የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘዳግም 30:11-20

ዘዳግም 30:11-20 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

“እኔ ዛሬ የማ​ዝ​ዝህ ይህች ትእ​ዛዝ ከባድ አይ​ደ​ለ​ችም፤ ከአ​ን​ተም የራ​ቀች አይ​ደ​ለ​ችም። ሰም​ተን እና​ደ​ር​ጋት ዘንድ ስለ እኛ ወደ ሰማይ ወጥቶ እር​ስ​ዋን የሚ​ያ​መ​ጣ​ልን ማን​ነው? እን​ዳ​ትል በሰ​ማይ አይ​ደ​ለ​ችም። ሰም​ተን እና​ደ​ር​ጋት ዘንድ ስለ እኛ ባሕ​ሩን ተሻ​ግሮ እር​ስ​ዋን የሚ​ያ​መ​ጣ​ልን ማን ነው? እን​ዳ​ትል ከባ​ሕሩ ማዶ አይ​ደ​ለ​ችም። ታደ​ር​ገው ዘንድ ቃሉ በአ​ፍ​ህና በል​ብህ፥ በእ​ጅ​ህም ውስጥ ለአ​ንተ እጅግ ቅርብ ነው። “እነሆ፥ ዛሬ በፊ​ትህ ሕይ​ወ​ት​ንና ሞትን፥ መል​ካ​ም​ነ​ት​ንና ክፉ​ነ​ትን አኑ​ሬ​አ​ለሁ። ዛሬ እኔ የማ​ዝ​ዝ​ህን የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛ​ዛት ብት​ሰማ፥ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ብት​ወ​ድድ፥ በመ​ን​ገ​ዶ​ቹም ሁሉ ብት​ሄድ፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንና ፍር​ዱ​ንም ብት​ጠ​ብቅ በሕ​ይ​ወት ትኖ​ራ​ለህ፤ በቍ​ጥ​ርም ትበ​ዛ​ለህ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ልት​ወ​ር​ሳት በም​ት​ሄ​ድ​ባት በም​ድ​ሪቱ ሁሉ ይባ​ር​ክ​ሃል። ልብህ ግን ቢስት፥ አን​ተም ባት​ሰማ፥ ብት​ታ​ለ​ልም፥ ለሌ​ሎች አማ​ል​ክ​ትም ብት​ሰ​ግድ፥ ብታ​መ​ል​ካ​ቸ​ውም፥ ፈጽ​መህ እን​ደ​ም​ት​ጠፋ እኔ ዛሬ እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ፤ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ግ​ረህ ትወ​ር​ሳት ዘንድ በም​ት​ገ​ባ​ባት ምድር ዘመ​ንህ አይ​ረ​ዝ​ምም። በፊ​ትህ ሕይ​ወ​ት​ንና ሞትን፥ በረ​ከ​ት​ንና መር​ገ​ምን እን​ዳ​ስ​ቀ​መ​ጥሁ እኔ ዛሬ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን በአ​ንተ ላይ አስ​መ​ሰ​ክ​ራ​ለሁ፤ እን​ግ​ዲህ አን​ተና ዘርህ በሕ​ይ​ወት ትኖሩ ዘንድ ሕይ​ወ​ትን ምረጥ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ባ​ቶ​ችህ ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም እን​ዲ​ሰ​ጣ​ቸው በማ​ለ​ላ​ቸው በም​ድ​ሪቱ ትቀ​መጥ ዘንድ፥ እርሱ ሕይ​ወ​ትህ፥ የዘ​መ​ን​ህም ርዝ​መት ነውና አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ውደ​ደው፤ ቃሉን ስማው፤ አጥ​ና​ውም።”

