የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መክብብ 2:17-23

መክብብ 2:17-23 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ከፀ​ሐ​ይም በታች የተ​ሠ​ራው ሥራ ሁሉ በእኔ ላይ ክፉ ነውና ሕይ​ወ​ትን ጠላሁ፥ ሁሉም ከንቱ፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው። ከእኔ በኋላ ለሚ​ወ​ለድ ሰው እተ​ወ​ዋ​ለ​ሁና ከፀ​ሐይ በታች እኔ የደ​ከ​ም​ሁ​በ​ትን ድካም ሁሉ ጠላ​ሁት። ጠቢብ ወይም አላ​ዋቂ እን​ደ​ሚ​ሆን ከፀ​ሐይ በታ​ችም በደ​ከ​ም​ሁ​በ​ትና ጠቢብ በሆ​ን​ሁ​በት በድ​ካሜ ሁሉ ይሰ​ለ​ጥን እንደ ሆነ የሚ​ያ​ውቅ ሰው ማን ነው? ይህም ደግሞ ከንቱ ነው። እኔም ተመ​ልሼ ልቤን ከፀ​ሐይ በታች በደ​ከ​ም​ሁ​በት ድካም ሁሉ ተስፋ አስ​ቈ​ረ​ጥ​ሁት። ሰው በጥ​በ​ብና በዕ​ው​ቀት በብ​ር​ታ​ትም ከደ​ከመ በኋላ ለሌላ ላል​ደ​ከ​መ​በት ሰው ዕድ​ሉን ያወ​ር​ሳ​ልና፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ትል​ቅም መከራ ነው። ከፀ​ሐይ በታች በደ​ከ​መ​በት ድካ​ምና በልቡ ዐሳብ ሁሉ ለሰው አይ​ሆ​ን​ለ​ት​ምና፤ ዘመኑ ሁሉ መከራ፥ ቍጣም፥ ቅሚ​ያም ነው፤ ልቡም በሌ​ሊት አይ​ተ​ኛም፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።

መክብብ 2:17-23 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ከመከራ በቀር ያገኘሁባት ጥቅም ባለመኖሩ ሕይወት በእኔ ዘንድ ትርጒም አልተገኘላትም፤ ይህም ከንቱ ስለ ነበር ነፋስን ለመጨበጥ እንደ መሞከር ይቈጠራል። ያለኝን ሀብት ሁሉ ከእኔ በኋላ ለሚተካው ትቼለት ስለምሄድ በዚህ ዓለም የደከምኩበትና ያተረፍኩት ነገር ሁሉ ከንቱ ነው፤ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ጠቢብ ይሁን ሞኝ ተለይቶ አይታወቅም፤ ይሁን እንጂ እኔ የደከምኩበትንና በጥበቤ ያተረፍኩትን ነገር ሁሉ ወስዶ ባለቤት ይሆናል፤ ይህም ከንቱ ነው። ስለዚህ በዚህ ዓለም የሠራሁትንና የደከምኩበትን ነገር ሁሉ ሳስታውስ ተስፋ አስቈረጠኝ። ባለህ ጥበብ፥ በቀሰምከውም ዕውቀትና ብልኀት የለፋህበትን ሁሉ ምንም ላልደከመበት ሰው ትተህለት ታልፋለህ፤ ይህም ከንቱ ስለ ሆነ ታላቅ መከራ ነው። ታዲያ፥ አስቦና ተጨንቆ በሕይወት ዘመኑ በሚደክምበት ነገር ሁሉ ሰው የሚያተርፈው ቁም ነገር ምንድን ነው? በሕይወቱ ዘመን የሚሠራው ነገር ሁሉ ከሐዘንና ከትካዜ በቀር የሚያተርፍለት ምንም ዐይነት ጥቅም የለም፤ ሌሊት እንኳ አእምሮው ዕረፍት አያገኝም፤ ይህም ሁሉ ከንቱ ነው።