የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘፀአት 38:1-20

ዘፀአት 38:1-20 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ርዝ​መቱ አም​ስት ክንድ፥ ወር​ዱም አም​ስት ክንድ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆን መሠ​ዊ​ያን ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት አደ​ረገ፤ አራት ማዕ​ዘ​ንም ነበረ፤ ከፍ​ታ​ውም ሦስት ክንድ ነበረ። ቀን​ዶ​ቹ​ንም በአ​ራቱ ማዕ​ዘን አደ​ረ​ገ​በት፤ ቀን​ዶ​ቹም ከእ​ርሱ ጋር ሥረ-ወጥ ነበሩ፤ በና​ስም ለበ​ጠው። የመ​ሠ​ዊ​ያ​ው​ንም ዕቃ ሁሉ፥ ምን​ቸ​ቶ​ቹ​ንም፥ መጫ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ ድስ​ቶ​ቹ​ንም፥ ሜን​ጦ​ዎ​ቹ​ንም፥ የእ​ሳት ማን​ደ​ጃ​ዎ​ቹ​ንም አደ​ረገ፤ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ ከናስ አደ​ረገ። እንደ መረብ ሆኖም የተ​ሠራ የናስ መከታ ለመ​ሠ​ዊ​ያው አደ​ረገ፤ መከ​ታ​ውም እስከ መሠ​ዊ​ያው እኩ​ሌታ ይደ​ርስ ዘንድ በመ​ሠ​ዊ​ያው በሚ​ዞ​ረው በደ​ረ​ጃው ታች አደ​ረ​ገው። ለና​ሱም መከታ ለአ​ራቱ ማዕ​ዘን የመ​ሎ​ጊ​ያ​ዎች ስፍራ ይሆኑ ዘንድ አራት ቀለ​በ​ቶች አደ​ረገ። መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት ሠራ፤ በና​ስም ለበ​ጣ​ቸው። ይሸ​ከ​ሙ​ባ​ቸ​ውም ዘንድ በመ​ሠ​ዊ​ያው ጎን ባሉት ቀለ​በ​ቶች ውስጥ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹን አገባ፤ ከሳ​ን​ቃ​ዎ​ቹም ሠርቶ ክፍት አደ​ረ​ገው። የመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ውን ሰንና መቀ​መ​ጫ​ው​ንም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ከሚ​ያ​ገ​ለ​ግሉ ከሴ​ቶች መስ​ተ​ዋት ከናስ አደ​ረገ። ለድ​ን​ኳ​ኑም በደ​ቡብ በኩል በስ​ተ​ቀኝ አደ​ባ​ባይ አደ​ረገ፤ የአ​ደ​ባ​ባዩ መጋ​ረ​ጃም ከተ​ፈ​ተለ ጥሩ በፍታ የተ​ሠራ ርዝ​መቱ መቶ ክንድ ነበረ። ሃያ​ው​ንም ምሰ​ሶ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንና ሃያ​ውን እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ከናስ አደ​ረገ፤ የም​ሰ​ሶ​ዎ​ቹ​ንም ኵላ​ቦ​ችና ዘን​ጎች ከብር አደ​ረገ። በሰ​ሜ​ኑም ወገን መቶ ክንድ ርዝ​መት ያላ​ቸ​ውን መጋ​ረ​ጃ​ዎች፥ ከና​ስም የተ​ሠሩ ሃያ ምሰ​ሶ​ዎ​ች​ንና ሃያ እግ​ሮ​ችን፥ ለም​ሰ​ሶ​ዎ​ችም የብር ኵላ​ቦ​ች​ንና ዘን​ጎ​ችን አደ​ረገ። በም​ዕ​ራ​ብም ወገን አምሳ ክንድ ርዝ​መት ያላ​ቸ​ውን መጋ​ረ​ጃ​ዎች፥ ዐሥ​ሩ​ንም ምሰ​ሶ​ዎች፥ ዐሥ​ሩ​ንም የናስ እግ​ሮች፥ ለም​ሰ​ሶ​ዎ​ቹም የብር ኵላ​ቦ​ች​ንና ዘን​ጎ​ችን አደ​ረገ። በም​ሥ​ራ​ቅም ወገን አምሳ ክንድ ርዝ​መት ያላ​ቸ​ውን መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ችን አደ​ረገ። በአ​ዜብ በኩል የመ​ጋ​ረ​ጃ​ዎች ርዝ​መት ዐሥራ አም​ስት ክንድ፥ ምሰ​ሶ​ዎ​ቹም ሦስት፥ እግ​ሮ​ቹም ሦስት ነበሩ። እን​ዲ​ሁም በሁ​ለ​ተ​ኛው ወገን በአ​ደ​ባ​ባዩ ደጅ በዚ​ህና በዚያ ዐሥራ አም​ስት ክንድ ርዝ​መት ያላ​ቸው መጋ​ረ​ጃ​ዎች፥ ሦስ​ትም ምሰ​ሶ​ዎች፥ ሦስ​ትም እግ​ሮች ነበሩ። በአ​ደ​ባ​ባዩ ዙሪያ ያሉ መጋ​ረ​ጃ​ዎች ሁሉ ከተ​ፈ​ተለ ከጥሩ በፍታ ተሠ​ር​ተው ነበር። የም​ሰ​ሶ​ዎ​ቹም እግ​ሮች የናስ፥ የም​ሰ​ሶ​ዎ​ቹም ኵላ​ቦ​ችና ዘን​ጎች የብር ነበሩ፤ የም​ሰ​ሶ​ዎ​ቹም ጕል​ላ​ቶች በብር ተለ​ብ​ጠው ነበር፤ በአ​ደ​ባ​ባዩ ላሉ ምሰ​ሶ​ዎች ሁሉ የብር ዘን​ጎች ነበ​ሩ​አ​ቸው። የአ​ደ​ባ​ባ​ዩም ደጅ መጋ​ረጃ ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም፥ ከቀ​ይም ግምጃ ፥ ከጥ​ሩም በፍታ በጥ​ልፍ አሠ​ራር የተ​ሠራ ነበረ፤ ርዝ​መቱ ሃያ ክንድ ነበረ፤ ቁመ​ቱም እንደ አደ​ባ​ባዩ መጋ​ረ​ጃ​ዎች አም​ስት ክንድ ነበረ፤ ከናስ የተ​ሠሩ ምሰ​ሶ​ዎ​ቹም አራት፥ እግ​ሮ​ቹም አራት ነበሩ፤ ኵላ​ቦ​ቹም የብር ነበሩ፤ ጕል​ላ​ቶ​ቹና ዘን​ጎ​ቹም በብር ተለ​ብ​ጠው ነበር። የድ​ን​ኳ​ኑም ካስ​ማ​ዎች፥ በዙ​ሪ​ያ​ውም ያሉ የአ​ደ​ባ​ባዩ ካስ​ማ​ዎች የናስ ነበሩ።

ዘፀአት 38:1-20 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ከፍታው ሦስት ክንድ የሆነ የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያ ከግራር ዕንጨት ሠሩ፤ ርዝመቱ አምስት ክንድ፣ ወርዱ አምስት ክንድ የሆነ ባለ አራት ማእዘን ነበረ። ቀንዶቹና መሠዊያው አንድ ወጥ ይሆኑ ዘንድ በአራቱም ማእዘኖች ላይ አራት ቀንድ ሠሩ፤ መሠዊያውንም በናስ ለበጡት። ዕቃዎቹንም ሁሉ ይኸውም ምንቸቶቹን፣ መጫሪያዎቹን፣ መርጫ ጐድጓዳ ሳሕኖቹን፣ ሜንጦዎቹንና የእሳት መያዣዎቹን ከናስ ሠሯቸው። ለመሠዊያውም ከጠርዝ በታች ሆኖ ከመሠዊያው ግማሽ ቁመት ላይ የሚሆን የናስ ፍርግርግ ማንደጃ ሠሩ። ለናሱ ፍርፍርግ ማንደጃ አራት ማእዘኖች መሎጊያዎቹን እንዲይዙ የናስ ቀለበቶችን ሠሩ። መሎጊያዎቹን ከግራር ዕንጨት ሠርተው በናስ ለበጧቸው። መሠዊያውን ለመሸከም በመሠዊያው ጐኖች ይሆኑ ዘንድ መሎጊያዎቹን በቀለበቶቹ ውስጥ አስገቧቸው፤ ውስጡንም ክፍት በማድረግ ከሳንቃዎች ሠሩት። የናስ መታጠቢያ ሳሕንና የናስ መቆሚያውን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ከሚያገለግሉት