ዘፀአት 35:4-29

ዘፀአት 35:4-29 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ሙሴም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ አላ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ ያዘ​ዘው ነገር ይህ ነው፤ ከእ​ና​ንተ ዘንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍር​ባ​ንን አቅ​ርቡ፤ የልብ ፈቃድ ያለው ከገ​ን​ዘቡ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያምጣ፤ ወር​ቅና ብር፥ ናስም፤ ሰማ​ያ​ዊም፥ ሐም​ራ​ዊም፥ ድርብ ቀይ ግም​ጃም፥ የተ​ፈ​ተለ በፍ​ታም፥ የፍ​የል ጠጕ​ርም፤ ቀይ ቀለ​ምም የገ​ባ​በት የአ​ውራ በግ ቍር​በት፥ የአ​ቆ​ስ​ጣም ቍር​በት፥ የማ​ይ​ነ​ቅ​ዝም ዕን​ጨት፤ ለመ​ብ​ራ​ትም ዘይት፥ ለቅ​ብ​ዐት ሽቱን፥ ለማ​ዕ​ጠ​ንት ዕጣ​ንን፤ የመ​ረ​ግድ ድን​ጋ​ይና የተ​ቀ​ረጸ ድን​ጋይ፥ ለል​ብሰ መት​ከ​ፍና ለል​ብሰ እን​ግ​ድዓ የሚ​ደ​ረግ ፈርጥ ያምጣ። “በእ​ና​ንተ ዘንድ ያለ፥ በልቡ ጥበ​በኛ የሆነ ሁሉ መጥቶ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ ያድ​ርግ። ድን​ኳ​ኑ​ንም፥ አደ​ባ​ባ​ዩ​ንም፥ መደ​ረ​ቢ​ያ​ው​ንም፥ መያ​ዣ​ዎ​ቹ​ንም፥ ሳን​ቆ​ቹ​ንም፥ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ ምሰ​ሶ​ዎ​ች​ንና እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን፤ የቃል ኪዳ​ኑን ታቦ​ትም፥ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ የስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ው​ንም፥ መጋ​ረ​ጃ​ው​ንም፤ ገበ​ታ​ው​ንና መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ፥ ኅብ​ስተ ገጹ​ንም፤ መብ​ራት የሚ​ያ​በ​ሩ​በ​ትን መቅ​ረ​ዙን፥ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ፥ ቀን​ዲ​ሉ​ንም፥ የመ​ብ​ራ​ቱ​ንም ዘይት፤ የዕ​ጣ​ኑ​ንም መሠ​ዊያ፥ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ የቅ​ብ​ዐ​ቱ​ንም ዘይት፥ ጣፋ​ጩ​ንም ዕጣን፥ ለማ​ደ​ሪ​ያ​ውም ደጃፍ የሚ​ሆን የደ​ጃ​ፉን መጋ​ረጃ፤ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን መሠ​ዊ​ያ​ውን፥ የና​ሱ​ንም መከታ፥ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ፥ የመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ውን