ዘፀአት 1:15-16
ዘፀአት 1:15-16 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
የግብፅም ንጉሥ አንዲቱ ሲፓራ፥ ሁለተኛዪቱም ፎሓ የሚባሉትን የዕብራውያትን አዋላጆች እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ “እናንተ ዕብራውያትን ሴቶች ስታዋልዱ ለመውለድ እንደ ደረሱ በአያችሁ ጊዜ፥ ወንድ ቢሆን ግደሉት፤ ሴት ብትሆን ግን አትግደሏት።”
ያጋሩ
ዘፀአት 1 ያንብቡዘፀአት 1:15-16 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
የግብጽም ንጉሥ ሲፓራና ፉሐ የተባሉትን ዕብራውያን ሴቶች አዋላጆች እንዲህ አላቸው፤ “የዕብራውያንን ሴቶች በማማጫው ድንጋይ ላይ በምታዋልዱበት ጊዜ የሚወለደው ሕፃን ወንድ ከሆነ ግደሉት፤ ሴት ከሆነች ግን በሕይወት ትኑር።”
ያጋሩ
ዘፀአት 1 ያንብቡዘፀአት 1:15-16 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
የግብፅም ንጉሥ አንዲቱ ሲፓራ ሁለተኛይቱም ፉሐ የሚባሉትን የዕብራውያንን አዋላጆች እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ “እናንተ የዕብራያንን ሴቶች ስታዋልዱ፥ ለመውለድ እንደደረሱ ባያችሁ ጊዜ፥ ወንድ ቢሆን ግደሉት፤ ሴት ብትሆን ግን በሕይወት ትኑር።”
ያጋሩ
ዘፀአት 1 ያንብቡ