ሐዋርያት ሥራ 20:7-11
ሐዋርያት ሥራ 20:7-11 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ከሳምንቱም በመጀመሪያው ቀን እሑድ ማዕድ ለመባረክ ተሰብስበን ሳለን ጳውሎስ በማግሥቱ የሚሄድ ነውና ያስተምራቸው ጀመረ፤ እስከ መንፈቀ ሌሊትም ድረስ ትምህርቱን አስረዘመ። ተሰብስበን በነበርንበት ሰገነትም ብዙ መብራት ነበር። ስሙ አውጤክስ የሚባል አንድ ጐልማሳ ልጅም በመስኮት በኩል ተቀምጦ ሳለ ከባድ እንቅልፍ አንቀላፍቶ ነበር፤ ጳውሎስም ትምህርቱን ባስረዘመ ጊዜ ያ ጐልማሳ ከእንቅልፉ ብዛት የተነሣ ከተኛበት ከሦስተኛው ፎቅ ወደ ታች ወደቀ፤ ሬሳውንም አነሡት። ጳውሎስም ወርዶ በላዩ ወደቀ፤ አቅፎም ያዘው፤ እነርሱንም፥ “ነፍሱ አለችና አትደንግጡ” አላቸው። ከዚህም በኋላ ወደ ሰገነት ወጣ፤ ማዕዱንም ባርኮ በላ፤ እስኪነጋም ድረስ ብዙ ትምህርት አስተማራቸው፤ ከዚያ በኋላም ተነሥቶ ሄደ።
ሐዋርያት ሥራ 20:7-11 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን እንጀራ ለመቍረስ ተሰብስበን ሳለን፣ ጳውሎስ በማግስቱም ለመሄድ ስላሰበ፣ ከእነርሱ ጋር ይነጋገር ነበር፤ ንግግሩንም እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ አራዘመ። በተሰበሰብንበትም ሰገነት ላይ ብዙ መብራት ነበር። አውጤኪስ የተባለ አንድ ጐበዝም በመስኮት ላይ ተቀምጦ ነበር፤ ጳውሎስ ንግግሩን ባስረዘመ ጊዜ፣ እንቅልፍ እንቅልፍ አለውና ጭልጥ ብሎ ተኛ፤ ከሦስተኛውም ፎቅ ቍልቍል ወደቀ፤ ሞቶም አነሡት። ጳውሎስም ወርዶ በላዩ ተጋድሞ ዐቀፈውና፣ “ሕይወቱ በውስጡ ስላለች ሁከት አትፍጠሩ” አላቸው። ተመልሶም እንደ ገና ወደ ፎቁ ወጣ፤ እንጀራውንም ቈርሶ በላ፤ እስኪነጋም ድረስ ብዙ ከተናገረ በኋላ ተነሥቶ ሄደ።
ሐዋርያት ሥራ 20:7-11 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ከሳምንቱም በመጀመሪያ ቀን እንጀራ ለመቁረስ ተሰብስበን ሳለን፥ ጳውሎስ በነገው ሊሄድ ስላሰበ ከእነርሱ ጋር ይነጋገር ነበር፥ እስከ መንፈቀ ሌሊትም ነገሩን አስረዘመ። ተሰብስበንም በነበርንበት ሰገነት እጅግ መብራት ነበረ። አውጤኪስ የሚሉትም አንድ ጎበዝ በመስኮት ተቀምጦ ታላቅ እንቅልፍ አንቀላፍቶ ነበር፤ ጳውሎስም ነገርን ባስረዘመ ጊዜ እንቅልፍ ከብዶት ከሦስተኛው ደርብ ወደ ታች ወደቀ፥ ሞቶም አነሡት። ጳውሎስም ወርዶ በላዩ ወደቀ፥ አቅፎም፦ ነፍሱ አለችበትና አትንጫጩ አላቸው። ወጥቶም እንጀራ ቆርሶም በላ፤ ብዙ ጊዜም እስኪነጋ ድረስ ተነጋገረ እንዲህም ሄደ።
ሐዋርያት ሥራ 20:7-11 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ከሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን እንጀራ ቈርሶ በአንድነት ለመብላት ተሰበሰብን፤ ጳውሎስ በማግስቱ መሄድ ስለ ነበረበት ለተሰበሰቡት ሰዎች ይናገር ነበር፤ ንግግሩንም እስከ እኩለ ሌሊት አስረዘመ። እኛ በተሰበሰብንበት ፎቅ ብዙ መብራት ነበር። ኤውጤኪስ የተባለ አንድ ወጣት በመስኮት ላይ ተቀምጦ ነበር፤ ጳውሎስ ንግግሩን በማስረዘሙ ወጣቱ ከባድ እንቅልፍ ያዘው፤ እንቅልፍ ስላሸነፈውም ከሦስተኛው ፎቅ ወደ ታች ወደቀ፤ ሰዎች ባነሡት ጊዜ ሞቶ አገኙት። ነገር ግን ጳውሎስ ወርዶ በልጁ ላይ ጐንበስ በማለት አቀፈውና “ገና በሕይወት አለ፤ አትደንግጡ!” አለ። ጳውሎስ ወደ ፎቅ ተመልሶ ወጣና እንጀራ ቈርሶ ከአማኞች ጋር በላ፤ እስኪነጋም ድረስ ከሰዎቹ ጋር ሲነጋገር ከቈየ በኋላ ሄደ።
ሐዋርያት ሥራ 20:7-11 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ከሳምንቱም በመጀመሪያ ቀን እንጀራ ለመቁረስ ተሰብስበን ሳለን፥ ጳውሎስ በነገው ሊሄድ ስላሰበ ከእነርሱ ጋር ይነጋገር ነበር፤ እስከ መንፈቀ ሌሊትም ነገሩን አስረዘመ። ተሰብስበንም በነበርንበት ሰገነት እጅግ መብራት ነበረ። አውጤኪስ የሚሉትም አንድ ጎበዝ በመስኮት ተቀምጦ ታላቅ እንቅልፍ አንቀላፍቶ ነበር፤ ጳውሎስም ነገርን ባስረዘመ ጊዜ እንቅልፍ ከብዶት ከሦስተኛው ደርብ ወደ ታች ወደቀ፤ ሞቶም አነሡት። ጳውሎስም ወርዶ በላዩ ወደቀ፤ አቅፎም “ነፍሱ አለችበትና አትንጫጩ፤” አላቸው። ወጥቶም እንጀራ ቆርሶም በላ፤ ብዙ ጊዜም እስኪ ነጋ ድረስ ተነጋገረ እንዲህም ሄደ።