ሰንም፥ መቀ​መ​ጫ​ው​ንም፤ የአ​ደ​ባ​ባ​ዩን መጋ​ረ​ጆች፥ ምሰ​ሶ​ዎ​ች​ንም፥ እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ የአ​ደ​ባ​ባ​ዩ​ንም ደጃፍ መጋ​ረጃ፤ የማ​ደ​ሪ​ያ​ውን ካስ​ማ​ዎች፥ የአ​ደ​ባ​ባ​ዩ​ንም ካስ​ማ​ዎች፥ አው​ታ​ሮ​ቻ​ቸ​ው​ንም፤ በመ​ቅ​ደስ ውስጥ ለማ​ገ​ል​ገል በብ​ል​ሃት የተ​ሠ​ሩ​ትን ልብ​ሶች፥ በክ​ህ​ነት ያገ​ለ​ግ​ሉ​በት ዘንድ የተ​ቀ​ደ​ሱ​ትን የካ​ህ​ኑን የአ​ሮ​ንን ልብ​ሶች፥ የል​ጆ​ቹ​ንም ልብ​ሶች።” የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ከሙሴ ዘንድ ወጡ። ከእ​ነ​ር​ሱም ሰው ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ ልቡ እን​ዳ​ነ​ሣ​ሣው፥ መን​ፈ​ሱም እሺ እን​ዳ​ሰ​ኘው ለም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ሥራ ለማ​ገ​ል​ገ​ያ​ውም ሁሉ ለመ​ቅ​ደስ ልብስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስጦታ አመጡ። ወን​ዶ​ችና ሴቶ​ችም ልባ​ቸው እንደ ፈቀደ ማር​ዳ​ዎ​ችን፥ ሎቲ​ዎ​ች​ንም፥ ቀለ​በ​ቶ​ች​ንም፥ ድሪ​ዎ​ች​ንም፥ የወ​ርቅ ጌጦ​ች​ንም ሁሉ አመጡ፤ ሰዎ​ችም ሁሉ የወ​ርቅ ስጦታ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቀ​ረቡ። ሰማ​ያ​ዊም፥ ሐም​ራ​ዊም፥ ቀይ ግም​ጃም፥ የተ​ፈ​ተለ በፍ​ታም፥ የፍ​የል ጠጕ​ርም፥ ቀይ የአ​ውራ በግ ቍር​በ​ትም፥ የአ​ቆ​ስጣ ቍር​በ​ትም ያላ​ቸው ሰዎች ሁሉ አመጡ። ስዕ​ለት የተ​ሳለ ሁሉ፥ የብ​ር​ንም፥ የና​ስ​ንም ስጦታ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍር​ባን አቀ​ረበ፤ የማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት ያለው ሁሉ ለድ​ን​ኳኑ ማገ​ል​ገያ ለሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ገው ሥራ አመጣ። በል​ባ​ቸው ጥበ​በ​ኞች የሆኑ ሴቶ​ችም በእ​ጃ​ቸው ፈተሉ፤ የፈ​ተ​ሉ​ት​ንም ሰማ​ያ​ዊ​ውን፥ ሐም​ራ​ዊ​ው​ንም፥ ቀዩ​ንም ግምጃ፥ ጥሩ​ው​ንም በፍታ አመጡ። ልባ​ቸ​ውም በጥ​በብ ያስ​ነ​ሣ​ቸው ሴቶች ሁሉ የፍ​የ​ልን ጠጕር ፈተሉ። አለ​ቆ​ችም የመ​ረ​ግድ ድን​ጋ​ይና የተ​ቀ​ረጸ ድን​ጋ​ይን ለል​ብሰ መት​ከ​ፍና ለል​ብሰ እን​ግ​ድዓ የሚ​ገ​ቡ​ት​ንም ፈር​ጦ​ችን፥ ለመ​ብ​ራ​ትም፥ ለቅ​ብ​ዐት ዘይ​ትም፥ ለጣ​ፋጭ ዕጣ​ንም ሽቱ​ንና ዘይ​ትን አመጡ። ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም ያመጡ ዘንድ ልባ​ቸው ያስ​ነ​ሣ​ቸው ወን​ዶ​ችና ሴቶች ሁሉ ሙሴ ይሠራ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላዘ​ዘው ሥራ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስጦታ በፈ​ቃ​ዳ​ቸው አመጡ።

