የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ቈላስይስ 2:1-8

ቈላስይስ 2:1-8 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ስለ እና​ንተ እና በሎ​ዶ​ቅያ ስላሉ፥ ፊቴ​ንም በሥጋ ስላ​ላ​ዩት ምእ​መ​ናን ሁሉ ምን ያህል እን​ደ​ም​ጋ​ደል ልታ​ውቁ እወ​ዳ​ለሁ። ይኸ​ውም ልቡ​ና​ቸው ደስ ይለው ዘንድ፥ ትም​ህ​ር​ታ​ቸ​ውም በማ​ወቅ፥ በፍ​ቅ​ርና ፍጹ​ም​ነት ባለው ባለ​ጸ​ግ​ነት፥ በጥ​በ​ብና በሃ​ይ​ማ​ኖት፥ ስለ ክር​ስ​ቶ​ስም የሆ​ነ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምክር በማ​ወቅ ይጸና ዘንድ ነው። የተ​ሰ​ወረ የጥ​በ​ብና የም​ክር መዝ​ገብ ሁሉ በእ​ርሱ ዘንድ አለ። ይህ​ንም የም​ላ​ችሁ በሚ​ያ​ባ​ብል ነገር የሚ​ያ​ስ​ታ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ኖር ነው። እኔ በሥጋ ከእ​ና​ንተ ዘንድ ባል​ኖ​ርም እን​ኳን፥ በመ​ን​ፈስ ከእ​ና​ንተ ጋር ነኝ፤ እነሆ ጠባ​ያ​ች​ሁ​ንና ሥር​ዐ​ታ​ች​ሁን፥ በክ​ር​ስ​ቶ​ስም ያለ የእ​ም​ነ​ታ​ች​ሁን ጽናት ስለ አየሁ ደስ ይለ​ኛል። እን​ግ​ዲህ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን እንደ ተቀ​በ​ላ​ች​ሁት፥ በእ​ርሱ ተመ​ላ​ለሱ። በእ​ርሱ ተመ​ሥ​ር​ታ​ችሁ ታነጹ፤ በም​ስ​ጋ​ናው ትበዙ ዘንድ፥ በተ​ማ​ራ​ች​ሁት ሃይ​ማ​ኖት ጽኑ። ለዚህ ዓለም ስሕ​ተት፥ በክ​ር​ስ​ቶስ ሕግ ያይ​ደለ፥ በሰው ሠራሽ ሥር​ዐት ለከ​ንቱ የሚ​ያ​ታ​ልሉ ሰዎች በነ​ገር ማራ​ቀቅ እን​ዳ​ያ​ታ​ል​ሉ​አ​ችሁ፥ ተጠ​ን​ቀቁ።

ቈላስይስ 2:1-8 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ስለ እናንተና በሎዶቅያ ስላሉት እንዲሁም በአካል አይተውኝ ስለማያውቁ ሁሉ ምን ያህል እየተጋደልሁ እንደ ሆነ እንድታውቁ እፈልጋለሁ፤ ደግሞም ልባቸው እንዲጽናናና በፍቅር እንዲተሳሰሩ፣ ፍጹም የሆነውን የመረዳት ብልጽግና አግኝተው የእግዚአብሔር ምስጢር የሆነውን ክርስቶስን እንዲያውቁ እተጋለሁ፤ የተሰወረ የጥበብና የዕውቀት ሀብት ሁሉ የሚገኘው በእርሱ ዘንድ ነውና። ማንም ንግግር በማሳመር እንዳያታልላችሁ ይህን እነግራችኋለሁ። ምንም በሥጋ ከእናንተ ርቄ ብገኝ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝና በሥርዐት መኖራችሁንና በክርስቶስ ያላችሁን ጽኑ እምነት እያየሁ ደስ ይለኛል። እንግዲህ ጌታ ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ተቀበላችሁት እንዲሁ በእርሱ ኑሩ፤ በእርሱ ተተክላችሁና ታንጻችሁ እንደ ተማራችሁት በእምነት ጸንታችሁ፣ የተትረፈረፈ ምስጋና እያቀረባችሁ ኑሩ። በክርስቶስ ላይ ሳይሆን፣ በሰዎች ልማድና በዚህ ዓለም መሠረታዊ ሕግጋት ላይ በተመሠረተ ፍልስፍናና ከንቱ ማግባቢያ ማንም ማርኮ እንዳይወስዳችሁ ተጠንቀቁ።

