የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሐዋርያት ሥራ 27:21-26

ሐዋርያት ሥራ 27:21-26 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ከእ​ኛም መብል የበላ አል​ነ​በ​ረም። ጳው​ሎ​ስም ተነ​ሥቶ በመ​ካ​ከል ቆመና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ ሰዎች ሆይ፥ ቀድሞ ቃሌን ሰም​ታ​ች​ሁኝ ቢሆን ከቀ​ር​ጤ​ስም ባት​ወጡ ኖሮ ከዚህ ጕዳ​ትና መከራ በዳ​ና​ችሁ ነበር። አሁ​ንም እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ መር​ከ​ባ​ችን እንጂ ከመ​ካ​ከ​ላ​ችን አንድ ሰው ስንኳ አይ​ጠ​ፋ​ምና አት​ፍሩ። እኔ ለእ​ርሱ የም​ሆ​ንና የማ​መ​ል​ከው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የላ​ከው መል​አክ በዚች ሌሊት በአ​ጠ​ገቤ ቆሞ ነበ​ርና። እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፦ ‘ጳው​ሎስ ሆይ፥ አት​ፍራ፤ በቄ​ሣር ፊት ልት​ቆም ይገ​ባ​ሃል፤ ከአ​ን​ተም ጋር የሚ​ሄ​ዱ​ትን ሁሉ እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ንተ ሰጥ​ቶ​ሃል።’ አሁ​ንም ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ እንደ ነገ​ረኝ እን​ደ​ሚ​ሆን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ና​ለ​ሁና። ነገር ግን ወደ አን​ዲት ደሴት እን​ደ​ር​ሳ​ለን።”