ሴቶች መስተዋት ሠሩት። ቀጥሎም አደባባዩን ሠሩ፤ የደቡቡ ክፍል ርዝመት አንድ መቶ ክንድ ሲሆን፣ በቀጭኑ ከተፈተለ በፍታ የተሠሩ መጋረጃዎች ነበሩት፤ ሃያ ምሰሶዎችና ሃያ የናስ መቆሚያዎች፣ የብር ኵላቦችና በምሰሶዎቹ ላይ ዘንጎች ነበሩት። የሰሜኑም ክፍል ቁመቱ አንድ መቶ ክንድ ነበር፤ ሃያ ምሰሶዎችና ሃያ የናስ መቆሚያዎች፣ የብር ኵላቦችና በምሰሶዎቹም ላይ ዘንጎች ነበሩት። የምዕራቡ ጫፍ ወርዱ አምሳ ክንድ ነበር፤ ዐሥር ምሰሶዎችና ዐሥር መቆሚያዎች እንዲሁም የብር ኵላቦችና በምሰሶዎቹም ላይ ዘንጎች ያሉት መጋረጃዎች ነበሩት። በፀሓይ መውጫ በኩል ያለው የምሥራቁም ጫፍ ወርዱ አምሳ ክንድ ነበር። ከሦስት ምሰሶዎችና ከሦስት መቆሚያዎች ጋር ርዝመታቸው ዐሥራ አምስት ክንድ የሆኑ መጋረጃዎች በአንድ በኩል ባለው መግቢያ ላይ ነበሩ፤ ከሦስት ምሰሶዎችና ከሦስት መቆሚያዎች ጋር ርዝመታቸው ዐሥራ አምስት ክንድ የሆኑ መጋረጃዎች በአደባባዩ መግቢያ በሌላው በኩል ነበሩ። በአደባባዩ ዙሪያ ያሉት መጋረጃዎች በሙሉ በቀጭኑ ከተፈተለ በፍታ የተሠሩ ነበሩ። የምሰሶዎቹ መቆሚያዎች ናስ ነበሩ፤ ኵላቦቹና በምሰሶዎቹ ላይ ያሉት ዘንጎች ከብር የተሠሩ ነበሩ፤ ጫፎቻቸውም በብር ተለብጠው ነበር፤ ስለዚህ የአደባባዩ ምሰሶዎች ሁሉ የብር ዘንጎች ነበሯቸው። በአደባባዩ መግቢያ ላይ ያለው መጋረጃ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና የጥልፍ ባለሙያ ከጠለፈው፣ በቀጭኑ ከተፈተለ በፍታ የተሠራ ነበር፤ ቁመቱ ሃያ ክንድ፣ እንደ አደባባዩ መጋረጃዎች ከፍታው አምስት ክንድ ነበረ፤ አራት ምሰሶዎችና አራት መቆሚያዎች ነበሩት፤ ኵላቦቻቸውና ዘንጎቻቸው የብር ሲሆኑ፣ ጫፎቻቸው በብር ተለብጠው ነበር። የማደሪያው ድንኳንና የአደባባዩ ዙሪያ ካስማዎች ሁሉ ከናስ የተሠሩ ነበሩ።

ዘፀአት 38:1-20 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ርዝመቱ አምስት ክንድ፥ ወርዱም አምስት ክንድ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆን መሠዊያን ከግራር እንጨት አደረገ፤ አራት ማዕዘንም ነበረ፤ ከፍታው ሦስት ክንድ ነበረ። ቀንዶቹንም በአራቱ ማዕዘን አደረገበት፤ ቀንዶቹም ከእርሱ ጋር በአንድ የተሠሩ ነበሩ፤ በናስም ለበጠው። የመሠዊያውንም ዕቃ ሁሉ፥ ምንቸቶቹንም፥ መጫሪያዎቹንም፥ ድስቶቹንም፥ ሜንጦቹንም፥ ማንደጃዎቹንም አደረገ፤ ዕቃውንም ሁሉ ከናስ አደረገ። እንደ መረብ ሆኖም የተሠራ የናስ መከታ ለመሠዊያ አደረገ፤ መከታውም እስከ መሠዊያው እኩሌታ ይደርስ ዘንድ በመሠዊያው በሚዞረው በደረጃው ታች አደረገው። ለናሱም መከታ ለአራቱ ማዕዘን የመሎጊያዎች ስፍራ ይሆኑ ዘንድ አራት ቀለበቶች አደረገ። መሎጊያዎቹንም ከግራር እንጨት ሠራ፥ በናስም ለበጣቸው። ይሸከሙትም ዘንድ በመሠዊያ ጎን ባሉት ቀለበቶች