ሐዋርያት ሥራ 7:47-50
ሐዋርያት ሥራ 7:47-50 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ሰሎሞን ግን ቤትን ሠራለት። ነገር ግን ልዑል የሰው እጅ በሠራው ቤት የሚኖር አይደለም፤ ነቢይ እንዲህ ብሎአልና። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ ምን ዐይነት ቤት ትሠሩልኛላችሁ? የማርፍበት ቦታስ ምን ዐይነት ቦታ ነው? ይህን ሁሉ እጆች የሠሩት አይደለምን?’
ሐዋርያት ሥራ 7:47-50 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ነገር ግን የማደሪያውን ቤት የሠራለት ሰሎሞን ነበር። “ይሁን እንጂ፣ ልዑል የሰው እጅ በሠራው ቤት ውስጥ አይኖርም፤ ይህም ነቢዩ እንዲህ ባለው መሠረት ነው፤ “ ‘ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ ማሳረፊያ ናት፤ ታዲያ ምን ዐይነት ቤት ትሠሩልኛላችሁ? ይላል ጌታ፤ ወይንስ ማረፊያ የሚሆነኝ የትኛው ቦታ ነው? ይህን ሁሉ የሠራው እጄ አይደለምን?’
ሐዋርያት ሥራ 7:47-50 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ነገር ግን ሰሎሞን ቤት ሠራለት። ነገር ግን ነቢዩ፦ ‘ሰማይ ዙፋኔ ነው ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ ለእኔ ምን ዓይነት ቤት ትሠራላችሁ?’ ይላል ጌታ፥ ወይስ የማርፍበት ስፍራ ምንድር ነው? ይህንስ ሁሉ እጄ የሠራችው አይደለምን? እንዳለ፥ ልዑል የሰው እጅ በሠራችው አይኖርም።
ሐዋርያት ሥራ 7:47-50 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ነገር ግን ለእግዚአብሔር ቤት የሠራው ሰሎሞን ነው። “ሆኖም ልዑል እግዚአብሔር በሰው እጅ በተሠራ ቤት ውስጥ አይኖርም፤ ይህም ነቢዩ እንዲህ ሲል እንደ ጻፈው ነው፤ ‘ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ ማሳረፊያ ናት፤ ታዲያ ለእኔ ምን ዐይነት ቤት ትሠሩልኛላችሁ? የማርፍበትስ ቦታ ምን ዐይነት ነው? ይላል ጌታ። ይህን ሁሉ እኔ በእጄ የሠራሁት አይደለምን?’ ይላል እግዚአብሔር።