ሐዋርያት ሥራ 4:7-10
ሐዋርያት ሥራ 4:7-10 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እነርሱም ጴጥሮስንና ዮሐንስን በመካከል አቁመው፣ “ይህን ያደረጋችሁት በምን ኀይል ወይም በማን ስም ነው?” ብለው ጠየቋቸው። በዚህ ጊዜ፣ ጴጥሮስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ የሕዝብ አለቆችና ሽማግሌዎች ሆይ፤ ዛሬ ለዚህ ሽባ ሰው ስለ ተደረገው በጎ ሥራ፣ እንዴት እንደ ዳነ የምትጠይቁን ከሆነ፣ እናንተ በሰቀላችሁት፣ እግዚአብሔር ግን ከሙታን ባስነሣው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም መዳኑንና ፊታችሁ መቆሙን እናንተም ሆናችሁ የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ይህን ይወቅ።
ሐዋርያት ሥራ 4:7-10 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በአደባባይም አቆሙና፥ “እናንተ ይህን በማን ስምና በማን ኀይል አደረጋችሁት?” ብለው መረመሩአቸው። ያንጊዜም በጴጥሮስ መንፈስ ቅዱስ ሞላበትና እንዲህ አላቸው፥ “እናንተ የሕዝብ አለቆችና ሽማግሌዎች ሆይ፥ ስሙ፤ ዛሬ ለበሽተኛው በተደረገው ረድኤት ምክንያት በእናንተ ዘንድ እኛ የሚፈረድብን ከሆነ እንግዲያ ይህ ሰው በምን ዳነ? እንግዲህ እናንተ ሁላችሁ፥ የእስራኤልም ወገን ሁሉ፥ እናንተ በሰቀላችሁት፥ እግዚአብሔርም ከሙታን ለይቶ በአስነሣው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይህ ሰው እንደ ዳነና በፊታችሁም እንደ ቆመ በርግጥ ዕወቁ።
ሐዋርያት ሥራ 4:7-10 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እነርሱንም በመካከል አቁመው፦ “በምን ኃይል ወይስ በማን ስም እናንተ ይህን አደረጋችሁ?” ብለው ጠየቁአቸው። በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የሕዝብ አለቆችና ሽማግሌዎች፥ እኛ ዛሬ ለድውዩ ሰው ስለ ተደረገው መልካም ሥራ ይህ በምን እንደዳነ ብንመረመር፥ እናንተ በሰቀላችሁት እግዚአብሔርም ከሙታን ባስነሣው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይህ ደኅና ሆኖ በፊታችሁ እንደ ቆመ፥ ለእናንተ ለሁላችሁ ለእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ የታወቀ ይሁን።
ሐዋርያት ሥራ 4:7-10 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እነርሱም ሁለቱን ሐዋርያት በመካከላቸው አቁመው፥ “ይህን ያደረጋችኹት በምን ኀይል ወይም በማን ስም ነው?” ሲሉ ጠየቁአቸው። በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እናንተ የሕዝብ አለቆችና ሽማግሌዎች ሆይ! እኛ ዛሬ የምንጠየቀው ለአንድ ሽባ ሰው ስለ ተደረገለት መልካም ሥራና በምን ዐይነት ሁኔታ እንደ ዳነ ነው። ይህ ሰው ድኖ በፊታችሁ የቆመው እናንተ በሰቀላችሁትና እግዚአብሔር ግን ከሞት ባስነሣው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንደ ሆነ ለእናንተ ለሁላችሁና ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ የታወቀ ይሁን።
ሐዋርያት ሥራ 4:7-10 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
እነርሱንም በመካከል አቁመው “በምን ኃይል ወይስ በማን ስም እናንተ ይህን አደረጋችሁ?” ብለው ጠየቁአቸው። በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ እንዲህ አላቸው “እናንተ የሕዝብ አለቆችና ሽማግሌዎች፥ እኛ ዛሬ ለድውዩ ሰው ስለተደረገው መልካም ሥራ ይህ በምን እንደ ዳነ ብንመረመር፥ እናንተ በሰቀላችሁት እግዚአብሔርም ከሙታን ባስነሣው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይህ ደኅና ሆኖ በፊታችሁ እንደ ቆመ፥ ለእናንተ ለሁላችሁ ለእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ የታወቀ ይሁን።