ውስጥ መሎጊያዎቹን አገባ፤ ከሳንቆቹም ሠርቶ ባዶ አደረገው። የመታጠቢያውን ሰንና መቀመጫውንም በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ከሚያገለግሉ ከሴቶች መስተዋት ከናስ አደረገ። አደባባዩንም አደረገ፤ በደቡብ ወገን ርዝመቱ መቶ ክንድ የሆነ፥ የተፈተለ የጥሩ በፍታ መጋረጆች ነበሩ። ከናስ የተሠሩ ሀያውን ምሰሶችና ሀያውን እግሮች አደረገ፤ የምሰሶቹንም ኩላቦችና ዘንጎች ከብር አደረገ። በሰሜኑም ወገን መቶ ክንድ ርዝመት ያላቸውን መጋረጆች፥ ከናስም የተሠራ ሀያ ምሰሶችንና ሀያ እግሮችን፥ ለምሰሶቹም የብር ኩላቦችንና ዘንጎችን አደረገ። በምዕራብም ወገን አምሳ ክንድ ርዝመት ያላቸውን መጋረጆች፥ አሥሩንም ምሰሶች፥ አሥሩንም የናስ እግሮች፥ ለምሰሶቹም የብር ኩላቦችንና ዘንጎችን አደረገ። በምሥራቅም ወገን አምሳ ክንድ ርዝመት ያላቸውን መጋረጆች አደረገ። በአንድ ወገንም የመጋረጆቹ ርዝመት አሥራ አምስት ክንድ፥ ምሰሶቹም ሦስት፥ እግሮቹም ሦስት ነበሩ። እንዲሁም በሁለተኛው ወገን በአደባባዩ ደጅ በዚህና በዚያ አሥራ አምስት ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጆች፥ ሦስትም ምሰሶች፥ ሦስትም እግሮች ነበሩ። በአደባባዩ ዙሪያ ያሉ መጋረጆች ሁሉ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ ተሠርተው ነበር። የምሰሶቹም እግሮች የናስ፥ የምሰሶቹም ኩላቦችና ዘንጎች የብር ነበሩ፤ የምሰሶችም ጉልላቶች በብር ተለብጠው ነበር፤ በአደባባዩ ላሉ ምሰሶች ሁሉ የብር ዘንጎች ነበሩአቸው። የአደባባዩም ደጅ መጋረጃ ከሰማያዊ ከሐምራዊም ከቀይም ግምጃ፥ ከጥሩም በፍታ በጥልፍ አሠራር የተሠራ ነበረ፤ ርዝመቱ ሀያ ክንድ ነበረ፥ ቁመቱም እንደ አደባባዩ መጋረጆች አምስት ክንድ ነበረ፤ ከናስ የተሠሩ ምሰሶቹም አራት፥ እግሮቹም አራት ነበሩ፤ ኩላቦቹ የብር ነበሩ፤ ጉልላቶቹና ዘንጎቹም በብር ተለብጠው ነበር። የማደሪያውም ካስማዎች በዙሪያውም ያለ የአደባባዩ ካስማዎች የናስ ነበሩ።

ዘፀአት 38:1-20 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያ ከግራር እንጨት ሠራ፤ እርሱም አራት ማእዘን ሆኖ ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር ርዝመት፥ ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር ስፋት፥ አንድ ሜትር ከሠላሳ ሳንቲ ሜትር ቁመት ነበረው፤ ከመሠዊያው ጋር አንድ ወጥ ሆነው የተሠሩ ጒጦችንም በአራቱ ማእዘን አደረገበት ሁሉንም በነሐስ ለበጠው። በመሠዊያው ላይ ያሉትንም የመገልገያ ዕቃዎች፥ ድስቶችንም፥ የእሳት መጫሪያዎቹንም፥ ጐድጓዳ ሳሕኖችንም፥ ሜንጦዎቹንም፥ ማንደጃዎቹንም ከነሐስ ሠራ፤ መረብ የሚመስል የነሐስ መከላከያ ሠራ፤ እርሱንም እስከ መሠዊያ ግማሽ ቁመት