ዘፀአት 35:4-29 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ሙሴ ለእስራኤላውያን ማኅበረ ሰብ ሁሉ እንዲህ አላቸው፤ “እግዚአብሔር ያዘዘው ይህ ነው፤ ካላችሁ ንብረት ሁሉ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቅርቡ፤ ፈቃደኛ የሆነ ማንም ለእግዚአብሔር፦ “የወርቅ፣ የብር፣ የናስ መባ ያምጣ። ሰማያዊ፣ ሐምራዊና ቀይ ማግ፤ ቀጭን ሐር፣ የፍየል ጠጕር፣ ቀይ የተነከረ የአውራ በግ ቈዳ፣ እንዲሁም የለፋ ቈዳ፣ የግራር ዕንጨት፤ ለመብራት የወይራ ዘይት፣ ለቅብዐ ዘይቱና ለጣፋጭ መዐዛ ላለው ዕጣን የሚሆኑ ቅመሞች፤ በኤፉዱና በደረት ኪስ ላይ የሚሆኑ መረግዶችና ሌሎች ዕንቍዎችን መባ አድርጎ ያምጣ። “በመካከላችሁ ጥበበኞች የሆኑ ሁሉ መጥተው እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ ይሥሩ፦ “የመገናኛውን ድንኳን ከነድንኳኑና ከነመደረቢያው፣ ማያያዣዎችን፣ ክፈፎችን፣ አግዳሚዎችን፣ ቋሚዎችንና መሠረቶችን፤ ታቦቱን ከነመሎጊያዎቹ፣ የስርየት መክደኛውንና የሚሸፍነውን መጋረጃ፤ ጠረጴዛውን ከነመሎጊያዎቹ፣ ዕቃዎቹን ሁሉና የገጸ ኅብስቱን፤ ለመብራት የሆነውን መቅረዝ ከነዕቃዎቹ፣ ቀንዲሎችንና ለመብራት የሚሆነውን ዘይት፤ የዕጣን መሠዊያውን ከነመሎጊያዎቹ፣ ቅብዐ ዘይቱንና ጣፋጭ ሽታ ያለውን ዕጣን፤ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ የሚሆነውን የመግቢያ መጋረጃ፤ የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያውን ከንሓስ መጫሪያው፣ መሎጊያዎቹንና ዕቃዎቹን ሁሉ፣ የንሓስ ሰኑን ከነማስቀመጫው፣ የአደባባዩን መጋረጃዎች ከነምሰሶዎቻቸውና ከነመሠረቶቹ፣ የአደባባዩን መግቢያ መጋረጃ፤ ለመገናኛው ድንኳንና ለአደባባዩ የሚሆኑ የድንኳን ካስማዎችና ገመዶቻቸው፤ በመቅደሱ ውስጥ ለማገልገል የሚለበሱ የፈትል ልብሶችን ይኸውም የካህኑ የአሮንን የተቀደሱ ልብሶችንና ካህናት ሆነው ሲያገለግሉ የሚለብሷቸውን የወንዶች ልጆቹን ልብሶች ይሥሩ።” ከዚያም የእስራኤል ማኅበረ ሰብ ሁሉ ከሙሴ ፊት ወጡ፤ ፈቃደኛ የነበረና ልቡን ያነሣሣው ሁሉ በመምጣት ለመገናኛው ድንኳን ሥራ፣ ለአገልግሎቱ ሁሉና ለተቀደሱ ልብሶች የሚሆን ለእግዚአብሔር መባ አመጡ። ፈቃደኛ የነበሩ ሁሉ፣ ወንዶችም ሴቶችም መጥተው ከሁሉም ዐይነት የወርቅ ጌጦች አመጡ፤ የአፍንጫ ጌጦችን፣ ሎቲዎችን፣ ቀለበቶችን፣ ድሪዎችንና