ሐዋርያት ሥራ 4:29-30
ሐዋርያት ሥራ 4:29-30 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
አሁንም፥ ጌታ ሆይ፥ ወደ ዛቻቸው ተመልከት፤ ለመፈወስም እጅህን ስትዘረጋ በቅዱስ ብላቴናህም በኢየሱስ ስም ምልክትና ድንቅ ሲደረግ፥ ባሪያዎችህ በፍጹም ግልጥነት ቃልህን እንዲናገሩ ስጣቸው።”
Share
ሐዋርያት ሥራ 4 ያንብቡሐዋርያት ሥራ 4:29-30 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
አሁንም ጌታ ሆይ፥ ዛቻቸውን ተመልከት፤ አገልጋዮችህ ቃልህን ያለ ፍርሀት በድፍረት እንዲናገሩ አድርግ፤ በቅዱሱ ልጅህ በኢየሱስ ስም በሽተኞች እንዲድኑና ተአምራትም፥ ድንቅ ነገሮችም እንዲደረጉ እጅህን ዘርጋ።”
Share
ሐዋርያት ሥራ 4 ያንብቡሐዋርያት ሥራ 4:29-30 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
አሁንም አቤቱ፥ ትምክህታቸውን ተመልከት፤ ቃልህንም በግልጥ ያስተምሩ ዘንድ ለባሮችህ ስጣቸው። በቅዱሱ ልጅህም በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሕሙማንን ትፈውስ ዘንድ ተአምራትንና ድንቅ ሥራንም ታደርግ ዘንድ እጅህን ዘርጋ።”
Share
ሐዋርያት ሥራ 4 ያንብቡ