ቈላስይስ 2:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ስለ እናንተና በሎዶቅያ ስላሉት ፊቴንም በሥጋ ስላላዩት ሁሉ እንዴት ያለ ትልቅ መጋደል እንዳለኝ ልታውቁ እወዳለሁና፤ ልባቸው እንዲጸናና፥ በፍቅርም ተባብረው በማስተዋል ወደሚገኝበት ወደ መረዳት ባለ ጠግነት ሁሉ እንዲደርሱ የእግዚአብሔርንም ምሥጢር እርሱንም ክርስቶስን እንዲያውቁ እጋደላለሁ፤ የተሰወረ የጥበብና የእውቀት መዝገብ ሁሉ በእርሱ ነውና። ማንም በሚያባብል ቃል እንዳያስታችሁ ይህን እላለሁ። በሥጋ ምንም እንኳ ብርቅ፥ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝና፥ ሥርዓታችሁንም በክርስቶስም ያለውን የእምነታችሁን ጽናት እያየሁ ደስ ይለኛል። እንግዲህ ጌታን ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ተቀበላችሁት በእርሱ ተመላለሱ፤ ሥር ሰዳችሁ በእርሱ ታነጹ፥ እንደ ተማራችሁም በሃይማኖት ጽኑ፥ ምስጋናም ይብዛላችሁ። እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን፥ እንደ ሰው ወግና እንደ ዓለማዊ እንደ መጀመሪያ ትምህርት ባለ በፍልስፍና በከንቱም መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠበቁ።

ቈላስይስ 2:1-8 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ስለ እናንተና በሎዶቅያ ስላሉት ሰዎች እንዲሁም ፊቴን እንኳ አይተውት ስለማያውቁ ሰዎች ሁሉ ምን ያኽል ብርቱ ትግል እንደማደርግ ልታውቁ እወዳለሁ። የምታገለውም ልባቸው ተጽናንቶና በፍቅር ተሳስረው፥ ፍጹም ማስተዋልን ሁሉ በማትረፍ የእግዚአብሔር ምሥጢር የሆነውን ክርስቶስን እንዲያውቁ ነው። የጥበብና የዕውቀት ሀብት ተሰውሮ የሚገኘው በክርስቶስ ዘንድ ነው። ይህንንም የምላችሁ ማንም በሽንገላ ቃል እንዳያታልላችሁ ብዬ ነው፤ በሥጋ ከእናንተ ብርቅም እንኳ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ፤ በመልካም ሥነ ሥርዓት መኖራችሁንና በክርስቶስ ላይ ያላችሁን ጽኑ እምነት በማየትም ደስ ይለኛል። ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንደተቀበላችሁት በእርሱ ኑሩ፤ በእርሱ ተመሥርታችሁና ታንጻችሁ፥ በተማራችሁት መሠረት፥ በእምነታችሁ ጸንታችሁ ኑሩ፤ ሞልቶ የሚተርፍ ምስጋናም አቅርቡ። በክርስቶስ ላይ የተመሠረተ ሳይሆን በሰው ሠራሽ ወግና በዓለማዊ ተራ ሥርዓት ላይ በተመሠረተ በፍልስፍናና በከንቱ ሽንገላ ማንም እንዳያጠምዳችሁ ተጠንቀቁ።

ቈላስይስ 2:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ስለ እናንተና በሎዶቅያ ስላሉት ፊቴንም አይተውት ስለማያውቁት ሰዎች ሁሉ ምን ያኽል እንደምጋደል እንድታውቁ እወዳለሁና፤ እንዲህም የምጋደለው ልባቸው እንዲጽናና፥ በፍቅርም በአንድነት እንዲተሳሰሩ፥ በፍጹም ማስተዋልም የሚገኘውን ባለጠግነት ሁሉ እንዲኖራቸው፥ የእግዚአብሔርንም ምሥጢር እርሱንም ክርስቶስን እንዲያውቁ ነው፤ የጥበብና የእውቀት ሀብት ሁሉ ተሰውሮ የሚገኘው በክርስቶስ ዘንድ ነውና። ይህንንም የምለው ማንም አሳማኝ በሚመስል ንግግር እንዳያታልላችሁ ብዬ ነው። በአካል ምንም እንኳ ብርቅ፥ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝና፤ መልካሙንም ሥነ ሥርዓታችሁንና በክርስቶስም ላይ ያላችሁን የእምነታችሁን ጽናት እያየሁ ደስ ይለኛል። እንግዲህ ጌታን ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ተቀበላችሁት በእርሱ ተመላለሱ፤ አብዝታችሁ ምስጋናን በማቅረብ እንደ ተማራችሁት ሥር ሰዳችሁ በእርሱ ታነጹ፤ በእምነትም ጽኑ። እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን እንደ ሰው ወግና እንደ መሠረታዊው የዓለም ረቂቅ መንፈስ በፍልስፍናና በከንቱ መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠንቀቁ።