ዘፀአት 38:22-23
ዘፀአት 38:22-23 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ከይሁዳ ነገድም የሆነ የሆር የልጅ ልጅ፥ የኡሪ ልጅ ባስልኤል እግዚአብሔር ለሙሴ እንዳዘዘው ሁሉ አደረገ። ከእርሱም ጋር ከዳን ነገድ የሆነ የአሒሳሚክ ልጅ ኤልያብ ነበረ፤ እርሱም በሰማያዊ፥ በሐምራዊ፥ በቀይም ግምጃ፥ በጥሩ በፍታ የሽመና ሥራ ይሠራ ዘንድ የቅርጽ፥ የሽመናና የጥልፍ ሥራ አለቃ ነበረ።
ያጋሩ
ዘፀአት 38 ያንብቡዘፀአት 38:22-23 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከይሁዳ ነገድ የሆር የልጅ ልጅ፣ የኡሪ ልጅ የሆነው ባስልኤል፣ እግዚአብሔር ሙሴን ያዘዘውን ሁሉ አደረገ። ከርሱም ጋራ ከዳን ነገድ የሆነው የአሂሳሚክ ልጅ ኤልያብ፣ ዕቅድ አውጭና የእጅ ጥበብ ባለሙያ፣ በሰማያዊ፣ በሐምራዊ፣ በቀይ ማግና በቀጭን በፍታ ጥልፍ ጠላፊ ነበር።
ያጋሩ
ዘፀአት 38 ያንብቡዘፀአት 38:22-23 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ከይሁዳ ነገድም የሆነ የሆር የልጅ ልጅ፥ የኡሪ ልጅ ባስልኤል እግዚአብሔር ለሙሴ ያዘዘውን ሁሉ አደረገ። ከእርሱም ጋር ከዳን ነገድ የሆነ የአሂሳሚክ ልጅ ኤልያብ ነበረ፤ እርሱም የቅርጽ ሠራተኛና ብልህ ሠራተኛ፥ በሰማያዊ በሐምራዊም በቀይም ግምጃ፥ በጥሩም በፍታ የሚሠራ ጠላፊ ነበረ።
ያጋሩ
ዘፀአት 38 ያንብቡ