ጌጣጌጦችን ሁሉ አመጡ፤ ሁሉም ወርቃቸውን እንደሚወዘወዝ መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቀረቡ። ሰማያዊ፣ ሐምራዊ ወይም ቀይ ማግ ወይም ቀጭን ሐር ወይም የፍየል ጠጕር፣ ቀይ የተነከረ የአውራ በግ ቈዳ ወይም የአቆስጣ ቈዳ አመጡ። የብር ወይም የናስ መባ ማቅረብ የቻሉ ሁሉ ለእግዚአብሔር መባ አድርገው አመጡ፤ የግራር ዕንጨት ያለው ሁሉ አስፈላጊ በሆነው ሥራ እንዲውል አመጣው። ጥበበኞች የሆኑ ሴቶች ሁሉ በእጃቸው ፈተሉ፤ የፈተሉትንም ሰማያዊ ሐምራዊ ወይም ቀይ ማግ ወይም ቀጭን በፍታ አመጡ። ፈቃደኛ የነበሩና ጥበቡ ያላቸው ሴቶች ሁሉ የፍየል ጠጕር ፈተሉ። መሪዎቹም ኤፉድና በደረት ኪሱ ላይ እንዲሆን የከበሩ ድንጋዮችንና ሌሎች ዕንቍዎች አመጡ። እንዲሁም ለመብራቱ፣ ለቅብዐ ዘይቱና ለጣፋጭ ሽታ ዕጣን የሚሆኑ ቅመሞችንና የወይራ ዘይትን አመጡ። ፈቃደኛ የሆኑ እስራኤላውያን ወንዶችና ሴቶች ሁሉ፣ እግዚአብሔር በሙሴ በኩል እንዲያከናውኑት ላዘዛቸው ሥራ ሁሉ የበጎ ፈቃድ ስጦታዎችን ለእግዚአብሔር አመጡ።

ዘፀአት 35:4-29 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ሙሴም ለእስራኤል ልጆች ማህበር ሁሉ አላቸው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ያዘዘው ነገር ይህ ነው፤ ከእናንተ ዘንድ ለእግዚአብሔር ቁርባንን አቅርቡ፤ የልብ ፈቃድ ያለው የእግዚአብሔርን ቁርባን ያምጣ፤ ወርቅና ብርም ናስም፤ ሰማያዊም ሐምራዊም ቀይ ግምጃም፥ ጥሩ በፍታም፥ የፍየል ጠጉርም፤ ቀይም የአውራ በግ ቁርበት፥ የአቆስጣም ቁርበት፥ የግራርም እንጨት፤ ለመብራትም ዘይት፥ ለቅብዓት ዘይትና ለጣፋጭ ዕጣን ቅመም፤ መረግድ ለኤፉዱና ለደረት ኪስ የሚደረግ ፈርጥ ያምጣ። በእናንተም ዘንድ ያሉ በልባቸው ጥበበኞች ሁሉ መጥተው እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ ያድርጉ። ማደሪያውን፥ ድንኳኑንም መደረቢያውንም፥ መያዣዎቹንም፥ ሳንቆቹንም፥ መወርወሪያዎቹንም፥ ምሰሶቹንም፥ እግሮቹንም፤ ታቦቱን መሎጊያዎቹንም፥ የስርየት መክደኛውንም በእርሱም ፊት የሚሸፍነውን መጋረጃ፤ ገበታውን መሎጊያዎቹንም ዕቃውንም ሁሉ፥ የገጹንም ኅብስት፤ መብራት የሚያበሩበትን መቅረዙን ዕቃውንም፥ ቀንዲሉንም፥ የመብራቱንም ዘይት፤ የዕጣኑን መሠዊያም መሎጊያዎቹንም፥ የቅብዓቱንም ዘይት፥ ጣፋጩንም ዕጣን፥ ለማደሪያውም ደጃፍ የሚሆን የደጃፉን መጋረጃ፤ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውን መሠዊያውን፥ የናሱንም መከታ፥ መሎጊያዎቹንም፥ ዕቃውንም ሁሉ፤ የመታጠቢያውን ሰንም መቀመጫውንም፤ የአደባባዩን መጋረጆች ምሰሶቹንም እግሮቻቸውንም፥ የአደባባዩንም ደጃፍ መጋረጃ፤ የማደሪያውን ካስማዎች፥ የአደባባዩንም ካስማዎች አውታሮቻቸውንም፤ በመቅደስ ውስጥ ለማገልገል በብልሃት የተሠሩትን ልብሶች፥ በክህነት ያገለግሉበት ዘንድ የተቀደሱትን የካህኑን የአሮን ልብሶች፥ የልጆቹንም ልብሶች። የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ ከሙሴ ፊት ወጡ። ከእነርሱም ሰው ሁሉ ልቡ እንዳነሣሣው መንፈሱም እሺ እንዳሰኘው ለመገናኛው ድንኳን ሥራ ለማገልገያውም ሁሉ ለተቀደሰውም ልብስ ለእግዚአብሔር ስጦታ አመጡ። ወንዶችና ሴቶችም ልባቸው እንደ ፈቀደ ማርዳዎችን፥ ሎቲዎችንም፥ ቀለበቶችንም፥ ድሪዎችንም፥ የወርቅ ጌጦችንም ሁሉ አመጡ፤ ሰዎችም ሁሉ የወርቅ ስጦታ ወደ እግዚአብሔር አቀረቡ። ሰማያዊም ሐምራዊም ቀይ ግምጃም፥ ጥሩ በፍታም፥ የፍየል ጠጉርም፥ ቀይ የአውራ በግ ቁርበትም፥ የአቆስጣ ቁርበትም ያላቸው ሰዎች ሁሉ አመጡ። ስእለት የተሳለ ሁሉ የብርንም የናስንም ስጦታ ለእግዚአብሔር ቁርባን አቀረበ፤ የግራርም እንጨት ያለው ሁሉ ለማገልገያ ሥራ አመጣ። በልባቸው ጥበበኞች የሆኑ ሴቶችም በእጃቸው ፈተሉ፥ የፈተሉትንም ሰማያዊውን ሐምራዊውንም ቀዩንም ግምጃ፥ ጥሩውንም በፍታ አመጡ። ልባቸውም በጥበብ ያስነሣቸው ሴቶች ሁሉ የፍየልን ጠጕር ፈተሉ። አለቆችም መረግድን፥ ለኤፉድና ለደረት ኪስ የሚገቡትንም ፈርጦችን፥ ለመብራትም ለቅብዓት ዘይትም ለጣፋጭ ዕጣንም ሽቱንና ዘይትን አመጡ። ከእስራኤል ልጆችም ያመጡ ዘንድ ልባቸው ያስነሣቸው ወንዶችና ሴቶች ሁሉ ሙሴ ይሠራ ዘንድ እግዚአብሔር ላዘዘው ሥራ ሁሉ ለእግዚአብሔር ስጦታ በፈቃዳቸው አመጡ።

ዘፀአት 35:4-29 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ሙሴ ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር ያዘዘው ነገር ይህ ነው፤ ለእግዚአብሔር መባ አቅርቡ፤ መባ ለማቅረብ የፈለገ ሁሉ እያንዳንዱ ልቡ የፈቀደውን ያኽል የወርቅ፥ የብር፥ ወይም የነሐስ ጥሩ ከፈይ ሰማያዊ፥ ሐምራዊና ቀይ ቀለም የተነከረ የበግ ጠጒር፥ ከፍየል ጠጒር የተሠራ ልብስ፥ ቀይ ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳ፤ የለፋ ቊርበት፥ የግራር እንጨት፥ ለመብራት የሚሆን የወይራ ዘይት፥ ለቅባት ዘይትና ለዕጣን ሽታ የሚሆን ቅመማ ቅመም፥ በተቀደሰው ኤፉድና የደረት ኪስ ላይ የሚሆን መረግድና ሌላውንም ጌጠኛ ፈርጥ ያምጣ። “በመካከላችሁ የሚገኙ የእጅ ጥበብ ዐዋቂዎች ሁሉ እግዚአብሔር ያዘዘውን ማናቸውንም ነገር ለመሥራት ይምጡ፤ ይኸውም ድንኳኑን፥ የውስጥና የውጪ መደረቢያዎችን፥ መያዣዎችንና ተራዳዎችን መወርወሪያዎችንና ምሰሶዎችን፥ እግሮቹን፥ የኪዳኑን ታቦት፥ መሎጊያዎቹን፥ የስርየት መክደኛውንና የታቦቱ መሸፈኛ የሆነውን መጋረጃ፥ ጠረጴዛውን፥ መሎጊያዎቹንና የእርሱንም መገልገያ ዕቃዎች ሁሉ እንዲሁም ለእግዚአብሔር የሚቀርበውን የተቀደሰ ኅብስት ለመብራት ማኖሪያ የሚሆነውን መቅረዝና የእርሱንም መገልገያ ዕቃዎች፥ መብራቶቹም ከዘይታቸው ጋር፥ የዕጣን መሠዊያውንና መሎጊያዎቹን፥ የቅባቱን ዘይት፥ ጣፋጭ ሽታ ያለውን ዕጣን፥ የድንኳኑን በር መጋረጃ፥ የሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርብበትን መሠዊያ፥ የነሐሱንም መከላከያ መሎጊያዎቹንና የእርሱን መገልገያ ዕቃዎች ሁሉ፥ የመታጠቢያውን ሳሕንና ማስቀመጫውን፥ ያደባባዩን መጋረጃዎች፥ ምሰሶዎቹንና እግሮቻቸውን፥ የአደባባዩን በር መጋረጃዎች፥ የድንኳኑንና የአደባባዩን ካስማዎች፥ አውታሮችና ካህናቱ በተቀደሰው ስፍራ በሚያገለግሉበት ጊዜ የሚለብሱአቸው በጥበብ ያጌጡ ልብሶችን ይኸውም ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹ የተሠሩትን የተቀደሱ ልብሶች ይሥሩ።” ከዚህ በኋላም የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ከሙሴ ፊት ወጡ፤ ለመሥራት እያንዳንዱ ለመስጠት ልቡ የፈቀደውን ለእግዚአብሔር መባ አመጣ፤ በዚህም ዐይነት እስራኤላውያን ለመንፈሳዊ አገልግሎት ለካህናት ልብስ የሚሆነውን ነገር ሁሉ አመጡ። ስጦታ ማቅረብ የፈለገ ሴቱም ወንዱም እያንዳንዱ የደረት ጌጥ፥ የጆሮ ወርቅ፥ የጣት ቀለበት፥ ድሪዎችና የወርቅ ጌጦችን አምጥቶ ለእግዚአብሔር የተለዩ እንዲሆኑ አደረገ። ጥሩ በፍታ፥ ሰማያዊ፥ ሐምራዊና ቀይ ከፈይ ከፍየል ጠጒር የተሠራ ልብስ፥ ቀይ ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳ፤ እንዲሁም የለፋ ቊርበት ያለው ሁሉ ይዞ መጣ። ብር ወይም ነሐስ ለማቅረብ ችሎታ ያላቸውም ሁሉ ስጦታቸውን ለእግዚአብሔር አመጡ፤ ለማንኛውም አገልግሎት የሚውል የግራር እንጨት ያለውም አመጣ። የእጅ ጥበብ ችሎታ ያላቸው ሴቶችም በእጃቸው የሠሩትን ጥሩ በፍታና ሰማያዊ፥ ሐምራዊና ቀይ ከፈይ ይዘው መጡ፤ እንዲሁም ስጦታ ለማቅረብ የፈለጉ ሴቶች ከፍየል ጠጒር የተገመደ ክር ሠሩ፤ አለቆችም በተቀደሰው ኤፉድና በደረት ኪስ ላይ የሚሆኑ መረግድና ሌሎችም ጌጣጌጦች፥ ለመብራትና ለቅባት እንዲሁም ጣፋጭ ሽታ ለሚሰጥ ዕጣን የሚሆን ቅመማ ቅመምና ዘይት አመጡ፤ ወንዶችና ሴቶች የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ እግዚአብሔር ሙሴን ላዘዘው ሥራ የሚውል ልባቸው የፈቀደውን ስጦታ ለእግዚአብሔር አመጡ።