እንዲደርስ አድርጎ በመሠዊያው ክፈፍ ሥር አኖረው፤ ለመሸከሚያ የሚያገለግሉ መሎጊያዎች መሹለኪያ ይሆኑ ዘንድ አራት ቀለበቶችን ሠርቶ በአራቱ ማእዘኖች ላይ አደረጋቸው። መሎጊያዎችንም ከግራር እንጨት ሠርቶ በነሐስ ለበጣቸው። በመሠዊያው ጐንና ጐን ባሉት ቀለበቶችም ውስጥ አስገባቸው፤ መሠዊያው ከሳንቃ የተሠራ ሆኖ ውስጡ ክፍት ነበር። የመታጠቢያውን ሳሕንና ማስቀመጫውን ጭምር ከነሐስ ሠራ፤ ነሐሱም የተገኘው በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ የሚያገለግሉ ሴቶች ካመጡት የነሐስ መስተዋቶች ነው። ለተቀደሰው ድንኳን መግቢያ ክፍል መጋረጃዎችን ከጥሩ በፍታ ሠራ፤ የመጋረጃዎቹም ርዝመት በደቡብ በኩል አርባ አራት ሜትር ነበር፤ መጋረጃዎችን የሚደግፉ ኻያ ምሰሶዎችንና ኻያ እግሮቻቸውን ከነሐስ ሠራ፤ የምሰሶዎቹንም ኩላቦችና ዘንጎች ከብር ሠራ፤ ከሰሜንም በኩል የአደባባዩ አሠራር እንደዚሁ ነበር፤ በምዕራብ በኩል ኻያ ሁለት ሜትር ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች ነበሩ፤ እነርሱም ዐሥር እግሮች ያሉአቸው ዐሥር ምሰሶዎች ነበሩአቸው፤ ምሰሶዎቹም ከብር የተሠሩ ኩላቦችና ዘንጎች ነበሩአቸው። የመግቢያው ደጅ ባለበት በምሥራቅ በኩል የአደባባዩ ስፋት ኻያ ሁለት ሜትር ነበር። በአንድ በኩል ያለው የበሩ መጋረጃ ስድስት ሜትር ከስድሳ ሳንቲ ሜትር ተኩል ርዝመት፥ ሦስት ምሰሶዎችና ሦስት እግሮችም ነበሩት። እንዲሁም በሌላው በኩል በአደባባዩ ደጅ በዚህና በዚያ ስድስት ሜትር ከስድሳ ሳንቲ ሜትር ርዝመት፥ ሦስት ምሰሶዎችና ሦስት እግሮች ነበሩት። በድንኳኑ መግቢያ ዙሪያ ያሉት መጋረጃዎች ሁሉ ከጥሩ በፍታ የተሠሩ ነበሩ፤ የምሰሶዎቹ እግሮች የተሠሩት ከነሐስ ነበር፤ ኩላቦቹ ዘንጎቹና የምሰሶዎቹ ጫፎች መሸፈኛዎች ከብር የተሠሩ ነበሩ፤ በአደባባዩ ዙሪያ ያሉት ምሰሶዎች ሁሉ በብር ዘንጎች የተያያዙ ነበሩ፤ ወደ ድንኳኑ የሚያስገባው ደጃፍ መጋረጃ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ በፍታ ተፈትሎ በእጅ ጥበብ ካጌጠ ቀጭን ሐር የተሠራ ነበር፤ እርሱም እንደ ድንኳኑ በር መግቢያ መጋረጃዎች ሁሉ ርዝመቱ ዘጠኝ ሜትር ቁመቱም ሁለት ሜትር ነበር፤ አራት የነሐስ እግሮች ባሉአቸው አራት ምሰሶዎች ተደግፎ ነበር፤ ኩላቦቻቸው፥ ጫፎቻቸውና ዘንጎቻቸው ከብር የተሠሩ ነበሩ፤ ለድንኳኑና በዙሪያው ላለው የአደባባይ አጥር መጋረጃዎች የሚያገለግሉት ካስማዎች ሁሉ የተሠሩት ከነሐስ ነበር።

ዘፀአት 38:1-20 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያ ከግራር እንጨት ሠራ፤ እርሱም ርዝመቱ አምስት ክንድ፥ ወርዱ አምስት ክንድ ነበር፥ አራት ማዕዘንም ነበረ፥ ከፍታው ሦስት ክንድ ነበረ። በአራቱም ማዕዘን ቀንዶችን አደረገበት፤ ቀንዶቹም ከእርሱ ጋር ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበሩ፤ በነሐስም ለበጠው። የመሠዊያውን ዕቃዎች በሙሉ፥ ምንቸቶቹን፥ መጫሪያዎቹን፥ ጐድጓዳ ሳሕኖቹን፥ ሜንጦቹን፥ ማንደጃዎቹን ሠራ፤ ዕቃዎቹን በሙሉ ከነሐስ ሠራ። ለመሠዊያውም መረብ የሚመስል የነሐስ መከታ ከጠርዙ በታች እስከ መሠዊያው ግማሽ ድረስ ሠራለት። ለነሐሱ መከታ አራቱ ማዕዘኖች ለመሎጊያዎቹ ማስገቢያ እንዲሆኑ አራት ቀለበቶችን አደረገ። መሎጊያዎቹን ከግራር እንጨት ሠራ፥ በነሐስም ለበጣቸው። እንዲሸከሙትም መሎጊያዎቹን በመሠዊያው ጎን ባሉት ቀለበቶች ውስጥ አስገባ፤ ክፍትም አድርጎ ከሳንቃዎች ሠራው። የነሐሱ የመታጠቢያ ሳሕንና የነሐሱ ማስቀመጫውን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ከሚያገለግሉ ሴቶች መስተዋት ሠራ። አደባባዩንም ሠራ፤ በደቡብ በኩል የአደባባዩ መጋረጃዎች ርዝመቱ መቶ ክንድ የሆነ፥ ከጥሩ በፍታ የተፈተለ ነበር። ምሰሶዎቻቸው ሃያ፥ የነሐስ እግሮቻቸውም ሃያ ነበሩ፥ የምሰሶዎቹ ኩላቦችና ዘንጎች ከብር የተሰሩ ነበሩ። በሰሜን በኩል መቶ ክንድ ርዝመት ያላቸውን መጋረጃዎች፥ ምሰሶዎቻቸው ሃያ የነሐስ እግሮቻቸውም ሃያ ነበሩ፥ የምሰሶዎቹ ኩላቦችና ዘንጎች ከብር የተሰሩ ነበሩ። በምዕራብ በኩል አምሳ ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች ነበሩ፤ ዐሥር ምሰሶዎችና ዐሥር የነሐስ እግሮች ነበሩት፥ የምሰሶዎቹ ኩላቦችና ዘንጎች ከብር የተሰሩ ነበሩ። በምሥራቅም በኩል አምሳ ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች ነበሩ። በአንድ በኩል የመጋረጃዎቹ ርዝመት ዐሥራ አምስት ክንድ ነበረ፥ ሦስት ምሰሶዎች እና ሦስት እግሮች ነበሩ። በሁለተኛው በኩል በአደባባዩ መግቢያ በዚህና በዚያ ዐሥራ አምስት ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች፥ ሦስት ምሰሶዎች እና ሦስት እግሮች ነበሩ። በአደባባዩ ዙሪያ ያሉት መጋረጃዎች በሙሉ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ የተሠሩ ነበሩ። የምሰሶዎቹ እግሮች ከነሐስ የተሠሩ፥ የምሰሶዎቹ ኩላቦችና ዘንጎች ከብር የተሠሩ ነበሩ፤ የምሰሶዎቹ ጉልላቶች በብር ተለብጠው ነበር፤ በአደባባዩ ያሉ ምሰሶዎች ሁሉ የብር ዘንጎች ነበሩአቸው። የአደባባዩ መግቢያ መጋረጃ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃና ከጥሩ በፍታ የተጠለፈ ነበረ፤ ርዝመቱ ሀያ ክንድ፥ ቁመቱ እንደ አደባባዩ መጋረጃዎች አምስት ክንድ ነበረ፤ ምሰሶዎቹ አራት ነበሩ፤ ከነሐስ የተሠሩ እግሮች አራት፥ ኩላቦቹ ከብር የተሠሩ ነበሩ፥ ጉልላቶቻቸውና ዘንጎቻቸው በብር ተለብጠው ነበር። የማደሪያውና በዙሪያው ያለ የአደባባዩ ካስማዎች ሁሉ ከነሐስ የተሠሩ ነበሩ።