ዘዳግም 30:11-20 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በዛሬው ዕለት የምሰጥህ ትእዛዝ ይህን ያህል አስቸጋሪ ወይም ከአንተ የራቀች አይደለችም። “እንድንፈጽማት አምጥቶ ይነግረን ዘንድ፣ ማን ወደ ሰማይ ይወጣል?” እንዳትል፣ በላይ በሰማይ አይደለችም። ደግሞም፣ “እንድናደርጋት አምጥቶ ይነግረን ዘንድ፣ ማን ባሕሩን ይሻገራል?” እንዳትልም፣ ከባሕር ማዶ አይደለችም። ነገር ግን ቃሉ ለአንተ በጣም ቅርብ ነው፤ ታደርገውም ዘንድ በአፍህና በልብህ ውስጥ ነው። እነሆ፤ ዛሬ ሕይወትንና በረከትን፣ ሞትንና ጥፋትን በፊትህ አኑሬአለሁ። አምላክህን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) እንድትወድ፣ በመንገዱም እንድትሄድና ትእዛዙን፣ ሥርዐቱንና ሕጉን እንድትጠብቅ አዝዝሃለሁ፤ ከዚያም በሕይወት ትኖራለህ፤ ትበዛለህም፤ አምላክህም እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ትወርሳት ዘንድ በምትገባበት ምድር ይባርክሃል። ዳሩ ግን ልብህ ወደ ኋላ ቢመለስና ባትታዘዝ፣ ለሌሎች አማልክት ለመስገድ ብትታለልና ብታመልካቸው፣ በርግጥ እንደምትጠፉ እኔ በዛሬው ዕለት እነግራችኋለሁ፤ ዮርዳኖስን ተሻግረህ ትወርሳት ዘንድ በምትገባባት ምድር ብዙ አትኖሩባትም። ሕይወትንና ሞትን፣ በረከትንና ርግማንን በፊትህ እንዳስቀመጥሁ ዛሬ ሰማይንና ምድርን ምስክር አድርጌ እጠራብሃለሁ። እንግዲህ አንተና ልጆችህ በሕይወት እንድትኖሩ ሕይወትን ምረጥ፤ ይኸውም አምላክህን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) እንድትወድ፣ ቃሉን እንድታደምጥና ከእርሱ ጋር እንድትጣበቅ ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሕይወትህ ነው፤ ለአባቶችህ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ሊሰጣቸው በማለላቸው ምድር ረዥም ዕድሜ ይሰጥሃል።

ዘዳግም 30:11-20 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እኔ ዛሬ የማዝዝህ ይህች ትእዛዝ ከባድ አይደለችም፥ ከአንተም የራቀች አይደለችም። ሰምተን እናደርጋት ዘንድ ስለ እኛ ወደ ሰማይ ወጥቶ እርስዋን የሚያመጣልን ማን ነው? እንዳትል በሰማይ አይደለችም። ሰምተን እናደርጋት ዘንድ ስለ እኛ ባሕሩን ተሻግሮ እርስዋን የሚያመጣልን ማን ነው? እንዳትል ከባሕሩ ማዶ አይደለችም። ነገር ግን ታደርገው ዘንድ ቃሉ በአፍህና በልብህ ውስጥ ለአንተ እጅግ ቅርብ ነው። ተመልከት፤ ዛሬ በፊትህ ሕይወትንና መልካምነትን፥ ሞትንና ክፋትን አኑሬአለሁ። በሕይወትም እንድትኖር እንድትባዛም፥ አምላክህም እግዚአብሔር ልትወርሳት በምትገባባት ምድር እንዲባርክህ፥ አምላክህን እግዚአብሔርን ትወድድ ዘንድ፥ በመንገዱም ትሄድ ዘንድ ትእዛዙንና ሥርዓቱን ፍርዱንም ትጠብቅ ዘንድ ዛሬ እኔ አዝዝሃለሁ። ልብህ ግን ቢስት አንተም ባትሰማ፥ ብትታለልም፥ ለሌሎችም አማልክት ብትሰግድ ብታመልካቸውም፥ ፈጽማችሁ እንድትጠፉ እኔ ዛሬ እነግራችኋለሁ፤ ዮርዳኖስን ተሻግረህ ትወርሳት ዘንድ በምትገባባት ምድር ዘመናችሁን አታስረዝሙም። በፊታችሁ ሕይወትንና ሞትን በረከትንና መርገምን እንዳስቀመጥሁ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በአንተ ላይ አስመሰክራለሁ፤ እንግዲህ አንተና ዘርህ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ሕይወትን ምረጥ፤ እግዚአብሔርም ለአባቶችህ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም እንዲሰጣቸው በማለላቸው በምድሪቱ ትቀመጥ ዘንድ፥ እርሱ ሕይወትህ የዘመንህም ርዝመት ነውና አምላክህን እግዚአብሔርን ትወድደው ትጠባበቀውም ቃሉንም ትሰማ ዘንድ ምረጥ።

