ሐዋርያት ሥራ 9:32-34
ሐዋርያት ሥራ 9:32-34 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ከዚህም በኋላ ጴጥሮስ በየቦታዉ ሲዘዋወር በልዳ ወደሚኖሩት ቅዱሳን ዘንድ ደረሰ። በዚያም ኤንያ የተሰኘ ሰውን አገኘ፤ እርሱም ታሞ በአልጋ ከተኛ ስምንት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ ሽባ ነበርና። ጴጥሮስም፥ “ኤንያ ሆይ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ይፈውስህ፤ ተነሥና አልጋህን አንጥፍ” አለው፤ ያንጊዜም ተነሣ።
Share
ሐዋርያት ሥራ 9 ያንብቡሐዋርያት ሥራ 9:32-34 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ጴጥሮስም ከአገር ወደ አገር በሚዘዋወርበት ጊዜ፣ በልዳ የሚኖሩትን ቅዱሳን ለመጐብኘት ወረደ። በዚያም ኤንያ የተባለ፣ ስምንት ዓመት የዐልጋ ቍራኛ የነበረ አንድ ሽባ ሰው አገኘ። ጴጥሮስም፣ “ኤንያ ሆይ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ይፈውስሃል፤ ተነሣና መኝታህን አንጥፍ” አለው። ኤንያም ወዲያውኑ ብድግ አለ።
Share
ሐዋርያት ሥራ 9 ያንብቡሐዋርያት ሥራ 9:32-34 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ጴጥሮስም በየስፍራው ሁሉ ሲዞር በልዳ ወደሚኖሩ ቅዱሳን ደግሞ ወረደ። በዚያም ከስምንት ዓመት ጀምሮ በአልጋ ላይ ተኝቶ የነበረውን ኤንያ የሚሉትን አንድ ሰው አገኘ፤ እርሱም ሽባ ነበረ። ጴጥሮስም፦ “ኤንያ ሆይ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ይፈውስሃል፤ ተነሣ ለራስህም አንጥፍ” አለው።
Share
ሐዋርያት ሥራ 9 ያንብቡ