ዘዳግም 17:18-19
ዘዳግም 17:18-20 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በመንግሥቱም ዙፋን በተቀመጠ ጊዜ ከሌዋውያን ካህናት ወስዶ ይህን ሕግ ለራሱ በመጽሐፍ ይጻፍ። አምላኩን እግዚአብሔርን መፍራት ይማር ዘንድ፥ የዚህን ሕግ ቃል ሁሉ ይህችንም ሥርዓት ጠብቆ ያደርግ ዘንድ፥ ልቡ በወንድሞቹ ላይ እንዳይኮራ ከትእዛዙም ቀኝና ግራ እንዳይል፥ እርሱም ልጆቹም በእስራኤል ልጆች መካከል ረጅም ዘመን ይነግሡ ዘንድ መጽሐፉ ከእርሱ ጋር ይኑር፥ ዕድሜውንም ሁሉ ያንብበው።
ዘዳግም 17:18-19 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ይልቅስ ንጉሥ በሚሆንበት ጊዜ እነዚህ በሌዋውያን ካህናት ተጠብቀው የሚኖሩት የእግዚአብሔር ሕግጋት የተጻፉበትን መጽሐፍ አንድ ቅጅ እንዲኖረው ያድርግ። ይህን መጽሐፍ አጠገቡ በማኖር በዘመኑ ሁሉ ያንብበው፤ ይህንንም ቢያደርግ እግዚአብሔርን ማክበርና በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፉትንም ሕጎችና ደንቦች በጥንቃቄና በታማኝነት መፈጸምን ይማራል።
ዘዳግም 17:18-19 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
“በግዛቱም በተቀመጠ ጊዜ ከሌዋውያን ካህናት ወስዶ ይህን ሁለተኛ ሕግ ለራሱ በመጽሐፍ ይጻፍ። መጽሐፉ ከእርሱ ጋር ይኑር፤ ዕድሜውንም ሁሉ ያንብበው። አምላኩን እግዚአብሔርን መፍራት ይማር ዘንድ፥ የዚህን ሕግ ቃል ሁሉ፥ ይህችንም ሥርዐት ጠብቆ ያደርግ ዘንድ፥
ዘዳግም 17:18-19 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በመንግሥቱ ዙፋን ላይ በሚቀመጥበትም ጊዜ፣ የዚህን ሕግ ቅጅ ከሌዋውያን ካህናት ወስዶ በጥቅልል መጽሐፍ ለራሱ ይጻፍ። አምላኩን እግዚአብሔርን ማክበር ይማር ዘንድ፣ የዚህን ሕግ ቃል ሁሉና ይህን ሥርዐት በጥንቃቄ ይከተል ዘንድ ከርሱ ጋራ ይሁን፤ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ያንብበው።