ዘዳግም 30:11-20 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

“ዛሬ እኔ የምሰጥህ ትእዛዝ በጣም ከባድ ወይም ከአንተ የራቀ አይደለም፤ ‘እርሱን ሰምተን እንታዘዘው ዘንድ ማን ወጥቶ ያመጣልናል’ ብለህ እንዳትጠይቅ፥ ይህ ሕግ የሚገኘው በሰማይ አይደለም። ‘እርሱን ሰምተን እንታዘዘው ዘንድ ከባሕር ማዶ ተሻግሮ ማን ሊያመጣልን ይችላል?’ ብለህ እንዳትጠይቅ፥ እርሱ የሚገኘው ከባሕር ማዶ አይደለም። ቃሉ ለእናንተ በጣም ቅርብ ነው፤ ትጠብቀውም ዘንድ በአፍህና በልብህ ውስጥ ይገኛል። “ዛሬ እኔ ሕይወትንና መልካምነትን ወይም ሞትንና ክፋትን እንድትመርጥ ሰጥቼሃለሁ፤ ዛሬ እኔ ለማዝህ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ትእዛዞች ታዛዥ ብትሆን፥ በሕጉ ብትመራ፥ ትእዛዞቹን፥ ሕጎቹንና ሥርዓቱን ብትጠብቅ በሕይወት ትኖራለህ፤ ትበዛለህም፤ አምላክህ እግዚአብሔርም በምትገባበት ምድር ይባርክሃል። ነገር ግን ልብህን ከእግዚአብሔር አርቀህ ቃሉን የማትሰማ ብትሆን፥ ለሌሎችም አማልክት ልትሰግድላቸውና ልታመልካቸው ብትባክን፥ እንደምትደመሰስ እነሆ፥ ዛሬ አስጠነቅቅሃለሁ። ዮርዳኖስን ተሻግረህ በምትወርሳት ምድር ለረጅም ዘመን አትኖርም። እነሆ፥ እኔ በሕይወትና በሞት መካከል፥ በእግዚአብሔር በረከትና መርገም መካከል ምርጫ እሰጣችኋለሁ፤ በምታደርጉትም ምርጫ ሰማይንና ምድርን በአንተ ላይ ምስክር አድርጌ እጠራለሁ፤ ስለዚህም እናንተና ዘሮቻችሁ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ሕይወትን ምረጡ። አምላክህን እግዚአብሔርን ውደድ፤ ለእርሱም ታዛዥ ሁን፤ በእርሱም እመን፤ ይህም ለአንተ ሕይወት ከመሆኑም በላይ ለቀድሞ አባቶችህ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ በመሐላ ቃል በገባላቸው መሠረት ገብተህ በምትኖርባት ምድር ለረጅም ዘመን ትኖራለህ።”

ዘዳግም 30:11-20 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

“ዛሬ የምሰጥህ ትእዛዝ እጅግ አስቸጋሪ ወይም ከአንተ የራቀች አይደለችም። ‘ሰምተን እንድናደርጋት አምጥቶ ይነግረን ዘንድ ማን ወደ ሰማይ ይወጣልናል?’ እንዳትል፥ በላይ በሰማይ አይደለችም። ደግሞም፥ ‘ሰምተን እንድናደርጋት አምጥቶ ይነግረን ዘንድ፥ ማን ባሕሩን ይሻገርልናል?’ እንዳትልም፥ ከባሕር ማዶ አይደለችም። ነገር ግን ቃሉ ለአንተ በጣም ቅርብ ነው፤ ታደርገውም ዘንድ በአፍህና በልብህ ውስጥ ነው። “እነሆ፤ ዛሬ ሕይወትንና መልካምነትን፥ ሞትንና ክፋትን በፊትህ አኑሬአለሁ። ጌታ አምላክህን በመውደድ፥ በመንገዱም በመሄድና ትእዛዙን፥ ሥርዓቱንና ሕጉን በመጠበቅ ያዘዝሁን ካደርግክ፤ በሕይወት ትኖራለህ፤ ትበዛለህም፤ ጌታ አምላክም ትወርሳት ዘንድ በምትገባበት ምድር ይባርክሃል። ልብህ ግን ርቆ አንተም ባትሰማ፥ ለሌሎችም አማልክት ብትሰግድላቸውና ብታመልካቸው ግን፥ ፈጽመህ እንደምትጠፋ እኔ ዛሬ እነግርሃለሁ፤ ዮርዳኖስን ተሻግረህ እንድትወርሳትም በምትገባባት ምድር ረጅም ዘመን አትኖርም። ሕይወትንና ሞትን፥ በረከትንና መርገምን በፊትህ እንዳስቀመጥሁ ዛሬ ሰማይንና ምድርን ምስክር አድርጌ እጠራብሃለሁ። እንግዲህ አንተና ልጆችህ በሕይወት እንድትኖሩ ሕይወትን ምረጥ። ጌታ አምላክህን ውደደው፤ ለቃሉም ታዘዝ፤ ከእርሱም ጋር ተጣበቅ። ጌታ ለአባቶችህም ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ሊሰጣቸው በማለላቸው ምድር የዕድሜህም ዘመን ሕይወትም ማለት ነው።”