ዘፀአት 35:4-29 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ሙሴ ለእስራኤል ልጆች ማህበር ሁሉ እንዲህ አለ፦ “ጌታ ያዘዘው ነገር ይህ ነው፥ እንዲህ በማለት፥ ለጌታ ከእናንተ ዘንድ መባን አቅርቡ፤ የልብ መነሣሣት ያለው ሁሉ ለጌታ መባ ያምጣ፤ ወርቅ፥ ብር፥ ነሐስ፥ ሰማያዊ፥ ሐምራዊና ቀይ ግምጃ፥ ጥሩ በፍታ፥ የፍየል ጠጉር፥ ቀይ የአውራ በግ ቁርበት፥ የአቆስጣ ቁርበት፥ የግራር እንጨት፤ ለመብራት የሚሆን ዘይት፥ ለቅባት የሚሆን ዘይትና ለጣፋጭ ዕጣን የሚሆን ቅመም፥ መረግድ፥ ለኤፉድና ለደረት ኪስ የሚደረግ ፈርጥ ያምጣ። “በእናንተ መካከል ያሉ በልባቸው ጥበበኞች የሆኑ ሁሉ መጥተው ጌታ ያዘዘውን ሁሉ ያድርጉ። ማደሪያውን፥ ድንኳኑን፥ መደረቢያውን፥ መያዣዎቹን፥ ሳንቃዎቹን፥ መወርወሪያዎቹን፥ ምሰሶዎቹን፥ እግሮቹን፤ ታቦቱንና መሎጊያዎቹን፥ የስርየት መክደኛውን፥ መሸፈኛ መጋረጃ፥ ገበታውና መሎጊያዎቹን፥ ዕቃውንም ሁሉ፥ ኅብስተ ገጹን፥ መብራት የሚያበሩበትን መቅረዝና ዕቃውን፥ ቀንዲሉን፥ የመብራቱን ዘይት፤ የዕጣኑን መሠዊያና መሎጊያዎቹን፥ የቅባቱን ዘይት፥ ጥሩ መዓዛ ያለው ዕጣን፥ የድንኳኑን ደጃፍ መጋረጃ፤ የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያና የነሐሱን መከታ፥ መሎጊያዎቹንና ዕቃውን ሁሉ፥ የመታጠቢያውን ሳሕንና ማስቀመጫውን፤ የአደባባዩን መጋረጃዎች፥ ምሰሶዎቹንና እግሮቻቸውን፥ የአደባባዩን ደጃፍ መጋረጃ፤ የማደሪያውን ካስማዎች፥ የአደባባዩን ካስማዎችና አውታሮቻቸውን፤ በመቅደስ ውስጥ ለማገልገል በብልሃት የተሠሩትን ልብሶች፥ በክህነት እንዲያገለግሉበት የተቀደሱትን የካህኑን የአሮን ልብሶችና የልጆቹን ልብሶች።” የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ ከሙሴ ፊት ወጡ። ልቡ ያነሣሣውና መንፈሱ ለመስጠት ፈቃደኛ የሆነ ሰው ሁሉ ለመገናኛው ድንኳን ሥራና ለአገልግሎቱ ሁሉ ለተቀደሰውም ልብስ የሚሆን ለጌታ ስጦታ አመጡ። ልባቸው የተነሣሣ ወንዶችና ሴቶች ሁሉ የአፍንጫ ጌጦችን፥ ሎቲዎችን፥ ቀለበቶችን፥ ድሪዎችን፥ የወርቅ ጌጦችን ሁሉ አመጡ፤ ሰዎች ሁሉ የወርቅ ስጦታ ለጌታ አመጡ። ሰማያዊ፥ ሐምራዊ፥ ቀይ ግምጃ፥ ጥሩ በፍታ፥ የፍየል ጠጉር፥ ቀይ የአውራ በግ ቁርበት፥ የአቆስጣ ቁርበት ያላቸው ሰዎች ሁሉ አመጡ። የብርና የነሐስ ስጦታ መስጠት የሚችል ሁሉ ለጌታ ስጦታ አቀረበ፤ የግራር እንጨት ያለው ሁሉ ለማንኛውም ሥራ አገልግሎት እንዲውል አመጣ። በልባቸው ጥበበኞች የሆኑ ሴቶች ሁሉ በእጃቸው ፈተሉ፥ የፈተሉትንም ሰማያዊውን፥ ሐምራዊውን፥ ቀይ ግምጃውንና ጥሩውን በፍታ አመጡ። ልባቸው በጥበብ ያነሣሣቸው ሴቶች ሁሉ የፍየልን ጠጉር ፈተሉ። አለቆችም የመረግድ ድንጋይ፥ በኤፉድና በደረት ኪስ የሚገቡ ፈርጦችን፥ ቅመማቅመም፥ ለመብራት የሚሆን ዘይት፥ ለቅባት የሚሆን ዘይት፥ ለጣፋጭ ሽታ ዕጣንን አመጡ። ከእስራኤል ልጆች ልባቸው ያነሣሣቸው ወንዶችና ሴቶች ሁሉ ጌታ በሙሴ እጅ እንዲሠራ ላዘዘው ሥራ ሁሉ የሚሆን ስጦታ በፈቃዳቸው ለጌታ አመጡ።