ ደምም በእጃቸው አለና። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ጉባኤን አመጣባቸዋለሁ፥ ለፍርሃትና ለመበዝበዝ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ። ጉባኤውም በድንጋይ ይወግሩአቸዋል፥ በሰይፋቸው ይቆርጡአቸዋል፤ ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻቸውን ይገድላሉ፥ ቤቶቻቸውንም በእሳት ያቃጥላሉ። ሴቶችም ሁሉ እንደ አመንዝራነታችሁ እንዳይሠሩ፥ እንዲጠነቀቁ አመንዝራነትን ከምድር ላይ አጠፋለሁ። አመንዝራነታችሁን በላያችሁ ላይ ይመልሳሉ፥ የጣዖቶቻችሁን ኃጢአት ትሸከማላችሁ፥ እኔም ጌታ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።